Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.
May 05, 2025በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ሕጋዊ ሰውነቱ እንዲመለስለት የጠየቀዉ ህወሓትህወሓት በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እና እግድ ሊያበቃ ጥቂት ቀናት በቀሩበት፥ የፓርቲው ሕጋዊ ሰውነት በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት እንዲመለስለት ጠየቀ። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ህወሓት ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለሶስት ወር ማገዱ፣ በሶስት ወር ማስተካከያ የማያደርግ ከሆነ በቀጥታ እንደሚሰረዝ አስታውቆ ነበረ።...more4minPlay
May 05, 2025የሚያዝያ 27 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባየፕሬሚየር ሊጉን ዋንጫ መውሰዱን ገና አራት ጨዋታዎች እየቀረው አረጋግጦ የነበረው ሊቨርፑል ትናንት በቸልሲ ብርቱ ሽንፈት ገጥሞታል ። በጀርመን ቡንደስሊጋ ቅዳሜ ዕለት ከኤርቤ ላይፕትሲሽ ጋር ሦስት እኩል የተለያየው ባዬርን ሙይንሽን ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩት ዋንጫውን መውሰዱን አረጋግጧል ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለድል በቅተዋል ።...more10minPlay
May 05, 2025ማሕደረ ዜና፣ የፕሬዝደንት ትራምፕ ሠላም የማስፈን ቃልና ተቃራኒ ርምጃየንግዱ ማትረፍ-መክሰር ዉጣ ዉረድ፣ የመሸጥ-መለወጡ ክርክር፣ ሐብት የማከማቸቱ ብልጠት ለፖለቲካዉ ድል፣ ለሚገቡት ቃል መከበር-መጣስ መሠረት መሆኑ አላከራከረም።የትራምፕ ደጋፊዎች ደጋግመዉ እንደሚሉት ሰዉዬዉ በንግድ፣ ድለላ፣ በየፍርድ ቤቱ እሰጥ አገባ ያዳበሩት ክርክርና ድርድር የዓለምን ዉጥንቅጥ መልክ ለማስያዝ ይጠቅማቸዋል ነበር-ተስፋዉ።...more14minPlay
May 05, 2025በትራምፕ አስተዳደር መብት የተነፈጉት የአሜሪካ ድምፅና ሌሎች የዓለምአቀፍ ሚዲያ ተቋማትከሁለት ሳምንት በፊት የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ፍርድ ቤት በትራምፕ አስተዳደር ከስርጭት የታገዱት የአሜሪካ ድምፅ እና ሌሎች የዓለምአቀፍ ሚዲያ ተቋማት ከእገዳው በፊት ወደነበሩበት ቁመና እንዲመለሱ፤ አስተዳደራዊ ዕረፍት የተሰጣቸው ቋሚና የኮንትራት ሠራተኞች የፍርድ ሂደቱ እየቀጠለ ቢሆንም ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ተወስኖ ነበር።...more5minPlay
May 05, 2025የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት እርዳታ መቋረጥና ተፅዕኖውከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ርዳታ መቋረጥ ጋር ተያየዞ በአማራ ክልል በተፈናቃዮችና ሌሎች እርዳታ በሚፈልጉ ወገኖች ላይ ችግር እየገጠማቸው እንደሆነ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተናገሩ ነው፣ መነግስት በበኩሉ ሊመጣ የሚችለውን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ ለመቋቋም እየሰራ እንደሆነ ገልጧል፡፡...more4minPlay
May 05, 202584ኛው የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች የድል በዓል84ኛው የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች የድል በዓል ዛሬ ሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተከብሯል። የፋሽስት ጣልያን መንግሥት ኢትዮጵያን ዳግም የወረረበትና ከአምስት ዓመታት የአርበኞች ተጋድሎ በኃላ ተሸንፎ የወጣበት ይህ ዕለት፣ በወራሪው ኃይል ወርዶ የነበረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ዳግም በክብር የተሰቀለበት ነው።...more4minPlay
May 04, 2025እንወያይ፤ አሳሳቢው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ መራቅበግጭቶችና በሌሎች ምክንያቶች በመላ አገሪቱ 8 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ መሆናቸውን የትምህርት ሚንስቴር በተለያዩ መድረኮች ገልጿል።ለመሆኑ የተማሪዎች በዚህ ልክ ከትምህርት ገበታ መራቅ የሚያስከትለው ጉዳት ምን ይመስላል? ለወደፊቱስ በግለሰብ ፣በኅብረተሰብ እና በሀገሪቱ የሚያመጣው ሁለንተናዊ ችግርስ ? ምንስ መደረግ አለበት?...more45minPlay
May 04, 2025የፕራግ ማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያዉያን አሸነፉበቼክ ሪፑብሊክ ዋና ከተማ ፕራግ ዛሬ የተካሄደውን የወንዶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሚ ብርሃኑ አሸነፈ። ለሚ ለሁለት ተከታታይ አመታት የፕራግ ውድድርን በማሸነፍ እስካሁን በፕራግ በተካሄዱ 30 ውድድሮች ክብረ ወሰኑን ያስጠበቀ የመጀመሪያው አትሌት ለመሆንም በቅቷል።...more0minPlay
May 03, 2025የዓለም የፕሬስ ነጻነት ሲዘከር የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ምኅዳርበመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ላይ የሚደርሱ ጫናዎች እና የተሻሻለው የመገናኛ ብዙኃን ሕግ የሚዲያ ምኅዳሩን "ከፉኛ ይጎዱታል" ሲል የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ገለፀ። የመብት ተሟጋች ድርጅቱ የፕሬስ ነጻነት ቀንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የመንግሥት አካላት "ነጻና ገለልተኛ የመገናኛ ብዙኃን እንድኖር ጥበቃና ድጋፍ እንድያደርጉ" ጠይቋል።...more4minPlay
May 03, 2025የዶናልድ ትራምፕ ዲፕሎማሲ በአፍሪቃየዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከአፍሪቃ አኅጉር ጋር ያላቸው ግንኙነት ላይ ቀይ መስመር ማስመር የሚፈልጉ ይመስላል ። አገራቸው የበጀት ቅነሳ መርኅ መሠረት ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በመላው ዓለም 30 ግድም ኤምባሲዎችን እና ቆንስላዎችን መዝጋት ይፈልጋሉ ። አብዛኞቹ ከአፍሪቃ ናቸው ።...more5minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.