Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,913 episodes available.
May 23, 2025በካማሺ ዞን ምዥጋ ወረዳ 18 ሰዎች ተገደሉ፤ ሶስት ታገቱበተጨማሪ 10 ሰዎች ወደ ነቀምት ሆስፒታል ለህክምና መሄዳቸውን አስተያየጣውን የሰጡን ነዋሪ ተናግረዋል፡፡ በወረዳው ከተማ ሶጌ ከተባለው ከተማ በ45 ኪ.ሜ ርቀት ገደማ ላይ በሚትገኘው አንገር መጢ ወይም ‹‹አይሻንጅድም›› በተባለው ከተማ ጥቃቱ መድረሱን የተናገሩት አንድ የአካባቢው ነዋሪ የተገደሉት ሁሉም ሰላማዊ ሰዎች መሆናቸው አመልክተዋል፡፡...more4minPlay
May 23, 2025የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሸቀጥ ለሚያስገቡና ለተጓዦች የሚፈቀደዉን የውጭ ምንዛሪ መጠን ጨመረባንኩ የውጭ ምንዛሪ ገቢያ ስርዓቱን ይበልጥ ለማጠናከር ወሰድኩ ያሏቸው አድርምጃዎች፤ አንደኛው ለአስመጪዎች የቅድመ ክፍያ መጠንን ከፍ የማድረግ ውሳኔ ነው ብሏል፡፡ በዚህም ሸቀጦችን ከውጪ ለማስገባት ሊከፈል የሚችለውን የቅድመ ክፍያ መጠን ከ5 ሺህ ወደ 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከፍ ማለቱ ነው ያስታወቀው፡፡...more4minPlay
May 23, 2025አንድ ለአንድ- የሕወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዝ እና ቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዋና ተዋናይ ሆኖ የቆየው ሕወሓት፤ ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቅርቡ አስታውቋል።ከ50 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉልህ ስፍራ ይዞ የቆየው ህወሓት መሰረዙ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ፖለቲካ ምን ያዞ ይመጣ ይሆን?...more24minPlay
May 22, 2025የጤና ባለሞያዎች የሥራ ማቆም አድማ፤ የውጭ ዜጎችን የመሬት ባለቤት የሚያደርገው ረቂቅ ሕግ፤ የተጠናከረው የጋዛ ጦርነት«ሰውን በህይወት ለማቆየት ከሞት ጋር ሲታገል የሚውል ሐኪም ስለ ቤት ኪራይና ስለ አስቤዛ ማሰብ አልነበረበትም። ሐኪሞችን እንደማንኛውም ሙያተኛ ከፈለጉ ይተውት ብለን ልንበትናቸው የማንችላቸው እንዲሁም አስገድደን ልናሠራቸው የማንችላቸው በህሊና እዳ የታጨቀ ሙያ ያላቸው ተገደን የምንፈልጋቸው እንቁ ምሁራን ናቸው ። የሚገባቸውን ክብር ስጡዋቸው»...more9minPlay
May 22, 2025ሦስተኛው የአውሮጳ ኅብረትና አፍሪቃ አገሮች የሚኒስትሮች ስብሰባሦስተኛው የአውሮጳ ኅብረትና የአፍሪቃ ኅብረት አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የጋራ ስብሰባ ትናንት ቤልጂየም ብራስልስ ከተማ ውስጥ ተካሂዶ ውሳኔ በማሳለፍና የጋራ መግለጫ በማውጣት ተጠናቅቋል። በስብሰባው 50 ሚኒስትሮችን ጨምሮ ከ70 በላይ ልኡካን የተሳተፉ መሆኑ ታውቋል ።...more4minPlay
May 22, 2025በውጪው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ቀጣይነት ያለዉ ባህል ትውፊታቸዉበውጪው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አንዱ ፈተና እዚህ የሚወለዱ ህጻናት ልጆቻቸው፣ ወግ እና ባህላቸውን፣ ቋንቋና ማንነታቸውን፣ ትውፊትና ስርዓታቸውን ይዘው እንዲያድጉ ማድረጉ ነው። ለዚህ ፈተና አንዱ መነሾ ደግሞ የሚያድጉበት ስርዓት፣ ቋንቋና ባህል ውስጥም ሙሉ በሙሉ ገብተው አሸንፈው መውጣታቸውም ግድ ማለቱ ነው።...more13minPlay
May 22, 2025የጤና ባለሞያዎች ጥያቄዎች ትኩረት እንዲሰጣቸውና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ ኢሰመኮ አሳሰበበጤና ባለሞያዎች የቀጠለው የሥራ ማቆም አድማ እና በመንግሥት የሚወሰዱ ርምጃዎች አፋጣኝ መፍትኄ ሊያገኙ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ። ችግሩ በመቀራረብ እና በመነጋገር ሊፈታ ይገባል ያለው ኢሰመኮ ፖሊስ የሕክምና ባለሞያዎችን በቁጥጥር ሥር እያዋለ መሆኑን መገንዘቡንም ዐሳውቋል።...more4minPlay
May 22, 2025የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በሽሬ ቆይታቸው ስለተፈናቃዮች የተናገሩትየተፈናቃዮች ጉዳይ ከፖለቲካዊ አጀንዳ በማስቀደም ተፈናቃዮች ወደቀያቸው መመለስ እንደሚገባ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ አሳሰቡ። አምባሳደሩ በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ ተገኝተው ተፈናቃዮች ያሉበት ሁኔታ በተመለከቱበት ወቅት፥ በቅርቡ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከተሰረዘው ሕወሓት አመራሮች ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን ተገለፀ።...more3minPlay
May 22, 2025ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የደቡብ አፍሪቃ አቻቸውን አሳጡፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኋይት ሐውስ ቢሮዋቸው ውስጥ የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳን በአደባባይ የማሳጣት ተግባር ፈጽመዋል። ቪዲዮ በማሳየት እና የኅትመት ውጤቶችንም በማጣቀስ ፕሬዝዳንት ራማፎሳንና አስተዳደራቸውን ከስሰዋል። የፕሬዝዳንቱ ክስ በገለልተኛ አካላት ማስረጃ ያልቀረበበት ነው ።...more4minPlay
May 21, 2025በወሊሶ ከተማ እና አከባቢው ኤሌክትሪክ እና ውኃ ከተቋረጠ ሦስት ሳምንት ተጠግቷልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ወሊሶ ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ አበራ በዳዳ የችግሩ መንስኤ በወልቂጤ የሚገኘው ትልቁ ሰብስቴሽን የአሌክትሪክ ማስተላለፊያ ትራንስፎርመር ላይ ጉዳት መድረሱ ነው ብለዋል። ወሊሶ እራሱን የቻለ ሰብስቴሽን ይሰራል ተብሎ ከዚህ በፊት ለህዝቡ ቃል መገባቱን የሚናገሩት ነዋሪዎች ያ ባለመሰራቱ ነው ለችግሩ የተዳረግነው” ይላሉ፡፡...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,913 episodes available.