Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.
May 07, 2025የጊምቢ ወረዳ መምህራን ቅሬታስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ መምህር በወረዳው በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ 150 የሚደርሱ መምህራን የደረጃ ዕድገት ክፍያውን ለአራት ወራት እንዳላገኙ አመልክተዋል፡፡ የጊምቢ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በመምህራን ቅሬታ ላይ በሰጠን ማብራሪያ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ከፍያው ሳይሰጣቸው መቆየቱን አረጋግጠዋል፡፡...more4minPlay
May 07, 2025የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና ክልሎች የሚሰበስቡት ግብር በሚያዝያ ወር “ከትሪሊዮን ብር ይሻገራል”የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ እስከ ሚያዝያ 2017 ፌድራል መንግሥትና ክልሎች ከታክስ የሰበሰቡት ገቢ ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን ተናግረዋል። ከዚህ ውስጥ ፌድራል መንግሥት 720 ቢሊዮን ብር ሰብስቧል። የታክስ ገቢ ከ2016 ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር በ279 ቢሊዮን ብር ቢልቅም ወይዘሮ ዓይናለም በቂ ነው የሚል ዕምነት የላቸውም።...more10minPlay
May 07, 2025በጀርመን መራኄ መንግስት ፍሪድሪሽ ሜርስ ሹመት የታየው ድንጋጤና እፎይታበሜርስ ሹመት የፈርንሳዩ ፕሪዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ በአውርጳ አጀንዳዎች የጀርመንና ፈረንሳይ ሽርክና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት በመግለጽ የደስት መልእክታቸውን ሲያስተላለፉ፤ የአውሮፓን በተለይም የጅርመንን ድጋፍ በዕጅጉ የሚሹት የዩክሬኑ ዘለንስኪም በሜርዝ ሹመት እፎይታ እንዳገኙና እንደተደሰቱም ቀድመው አስታውቀዋል።፡...more5minPlay
May 06, 202510ኛው የጀርመን መራኄ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ10ኛው የጀርመን መራኄ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ በአንድም የጀርመን ፌደራል ግዛት ሚኒስትር አለያም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አላገለገሉም። የአንዲት አነስተኛ የጀርመን ከተማ ከንቲባም አልነበሩም። ሜርስ ከኮንራድ አደናወር ቀጥሎ ለዚህ ሥልጣን የበቁ በእድሜ ትልቁ ፖለቲከኛ መሆናቸውም ከቀደሙት መራኄ መንግሥታት የተለዩ ያደርጋቸዋል ።...more10minPlay
May 06, 2025ለትግራይ ተፈናቃዮችና ችግረኞች የሚሰጠዉ ርዳታ ማነስ ያስከተለዉ ሥጋትየትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ቁጥራዊ መረጃ እንደሚያመለክቱት በክልል ተፈናቃዮች ጨምሮ 2 ነጥብ 4 ሚልዮን ህዝብ አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ ይፈልጋል። ይህ ባለፉት ዓመት ከነበረው የእርዳታ ፈላጊ ህዝብ መጠን በተወሰነ መልኩ መቀነስ ቢታይበትም አሁንም በክልሉ ያለ ሰብአዊ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑ ማሳያ መሆኑ ይገለፃል።...more4minPlay
May 06, 2025የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ድጋፍ መቆም፣ ቀጣዩ ጠቅላላ ምርጫ እንዲሁም የሲቪክ ድርጅቶች ሚናየአሜሪካ የተራድዖ ድርጅት (USAID) ባለፈው የግሪጎርያን 2024 ብቻ ለኢትዮጵያ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጎ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። ሀገር በቀል ሲቪል ድርጅቶች በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና እና በሌሎች መስኮች ከሚያከናውኗቸው የልማት ተግባራት አብዛኛዎቹ ከዚሁ ድርጅት በሚገኝ የሀብት ምንጭ የሚሠሩ ስለመሆኑ ይነገራል።...more4minPlay
May 06, 2025የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት አርዳታ መቋረጥ በጤና አገልግሎት ላይ ያስከተለዉ ተጽእኖእናቶች በእርግዝና ወቅት የቅድመ ወሊድ እና ድህረ ወሊድ ክትትላቸው በርካታ ቦታዎች ላይ አሁንም አሳሳቢ በመሆኑ ሰፊ የግንዛቤ ስራዎች እንደሚያስፈልግ የገለጹት ባለሙያው በተጠቀሱት አከባቢዎች ለአንድ ዓመት ግድም በተሰራው ስራ ተስፋ ታይቶም እንደነበር አስረድተዋል፡፡ “እውነት ለመናገር ፕሮጀክቱ ጥሩ ውጤቶችን አምጥቷል...more4minPlay
May 06, 2025የጀርመን ወግ አጥባቂ ፖለቲከኛ ፍሬድሪሽ ሜርስ መራሔ መንግስት ሆነዉ ተመረጡየጀርመን ምክር ቤት (Bundestag) ሜርስን ለመራሔ መንግስትነት የመረጠዉ ለሁለተኛ ጊዜ በሰጠዉ ድምፅ ነዉ።ምክር ቤቱ ዛሬ ማርፈጃዉ ላይ ባደረገዉ ምርጫ ሜርስ ያገኙት 310 ድምፅ ለመራሔ መንግስትነት ለመመረጥ የሚያበቃቸዉ አልነበረም...more5minPlay
May 06, 2025ፍሪድሬሽ ሜርስ የጀርመን መራኄ መንግሥት ሆኑፍሪድሬሽ ሜርስ በሁለተኛ ዙር ምርጫ የጀርመን መራኄ መንግሥት ሁነው ተመረጡ ። የጀርመን የሕዝብ እንደራሴዎች ዛሬ ጠዋት በሰጡት ድምፅ 6 የምክርቤት አባላት ድምፅ የጎደላቸው ፍሬድሪሽ በ325 ድምፅ ተመርጠዋል ። መራኄ መንግሥት ለመሆን የሚያስፈልገው 316 ድምፅ ነበር ።...more0minPlay
May 06, 2025በጀርመን መራኄ መንግስትነት ይመርጣሉ ተብለው የሚጠበቁት ፍሪድሬሽ ሜርስ በመጀመሪያው ዙር ምርጫ አብላጫ ድምፅ ሳያገኙ ቀሩ።የጀርመን የሕዝብ እንደራሴዎች ዛሬ ጠዋት በሰጡት ድምፅ ፍሪድሬሽ ሜርስ መራኄ መንግሥት ይሁኑ ሲሉ የመረጡት 310 ብቻ በመሆናቸው ሜርስ መራኄ መንግስት ለመሆን የሚያስፈልጋቸው 6 የምክርቤት አባላት ድምፅ ጎድሏቸዋል ። በዚህም ምክንያት የምክር ቤቱ ስብሰባ ሰዓት ተቋርጧል ። የዜና ምንጮች ዛሬ ሁለተኛ ድምፅ አሰጣጥ አይኖርም ሲሉ ዘግበዋል ።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.