Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.
May 03, 2025የዩክሬን ፕሬዚደንት ዐይኖች ወደ አፍሪቃ አማትረዋልየዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜለንስኪ ዐይኖች ወደ አፍሪቃ ማማተር ጀምረዋል ። ፕሬዚደንቱ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሚያዝያ 16 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ደቡብ አፍሪቃን በመጎብኘት አዲስ ምእራፍ አስጀምረዋል ።...more6minPlay
May 03, 2025በደቡብ ሱዳናውያን መካከል በተከሰተ ግጭት ኢትዮጵያኑ ጉዳት ደረሰባቸውየሱዳን ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ተቃዋሚ (SPLM in Oppsition) የተባለው የደቡብ ሱዳን አማፂ ኃይልና የደቡብ ሱዳን የመንግስት ወታደሮች ኢትዮጵና ደቡብ ሱዳን በሚዋሰኑበት የጋምቤላ ክልል ላሬ ወረዳ ባለፈው ረቡዕ ባካሄዱት ጦርነት የላሬ ወረዳ ወና አስተዳዳሪ አቶ ቶክ ሞንግ መቁሰላቸውን ህክማና ጣቢያ ሆነው ለዶይቼ ቬሌ ተናገሩ...more4minPlay
May 03, 2025ስሞታ የቀረበበት ሀገራዊው የውትድርና ምልመላ እና የመከላከያ ሰራዊት ምላሽበኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተለያዩ አከባቢዎች እየተከናወኑ ነው በተባሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ምልመላ ከፍላጎት ውጪ እየተከናወነ መሆኑን የአይን ምስክሮች ተናግረዋል። መከላከያ ሰራዊት ግን ግን የመመልመያ መሥፈርቶች መሠረት በማድረግ ብቻ ወታደሮችን እየመለመለ መሆኑን በመግለጽ የቀረበበትን ክስ አጣጥሏል።...more4minPlay
May 03, 2025በኢትዮጵያ “በቅርቡ የተገኙ የፕሬስ ነጻነት አብዛኞቹ ውጤቶች ተቀልብሰዋል” ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድንበ2018 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ሲይዙ ኢትዮጵያ በድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የፕሬስ ነጻነት ኢንዴክስ 150ኛ ነበረች። በዓመቱ 110ኛ፣ በ2020 ደግሞ 99ኛ ደረጃን በመያዝ መሻሻል አሳይታ ነበር። ዘንድሮ ከ180 ሀገራት 145ኛ ደረጃ ያስቀመጣት ድርጅቱ “በቅርቡ የተገኙ የፕሬስ ነጻነት አብዛኞቹ ውጤቶች ተቀልብሰዋል” ብሏል።...more0minPlay
May 02, 2025የአብን መግለጫ፣ የኤርትራ ተቃዉሞና የፖለቲካ ተንታኝ አስተያየት“በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ቡድኖች በኤርትራ ላይ እያራመዱት ያለው ሉዓላዊት ሀገር የመቆጣጠር ፍላጎት ሊታሰብበት ይገባል” ሲል የኤርትራ መንግሥት ጠይቋል፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፣ “ኤርትራ ሀገር ሆና የተመሰረተችበት ሂደት ቅቡልነት ላይ ጥያቄ አለኝ” ብሏል...more4minPlay
May 02, 2025የውጭ ዜጎችን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት የሚያደርገው ረቂቅ ሕግ ተስፋ እና ሥጋትየሚኒስትሮች ምክር ቤት "የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ የሚሆኑበትን" ውሳኔ አሳልፎ፣ ረቂቅ አዋጅን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቶቷል። "የዜጎችን የመሬት ይዞታ የማግኘትና የመጠቀም መብት በማያጣብብ መልኩ" ይተገበራል የተባለው ይህ የመንግሥት ውሳኔ በአወንታም፣ በሥጋትም ሀሳብ እየተሰጠበት ነው።...more4minPlay
May 02, 2025የትግራይ ሲቢል ማሕበራት ሕብረት የክልሉን ጊዚያዊ አስተዳደር ወቀሰየትግራይ ሲቪል ማሕበረሰብ ሕብረት በክልሉ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ እየከፋ፣ የህዝብ አንድነት እየተከፋፈለ፣ ወደ አደገኛ ሁኔታ እያመራ ነው የለ ሲሆን፥ ይህ ለመፍታት ሊያግዝ ይችል የነበረው በቅርቡ ዳግም ወደስራ የገባው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ደግሞ ሁሉም አካላት ያካተተ ተደርጎ ሊዋቀር ሲገባ፥ ከዚህ በተቃራኒ የሆነ መንገድ መከተሉ አመልክቷል።...more3minPlay
May 02, 2025ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን «ጥቃትና ግፍ እየደረሰባቸዉ ነዉ» ድርጅቶችለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይገለጽና ድምፃቸው እንዲቀየር የጠየቁት እነዚህ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፣ በቅርቡ አንደኛው ልጃቸው ትከሻውን በጥይት ተመትቶ እስካሁን ተገቢውን ህክምናም ሆነ ማስታገሻ መድኃኒት ባለማግኘቱ ምክንያት በከፍተኛ ስቃይ ላይ እንደሚገኝ ይናገራሉ።...more4minPlay
May 02, 2025የተለያዩ ማሽኖችን ሀገር ውስጥ በሚገኙ ቁሳቁስ የሚሰሩት ወጣቶች በደሴከዉጭ ሀገራት በከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ የሚገብ የተለያዮ ማሽነሪዎችን ሀገር ዉስጥ በሚገኙ ቁሳቁስ በመስራት ለበርካቶች የእዉቀት ሽግግር እያደረጉ ያሉት የጋቢ ቤተሰቦች በደሴበተለይም ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚዉጡ ተማሪዎች አዳዲስ የፈጠራ ስራ መስራት የሚችሉበትን እድል በማመቻቸት እራሳቸዉን እንዲያሳዮ እድል ይፈጥራሉ...more9minPlay
May 02, 2025የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሪደር ልማት “እያደረሰ ያለው ጉዳት እጅግ ከባድ ነው” የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተመራማሪ ሐይማኖት አሸናፊየአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኮሪደር ልማት የሚከናወነው “ነዋሪዎች ፈቃደኛ ሆነው፣ ልማቱ ገብቷቸው” እንደሆነ ገልጸዋል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተመራማሪ ግን “የመንግሥት አካላት እንደሚያቃልሉት በጣም ጥቂት የሚባል ሕብረተሰብ አይደለም እየተጎዳ የሚገኘው” ሲሉ ይናገራሉ። ሐይማኖት አሸናፊ የዶይቼ ቬለ የአንድ ለአንድ እንግዳ ናቸው...more17minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.