Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.
May 08, 2025አሜሪካዊው ካርዲናል ሮበርት ፕሪቮስት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተመረጡአሜሪካዊው ካርዲናል ሮበርት ፕሪቮስት በዓለም ዙሪያ 1.4 ቢሊዮን አማኞች ያሏት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተመረጡ። የ69 ዓመቱ ሮበርት ፕሬቮስት ለርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳትነታቸው ሊዎ 14ኛ የሚለውን ሥም ወስደዋል። ከቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ የመጀመሪያ መልዕክታቸው “ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን” የሚል ነበር።...more0minPlay
May 08, 2025በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የሚያስፈትኑ 470 ትምህርት ቤቶች ብቻ ናቸውበአማራ ክልል ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች ከስራ ውጪ በመሆን በተማሪዎች የመማር ሂደት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲፈጠር ቆይቷል፡፡ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በአማራ ክልል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ደግሞ በድጋሜ በተማሪዎችና በትምህርት ቤቶች ላይ ጫናው መቀጠሉን መርጃዎች ያሳያሉ፡፡...more4minPlay
May 08, 2025በአዉሮጳ ሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ያበቃበት 80ኛ ዓመት«በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ ንግግር እንዳደርግ ስጋበዝ በ 19 ኛዉ መቶ ክፍለዘመን ኢትዮጵያ ለጀርመን እርዳታ ሰጭ የነበረችበት ጊዜ እንደነበር ታዉቁ ነበር ወይ እያልኩ እቀልዳለሁ፤ እጠይቃለሁ። ይህ የሆነዉ ሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ ነዉ። ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያዉያኖች በዚህ ሁኔታችን መኩራት ይገባናል።» ልዑል አስፋ ወሰን አስራተ...more14minPlay
May 08, 2025የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት፤ የUSAID መዘጋት፣ የምርጫ ቦርድና ህወሓት፣ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄዘገቦች እንደሚጠቁሙት USID እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር ከ2020 ወዲሕ ብቻ ለኢትዮጵያ የ3.6 ቢሊዮን ዶላር ሰብአዊ ርዳታ ሰጥቷል።በግጭትና በተፈጥሮ አደጋዎች ለተጎዱ ሰዎችና ተቋማት መርጃ በ2022 (እጎአ)ብቻ ለኢትዮጵያ የሰጠዉ ድጋፍ ከ1.9 ቢሊዮን ዶላር ይበልጣል-እንደ ዘገቦቹ...more9minPlay
May 08, 2025የፍራንኮ ጀርመን ዲፕሎማሲ በአዲስ ምዕራፍፈረንሳይ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጠናቀቀበትን የውሮጳ የድል ቀን ዛሬ አስባ ዋለች። ከምርጫ በኋላ በመጀመሪያው የአውሮጳ ጉዟቸው ትናንት ረቡዕ ወደ ፓሪስ ያቀኑት የጀርመኑ መራሔ መንግስት ፍሬድሪክ ሜርስ አውሮጳ ትልቅ ስጋት እንደተደቀነባት ተናግረዋል።...more4minPlay
May 08, 2025አቶ ታዬ ደንደአ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ያቀረቡት ክስየሰላም ሚኒስትር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ምክር ቤት አባል የነበሩ አቶ ታዬ ደንደዓ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ስያገለግሉ የነበረውን ገዢውን የብልጽግና ፓርቲ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰሱ፡፡ አቶ ታዬ ለቦርዱ ያስገቡት ደብዳቤ ፓርቲው በቅርቡ ያካሄደውን ሁለተኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የህጋዊነት ጥያቄ በማንሳት እልባቱን የሚጠይቅ ነው፡፡...more4minPlay
May 08, 2025በአማራ ክልል የዘፈቀደ እሥር መቀጠሉን ኢሰመኮ ገለፀበአማራ ክልል ለአሥር ወራት ተደንግጎ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግንቦት 2016 ዓ.ም ያበቃ ቢሆንም የዘፈቀደ እሥር መቀጠሉን ኢሰመኮ አስታወቀ። የአፍሪካ ሰብአዊ እና ሰዎች መብቶች ኮሚሽን ጉባኤ ላይ አጭር ማብራሪያ የሰጡት የኮሚሽኑ የሲቪል ፖለቲካ እና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶክተር አብዲ ጅብሪል ናቸው።...more4minPlay
May 07, 2025የፓሪስ ሳን ዠርማ እና የአርሰናል የሻምፕዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታየአውሮጳ ሻምፕዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ፓሪስ ውስጥ ይካሄዳል። ትናንት በነበረው ተመሳሳይ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ የጣሊያኑ ኢንተር ሚላን የስፔኑ ባርሴሎናን አራት ለሦስት አሸንፎ ለፍፃሜ በቅቷል። የዛሬው ግጥሚያ አሸናፊ ከኢንተር ሚላን ጋር ለዋንጫ ይጫወታል።...more0minPlay
May 07, 2025የጤና ባለሙያዎች የመጨረሻ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻና የስራ ማቆም አድማ ማስጠንቀቂያየትናንቱ የሀኪሞቹ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ ለአንድ ወር የተቀመጠው የማስጠንቀቂያ ጊዜ የመጨረሻ ምዕራፍ መሆኑን አስረድተው አስተያየታቸውን የሰጡን አንድ እንቅስቃሴውን የሚመሩት ሀኪም፣በሚቀጥሉት7 ቀናት የጤና ባለሙያዎች ተገቢ ያሉትን ምላሽ ከሚመለከተው አካል ካላገኙ በማህበራዊ ሚዲያ እንዳስቀመጡት የስራ አድማ ሊመቱ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፡፡...more4minPlay
May 07, 2025መቀመጫውን ካይሮ ያደረገው አዲሱ የአፍሪቃ የህዋ ኤጀንሲበጎርጎሪያኑ 2016 ዓ/ም የአፍሪቃ ህብረት፤የአህጉሪቱን የህዋ ሳይንስ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ የነደፈ ቢሆንም፤እንደ ሌሎቹ አህጉሮች የህዋ ሳይንስ ኤጀንሲ በአፍሪቃ ደረጃ ለማቋቋም ግን ሳይችል ቆይቷል። በቅርቡ ግን ለበርካታ አመታት ሲደረግ የነበረው ጥረት ሰምሮ፤ በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ የአፍሪቃ የህዋ ኤጀንሲ በይፋ ተመርቋል።...more13minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.