Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.
May 10, 2025የሞት ቅጣት ያስቀጣል የተባለው የታንዛኒያ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ክስቻዴማ የተባለው የታንዛኒያ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ቱንዱ ሊሱ ባለፈው ወር ባደረጉት ንግግር ፤ ታንዛኒያውያን እንዲያምፁ እና የአገሪቱን ፕሬዚዳንታዊ እና የፓርላማ ምርጫ እንዲረብሹ አድርገዋል ተብለው በቁጥጥር ስር ውለዋል። ቲንዱ የተከሰሱት በሀገር መክዳት ሲሆን፤የሞት ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተብሏል።...more6minPlay
May 10, 2025በአፋር ክልል ለሰብአዊ ርዳታ ፈላጊዎች “ከዩኤስኤይድ ብዙ ድጋፍ ይገኝ” የነበረ ቢሆንም ተቀዛቅዟልየአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (USAID) የሚያደርገው ድጋፍ ከቆመ በኋላ በአፋር ክልል የሰብአዊ ርዳታ ጉዳይ ሥጋት ፈጥሯል። ለሰብአዊ ርዳታ ፈላጊዎች “ከዩኤኤይድ ብዙ ድጋፍ ይገኝ” የነበረ ቢሆንም መቀዛቀዙን የክልሉ ባለሥልጣን ለዶቸ ቨለ ተናግረዋል። ተቋሙ ለግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የሚሰጠው ድጎማ መቆም የሠራተኞች ስንብት አስከትሏል።...more4minPlay
May 10, 2025በኦሮሚያ ክልል አሙሩ ወረዳ ልጆቻቸው ከታጣቂዎች የተቀላቀሉ የተባሉ ነዋሪዎች ቤታቸው በጸጥታ ኃይሎች መቃጠሉን ተናገሩበኦሮሚያ ክልል አሙሩ ወረዳ ልጆቻቸው ከታጣቂዎች የተቀላቀሉ ነዋሪዎች ቤቶች መቃጠላቸውን እማኞች ተናገሩ። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው እንደሚሉት በወታደራዊ የጦር ሠፈር የታሠሩ፤ ድብደባ የተፈጸመባቸው ሰዎች አሉ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ቅሬታዎቹ እንደደረሱት ቢያረጋግጥም በአካባቢው የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት ምርመራ እንዳላከናወነ ገልጿል።...more4minPlay
May 10, 2025በአማራ ክልል ሆስፒታሎች የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄዎች የደገፉ ሰልፎች ተካሔዱየጤና ባለሙያዎችን የማህበራዊ ንቅናቄ ዘመቻ በመደገፍ በአማራ ክልል የተለያዩ የጤና ተቋማት ሠላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ ባለሙያዎቹ ጥያቄዎቻቸው ምላሽ ካላገኙ ከነገ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ ከአንድ ወር በፊት አስጠንቅቀዋል። የጤና ሚኒስቴር ለባለሙያዎች ጥያቄዎች እውቅና እንድሚሰጥና በእቅድ ምላሸ እንደሚሰጥ ቀደም ሲል አሳውቋል፡፡...more4minPlay
May 09, 2025በከፋ ችግር ምያንማር ከነበሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 82ቱ አዲስ አበባ ገቡምያንማር ውስጥ ለዘጠኝ ወራት "በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ" የቆዩ 82 ኢትዮጵያውያን ዛሬ አርብ ግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን መካከል 41ዱ ከሁለት ቀናት በፊት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውንም ቤተሰቦቻቸውና ከተመለሱት መካከል አንዱ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።...more4minPlay
May 09, 2025አንድ ለ አንድ ፦ ከኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፈደሬሽን ፕሬዝዳንት ጋርከኢትዮጵያ ሠራተኞች ዋና ዋና ችግሮች መካከል አሳሳቢው የሠራተኞች የኑሮ ሁኔታ፣ ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል አለመወሰን የገቢ ግብር ማሻሻያ ተግባራዊ አለመሆን እንደሚገኙበት የሠራተኞች ማኅበራት መሪዎች የአባላቶቻቸው የመብት ጥያቄ እንዲከበር ሲጠይቁ ከስራ መባረር ፣ራቅ ወዳለ ቦታ እንዲዘዋወሩ ማድረግም ይጠቀሳሉ ብለዋል።...more16minPlay
May 09, 2025በህክምና ሙያ ተመርቃ ተሰዳ ለመስራት የተገደደች ወጣትበኢትዮጵያ በጤና ባለሙያዎች የሚነሳው የተመጣጣኝ ደመወዝ ጥያቄ የበርካቶችን ትኩረት እንደሳበ ዘልቋል፡፡ በዘርፍ በመመረቅ ለተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በሙያው በመስራት የተሻለ ክፍያ ፍለጋ ወደ ሌላ አገር ተሰዳ እስከመስራት መድረሷን የምትገልጸው የህክምና ባለሞያ ወቅታዊውን የባለሞያዎቹን ዘመቻ ተገቢ ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች፡፡...more4minPlay
May 09, 2025የመቐለ ልደታ ማርያም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መልካም ምኞትአሜሪካዊው አዲሱ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ተኛ የአሜሪካ መንግስት በስደተኞች ላይ የያዘውን አቋም እንዲቀይር እንዲሁም የእርዳታ ስራዎችን ያስተጓጎለዉ ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤን በትኩረት ይሰራሉ ብለው እንደሚጠብቁ የመቐለ ልደታ ማርያም ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ቆሞስ አባ ጥዑም በርሃ ገለፁ።...more3minPlay
May 09, 2025ርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በምርጫዉ ማግስትለአዲሱ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከዓለም መንግሥታትና የመንግሥታት ተጠሪዎች እንዲሁም ከእምነቱ ተከታዮች የሚደርሰዉ የደስታ መግለጫ መልክት እንደቀጠለ ነዉ። ርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳቱ ከምርጫዉ በኋላ “ያለ ፍርኃት፣ በአንድነት ከእግዚአብሔርና እርስ በርሳችን እጅ ለእጅ በመያያዝ እንራመድ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።...more4minPlay
May 09, 2025«በዓለም ላይ ከ 5 አንዷ ሴት የወሲባዊ ጥቃት ሰለባ ናት»በህፃናት ልጆች ላይ የሚፈጸም ወሲባዊ ጥቃት የዓለም አቀፍ ችግር ነው። አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው በዓለም ላይ እድሜያቸው ለአካለ መጠን ያልደረሱ፤ ከሰባት ወንዶች አንዱ ፣ ከሴቶች ደግሞ ከአምስት ሴቶች አንዷ የወሲባዊ ጥቃት ሰለባ ይሆናሉ።...more10minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.