Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.
April 15, 2025ጤናና አካባቢ፤ የኮሌራ ስርጭትየአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋም ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ በሽታው ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በአማራ ክልል 3 ወረዳዎች መከሰቱንና ከ1ሺህ 400 በላይ ሠዎች በበሽታው መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡...more11minPlay
April 14, 2025ማሕደረ ዜና፣ የኢራን-አሜሪካ ድርድር ጠብ-ግጭቱን ያበርድ ይሆን?የሙጃህዲያን ኢ-ኻሊቅ (MEK)ና የቡድኑ ምክር ቤት መሪዎች ኢራን በ1967 ከአሜሪካ ባገኘችዉ ድጋፍ የጀመረችዉን የኑክሌር መርሐ ግብርን ወደ ኑክሌር ቦምብ መስሪያነት ለመቀየር ናታንዝና አራክ ዉስጥ በድብቅ እያብላላች መሆኑን ለዓለም አረዱ።ወይም አበሰሩ።ነሐሴ 2003፤ ዋሽግተን።...more0minPlay
April 14, 2025የህወሓት ሊቀ-መንበር በፕሪቶሪያ ግጭት የማቆም ሥምምነት ላይ በአፋጣኝ ውይይት እንዲደረግ ጠየቁየህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በፕሪቶሪያ በተፈረመው ግጭት የማቆም ሥምምነት ላይ የአፍሪካ ኅብረት አሸማጋዮች በአፋጣኝ ተሰብስበው እንዲወያዩ ጥሪ አቀረቡ። በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስቱ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እየጣሰ በተናጠል አዋጆች፣ ደንቦች እና መመርያዎች እያወጣ ይገኛል ሲል ወቅሷል።...more4minPlay
April 13, 2025ያለፉት ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያ ጉዞከትግራዩ ጦርነት በኋላ አልቀጠለም እንጂ በዐቢይ የመጀመሪያው የስልጣን ዘመን ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ሰላም አውርዳም ነበር። ሰባቱ ዓመታት ኢትዮጵያ በየዘርፉ ብዙ ለውጦች ያስመዘገበችባቸው ዓመታት ናቸው ሲሉ የሚያወድሱ እንዳሉ ሁሉ፣ በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማታወቅ ሰብዓዊ እልቂትና የመብት ጥሰቶች የደረሰበት ጊዜ ነው ሲሉ የሚኮንኑም አሉ።...more40minPlay
April 13, 2025ሩሲያ በሰሜናዊ ዩክሬን ሱሚ የተባለች ከተማ ላይ በባልስቲክ ሚሳይል በፈጸመችው ጥቃት ሁለት ሕጻናትን ጨምሮ በትንሹ 31 ሰዎች ተገደሉሩሲያ በሰሜናዊ ዩክሬን በምትገኘው ሱሚ የተባለች ከተማ ላይ በባልስቲክ ሚሳይል ዛሬ እሁድ ጠዋት በፈጸመችው ጥቃት በትንሹ 31 ሰዎች መገደላቸውን ዩክሬን አስታወቀች። ከሟቾቹ መካከል ሁለት ሕጻናት ይገኙበታል። አስር ሕጻናትን ጨምሮ ሌሎች 84 ሰዎች በጥቃቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው ዩክሬን ገልጻለች።...more0minPlay
April 12, 2025አዲሱ የትራምፕ የቀረጥ ጭማሪና የአፍሪቃ ሃገራትለሁለተኛ ጊዜ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መንግሥታዊ ሥልጣን የመጡት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መላውን ዓለም ውዝግብ ውስጥ የከተተ ከፍተኛ የቀረጥ ጭማሪ ይፋ ካደረጉ ሳምንት አለፈ።...more6minPlay
April 11, 2025ወደየቀያቸዉ የተመለሱ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የገጠማቸዉ ፈተናየኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮምሽን የትግራዩ ጦርነት ተከትሎ የተፈናቀሉ ዜጎች ሁኔታ ሲከታተል መቆየቱ የሚገልፅ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ወደ ቀድሞ ቀዬአቸው እንዲመለሱ የተደረጉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብት አያያዝ ሁኔታ በትግራይ ሰሜን ምዕራብ እና ደቡባዊ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የሸፈነ ክትትል ማድረጉ አመልክቷል።...more5minPlay
April 11, 2025በአማራ ክልል የሚደረገዉ ግጭት በጤና ባለሙያዎች ስራ ላይ ያደረሰዉ ጫናሁለት አመት ሊሞላዉ ጥቂት ጊዚያት የሚቀሩት የአማራ ክልል ግጭት ዉስጥ መድኃኒቶች በመንገድ ላይ መዘረፍ የበጀት እጥረትና ትራንስፖርት አለመኖር ለጤና ባለሙያዉ የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ፈተና መሆኑ ይገለፃል የአማራ ክልል የጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት አቶ ሻምበል ፈንታየ አስታዉቀዋል።...more4minPlay
April 10, 2025ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎቷን ትገፋበታለች ተባለየኢትዮጵያ መንግሥት ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የሀገሪቱን የባሕር በር የማግኘት መብት ለማሳካት መንግሥት ዲፕሎማሲያዊ፣ ሕጋዊ እና ሰላማዊ መንገዶች መከተሉን እንደሚገፋበት አሳወቀ። የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት መሻከር ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን የመጠቀም ዕድሏን እንዳጠበበው አንድ የኤኮኖሚ ባለሞያ ተናግረዋል።...more4minPlay
April 08, 2025ምዕራብ ኦሮሚያ በጃርዳጋ ጃርቴ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት የ10 ሰዎች ተገደሉከጃርዳጋ ጃርቴ ወረዳ አስተያየታቸውን የሰጡን ሌላው ነዋሪም በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈው ነዋሪዎች ስርዓተ ቀብራቸው በትናንትናው እለት በአንድ ቦታ መፈጸሙን ገልጸው በጥቃቱ ህይወታቸው ያልፈው በብዛት ተማሪዎች እንደሆኑ አስታውቀዋል...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.