Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.
March 14, 2025በኦሮሚያ እና ማዕከላዊ-ኢትዮጵያ ክልሎች አዋሳኝ ስጋት ያጫረው የታጣቂዎች እንቅስቃሴበኦሮሚያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች አዋሳኝ አከባቢ በሚገኘው የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ አይመለል ቀበሌ ከኦሮሚያ ክልል ወደ አከባቢ የተንቀሳቀሱ ሸማቂ ታጣቂዎች በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ገለፁ። ደጋግሟል ያሉት ይህ የታጣቂዎቹ ጥቃት መረጋጋት እየነሳቸው በመሆኑ መፍትሄ እንዲያገኝም ጠይቀዋል፡፡...more4minPlay
March 14, 2025በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ተነገረበአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከፀጥታ ችግር ጋር እና በተፈጥሯዊ በሆነ ድርቅ ምክንያት 1ሚልየን የሚደርሱ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸዉ የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። በዞኑ በታህሳስ ወር ተከስቶ የነበረዉ የምግብ እጥረት 10ሸህ የሚደርሱ ሰዎችን ለጉዳት ዳርጎ ነበር።...more5minPlay
March 06, 2025አራት ፓርቲዎች፣ ኦነግና ኦፌኮ በኦሮምያ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ያቀረቡትን ጥያቄ ተቃወሙየኦሮሚያ ክልል ጉዳይ ሌሎች ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎችንም ይመለከታል ያሉት የፖለቲካ ድርጅቶች፣ኦነግና ኦፌኮ በኦሮምያ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት የሚያራምዱትን አቋም ነቅፈው ተችተዋል። አካሄዱንም«ፍትሕ አልባ፣ ኢ- ሕገ መንግሥታዊ»ብለውታል። አዲስ አበባን የአንድ ክልል አድርጎ ማሰብ እና መጠየቅ "ከቀን ቅዠት" ተለይቶ አይታይም ብለዋል።...more4minPlay
March 06, 2025129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓል በአዉሮጳ በድምቀት ተከበረ«ዓድዋ የይቻላል መንፈስ አዋጅ ነዉ።» 129ኛው የዓድዋ ድል መታሰብያ አንድነትን ህብረት ብሎም ኢትዮጵያዊነትን በሚያጎላ መልኩ ለንደን ላይ በድምቀት ተከብራል። የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም በዉጭ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በተለይ አዉሮጳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የዓድዋ ድል የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ምልክት መሆኑን ያበሰሩበትም ነበር።...more0minPlay
March 05, 2025የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር ወለድ ምጣኔ ማሻሻያ ፊቱን ወደ ገበያ ተመን አዞረለዓመታት ለመንግሥት “ርካሽ” ብድር ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሠረታዊ የወለድ ምጣኔ ማሻሻያ ተግባራዊ ሲያደርግ ፊቱን ወደ ገበያ ተመን አዙሯል። ንግድ ባንክ ከዚህ ቀደም ከውጪ ምንዛሪ ግኝት ጋር በተያያዘ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ደንበኞቹ የሚያቀርባቸውን ጥቅማ ጥቅሞች በመተው ለወጪ ንግድ በሚያቀርበው ብድር የሚያስከፍለውን ወለድ አሳድጓል።...more11minPlay
March 05, 2025በትግራይ ክልል ድህነት፣ ሥራ አጥነትና የወጣቶች ስደት መበራከትበትግራይ ክልል ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው መዳከሙን ተከትሎ ድህነት፣ ሥራ አጥነት እና የወጣቶች ስደት መበራከቱ ተገለ ። ከጦርነት በኋላ ይጠበቅ የነበረ ዳግመ ግንባታ ይሁን የኢኮኖሚ ማነቃቅያ ሥራዎች በሚጠበቀው ሁኔታ የሉም ሲሉም የኢኮኖሚ ዘርፍ ምሁራን ይገልፃሉ ።...more4minPlay
March 03, 2025ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮ-ሶማሊያ ወዳጅነት ካንጀት ወይስ ካንገት?የአዲስ አበባና የሞቃዲሾ መሪዎች የጠባቸዉን መሰረታዊ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ማስወገዳቸዉን በይፋ ሳይናገሩ በወር እድሜ ለመወዳደስ፣ መተቃቀፍ መነፋፈቅ መድረሳቸዉ በርግጥ ብዙዎችን ጉድ አጃኢብ ማሰኘቱ አልቀረም።ማስታወቂያ ሚንስትር ዳዉድ አዌስ እንደሚሉት ግን ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሥምምነት ተሰርዟል።...more14minPlay
March 03, 2025የአሜሪካ የተራድዖ ድርጅት ድጋፍ መቆም በሲቪል ማሕበራት ላይ ያሳረፈው ጫናአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (UDAID) ድጋፍ በድንገት መቋረጥ በአብዛኞቹ ሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ሥራ ላይ ብርቱ ጫና ማድረሱ ተነገረ። የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት እንዳለው በጤና፣ በሰላምና በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ሲሰሩ የነበሩ የድርጅቱ ወኪሎች የፕሮጀክት ስረዛ ስለተደረገባቸው በሁሉም ክልሎች ተጎጂ ሆነዋል።...more4minPlay
March 01, 2025በስደት ህይወቱን በመቀየር ለሌሎችም የተረፈው ወጣት ኢትዮጵያዊበስደት ህይወት ለራሱም ሆነ ለሌሎች የስራ እድልን ፈጥሮ ወደ ሌላ የስኬት ምዕራፍ ስለማደግ የሚያማትረው ሙርቴሳ ፈይሶ ዓላማው በዚህም ለማብቃት አለመሆኑን ያስረዳል፡፡...more0minPlay
February 25, 2025«የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየቀነሱ ይሄዳሉ ብየ አምናለሁ»፦ አዲሱ የኢሰመኮ የበላይ ኃላፊኢትዮጵያ ውስጥ የጋራ የሚያስተሳስሩ እሴቶች እየተሸረሸሩ መምጣት ለሰብአዊ መብት ጥሰቶች ምክንያት ናቸው ሲሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ዋና ኮሚሽነር ተናገሩ ። ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ፦ መንግሥት ሕገ መንግሥቱን እና የፈረማቸውን ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ሊያከብር እና ሊያስከብር ይገባል ብለዋል ።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.