Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,913 episodes available.
May 20, 2025የአፍ ምሬት መንስኤው ምን ይሆን?አፌን መረረኝ ወይም ምሬት ተሰማኝ ሲባል ሰምተን ይሆናል አለያም እኛም አጋጥሞን ሊሆን ይችላል። የህክምና ባለሙያዎች ለአፍ ምሬት መንስኤው አንድ ብቻ አይደለም ነው የሚሉት።...more11minPlay
May 19, 2025ማሕደረ ዜና፣ የምርጫ 97 ሒደት፣ዉጤትና አሳዛኝ ፍፃሜዉ 20 ዓመት ደፈነከ25 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፅ ሰጥቶበታል።ሕዝባዊ፣ ታሪካዊ፣ አብነታዊም ነበር።የአሸናፊ-ተሸናፊዉ ዉዝግብ፣ የገዢዉ ፓርቲ ጨካኝ ርምጃና እስከዛሬ የተረፈዉ መዘዝ ሲጤን ግን ራቅ ሲል በ1953 በአፄ ኃይለ ሥላሴ ላይ ከሞከረዉ መፈንቅለ መንግስት፣ ቀረብ ሲል በ1969 በኮሌኔል መንሥቱ ላይ ከተሞከረዉ የግድያ ጥቃት ዉጤት ጋር የሚያመሳስሉት አሉ።...more16minPlay
May 19, 2025የጤና አገልግሎት ፈላጊዎች ቅሬታ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታልበአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተገልጋዮች በህክምና ባለሙያዎች እጥረት አገልገሎት ለማግኘት መቸገራቸውን አመለከቱ።...more4minPlay
May 19, 2025የቀጠለው የሐኪሞች ሥራ ማቆም አድማሰሞኑን የተጀመረው የጤና ባለሙያዎች የሥራ ማቆም አድማ ዛሬም በአንዳንድ ሆስፒታሎች ቀጥሎ መዋሉን የንቅናቄው አስተባባሪዎች ተናግሩ። አንዳንዶቹ ደግሞ በከፊልም ቢሆን በሥራ ላይ እንደሆኑ ገልጠዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ማዕከል 75 የጤና ባለሙያዎች መታሰራቸውን አመልክቷል።...more4minPlay
May 19, 2025«ሥራችንን እየሰራን ትግላችን በሰላማዊ መንገድ እንቀጥላለን» የጤና ባለሙያዎችየጤና ባለሙያዎች ተገደን ወደ ስራ እንድንመለስ ተደረግን አሉ። በአማራ ክልል የጤና ባለሙያዎች እንቅስቃሴን የተቀላቀሉ በደሴ ከተማና ምእራብ ወሎ አካባቢ በሚገኙ የጤና ተቋማት የሚሰሩ ባለሙያዎች ለእስራት ጭምር መዳረጋቸዉን ገለፁ። የአማራ ክልል የጤና ባለሙያዎች ለምናነሳው የደመወዝ ጥያቄ ስራችንን እየሰራን ትግላችንን እንቀጥላለን ብለዋል።...more4minPlay
May 19, 2025ሶማሊላንድ ከሶማሊያ መነጠሏን ያወጀችበት 34ኛ ዓመትሶማሊላንድ ከሶማሊያ መነጠሏን ያወጀችበትና ራሷን እንደ ነጻ ሀገር የቆጠረችበት 34ኛውን "ብሔራዊ የነፃነት ቀን" ትናንት እሑድ ሀርጌሳ ላይ አክብራለች። ሶማሊያ የሉዓላዊ ግዛቷ አንድ አካል አድርጋ የምታያት ሶማሊላንድ፣ በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትዕይንቶችን አቅርባለች።...more4minPlay
May 19, 2025ህወሓት በመንግሥት ላይ ያቀረበዉ ወቀሳየኢትዮጵያ መንግስት ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ከፍቶብኛል ሲል ህወሓት ከሰሰ። ህወሓት እንዳለው የፕሪቶርያ ስምምነት የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ እንዲቆሙ የሚደነግግ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት ይህ ወደጎን በመግፋት 'በትግራይ ህዝብ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ተቋማት ላይ' በባለስልጣናቱ እና ሚድያዎች በኩል የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ እያካሄደ ነው ሲል ወቀሰ።...more0minPlay
May 19, 2025የግንቦት 11 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባየአትሌቶች የእድሜ ማጭበርበር ጉዳይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን እጅግ ያሳሰበው ይመስላል ። ኢትዮጵያ ውስጥ አዳጊ እና ወጣት አትሌቶች እንደ እነ መዲና በዓለም አቀፍ መድረክ ብርቱ ተፎካካሪ እንዲሆኑ ምን መደረግ አለበት? ቃለ መጠይቅ አድርገናል። የኤፍ ኤ ካፕ፣ ፕሬሚየር ሊግ፣ ቡንደስሊጋ እንዲሁም ሌሎች ስፖርታዊ መረጃዎችንም አካተናል ።...more10minPlay
May 18, 2025የኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ ከ1997 ምርጫ ወዲህ ከወዴት አለ?በ1997 ምርጫ ኢሕአዴግን የተገዳደሩት ፓርቲዎች ባለፉት 20 ዓመታት ተዳክመዋል። ኢሕአዴግን በብልጽግና ፓርቲ የተካው ለውጥ ያነቃቃቸውም ተከፋፍለዋል። የፓርቲ ፖለቲካ በኢትዮጵያ ሞተ ወይስ እያጣጣረ ነው? ይህ ውይይት ዶክተር ብዙነህ ጌታቸው እና ዶክተር አዲሱ ላሽተውን በመጋበዝ የፓርቲ ፖለቲካን በ2018 ሊካሔድ ከታቀደው ምርጫ አኳያ ይዳስሳል።...more44minPlay
May 17, 2025ትኩረት በአፍሪቃ፤ የሱዳን ጦርነት፣የአረብና የአሜሪካኖች አቋም፣ የማሊ ፓርቲዎች መታገድሰዉ አልባ አዉሮፕላኖቹን ለፈጥኖ ደራሹ ጦር ያስታጠቀችዉ ወይም ግዢዉን ያመቻቸዉ ወትሮም ለጄኔራል ሐምቲ ጠንካራ ድጋፍ ትሰጣለች የምትባለዉ የተባበሩት አረብ አረብ ኤምሬቶች ናት ይባላል። የሱዳን መንግስት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን በዘር ማጥፋት ወንጀል ICJ በሚል ምሕፃረ ቃል በሚጠ,ራዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፍርድ ቤት ላይ ከስሷታል።...more12minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,913 episodes available.