Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.
April 07, 2025ወደ ትምህርት ገበታ ያልተመለሱት 1.2 ሚልዮን የትግራይ ሕጻናት እና አዳጊዎችበትግራይ 1.2 ሚልዮን ሕጻናት እና አዳጊዎች ወደ ትምህርት ገበታ አለመመለሳቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። በትግራይ ከጦርነቱ በኋላ ጭምር የቀጠሉት ሰብአዊ፣ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንዲሁም መፍትሔ ያላገኘው የተፈናቃዮች ጉዳይ አሁንም በትግራይ ሚልዮኖች ከትምህርት እንዲርቁ ማድረጉ ተገልጿል።...more3minPlay
April 07, 2025በመንግሥት እና በፋኖ መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት የአማራ ክልል ንግድን ማቀዛቀዙበአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ ጦርነት ምክንያት የንግድ ስራዉ መቀዛቀዙ ተገለፀ። ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ የመንገድ መዘጋት ዝርፊያና የማህበረሰቡ የመሸመት አቅም ዉስንነት ነጋዴዎችን ከንግድ ስራ እያስወጣ መሆኑም ተነግሯል። የንግዱ መቀዛቀዝ የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ተፅኖ ይኖረዋል ተብሏል።...more4minPlay
April 07, 2025የጅቡቲ የኢኮኖሚ እና የቱሪዝም ማዕከል የመሆን ጥረትበአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በጅዖ ፖለቲካ እና በንግድ መስመርነት ቁልፍ እና ስልታዊ ጠቀሜታ ያላት ትንሿ ሀገር ጅቡቲ፤ በአሕጉሩ በጎ ምጣኔ ሐብታዊ ትስስር ለመፍጠር ያስችላል ያለችውን ሁለተኛውን ዙር ዓመታዊ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ዛሬ ማካሄድ ጀምራለች። ጅቡቲ በአፍሪካ ቀንድ የቱሪዝም እና የሰላም ማዕከል ለማድረግ ጥረት እያደረገች ነው።...more4minPlay
April 07, 2025ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የኢራን ፍጥጫ-የመካከለኛዉ ምሥራቅ ምሥቅልቅል ሌላ ገፅታየቴሕራን የፖለቲካና የጦር ሹማምንት ደግሞ ለፕሬዝደንት ትራምፕ ዛቻ አፀፋ ዛቻ እየሰነዘሩ ነዉ።የአያቶላሕ ዓሊ ኻማኒይ የቅርብ አማካሪ አሊ ላርጃኒ ባለፈዉ ሳምንት እንዳሉት ኢራን የኑክሌር ቦምብ መታጠቅ አትፈልግም።የአሜሪካኖች ዛቻ ከበረታ ግን ቀጠሉ የቀድሞዉ የኢራን የኑክሌር ጉዳይ ተደራዳሪ «ሌላ ምርጫ የለንም---መታጠቅ እንጂ።»...more14minPlay
April 06, 2025የዶይቼ ቬለ አማርኛ የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓልን በማስመልከት ሉድገር ሻዶምስኪ ያስተላለፉት መልዕክትየዶይቼ ቬለ የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን ሲያከብር ኃላፊው ሉድገር ሻዶምስኪ “በሐሰተኛ መረጃ በተጥለቀለቅንበት ባሁኑ ጊዜ ሐቅ ላይ ብቻ በመመርኮዝ እንዘግባለን” ሲሉ ቃል ገብተዋል። ኃላፊው “በፖለቲካ፣ በጎሳም ይሁን በሐይማኖት ንቅናቄዎች እና ዝንባሌዎች ወደ የትኛውም አንወግንም” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።...more5minPlay
April 06, 2025የዶቼ ቬለ ነባር አድማጮች ፣ተሳታፊዎችና በተለያየ ሞያ የተሰማሩ ተከታታዮች አስተያየትሊቀ ካህናት ዶክተር መርአዊ ተበጀ፣ መቶ አለቃ ዉቤ ታሪኩ፣ ጥቁር አሚን፣ ዓለማየሁ መላከ፣ መሐመድ ሐሰን ፤ ለረጅም ጊዜ የዶቸ ቬለን ስርጭት ከሚከታተሉ፣ከሚሳተፉና አስተያየት ከሚሰጡት መካከል ይገኙበታል። የነዚህናና ከተለያዩ ቦታዎች በልዩ ልዩ ሙያ ውስጥ የተሰማሩ አድማጮችም አስተያየቶችንም አሰባስበናል።...more0minPlay
April 06, 2025የዶይቸቬለ ዋናው ስቱዲዮ የቀን ተቀን አሠራርን በጥቂቱ እናስቃኛችሁዶይቸ ቬለ የአማርኛው ክፍል ለስድሳ ዓመታት በፊት ከአመሻሹ 11 ሰአት ላይ፥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ከምሽቱ አንድ ሰአት ላይ ሥርጭቶቹን በቀጥታ ለአድማጮች ያደርሳል ። የየቀኑ የአንድ ሰአት ሥርጭቶቹን ወደ አድማጮቹ ከማድረሱ አስቀድሞ በርካታ ሒደቶችን ያሳልፋል ። የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴው ምን ይመስላል?...more5minPlay
April 05, 2025በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በብሔራዊ ምክክር እንዲሳተፉ ተጨማሪ ጥሪ ቀረበበአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በብሔራዊ ምክክር እንዲሳተፉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ ጥሪ አቀረቡ። ኮሚሽኑ በክልሉ የሚያካሒደው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ዛሬ ተጀምሯል። “አለመገናኘት እያጋደለን ነው” የሚሉ አንድ ተሳታፊ “ ከመማከር ሰላም አለ” ሲሉ ሒደቱ መፍትሔ ያመጣል የሚል ተስፋቸውን ገልጸዋል...more4minPlay
April 05, 2025ትኩረት በአፍሪቃ፣ የደቡብ ሱዳን ዉጥረት፣ የሩሲያ ጥቅም በሊቢያተቀናቃኞቹ ኃይላቸዉን ለማጠናከር፣ ሌላኛዉን ወገን ለማደከምና ለዉጊያ የሚያደርጉት ዝግጅት ቀጥሏል።የሳልቫ ኪር መንግስት የሱዳን ሕዝብ ነፃ አዉጪ ንቅናቄ -ተቃዋሚ (SPLM-IO) የሚባለዉ የማቻር የፖለቲካ ፓርቲ ያዘዉ የነበረዉን አንድ ክፍለ ጦር ከማቻር ፓርቲ ከድቶ ሳልቫ ኪር ከሚያዙት የደቡብ ሱዳን ጦር ጋር እንዲያብር አድርጓል።...more14minPlay
April 04, 2025የአንድ ለአንድ እንግዳ ወ/ሮ ራኬብ መሰለየአንድ ለአንድ እንግዳችን በተለይ የሕጻናት፤ የሴቶች እና የጾታ ሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅ ከፍተኛ ባለሙያ ናቸው። ወ/ሮ ራኬብ መሰለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሲሆኑ አሁንም የሥራ ጊዜያቸው እንዳላለቀ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።...more16minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.