Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.
February 24, 2025ወግ አጥባቂው ፍሪድሪሽ ሜርስ ማናቸው?ሜርክል ቀደም ብለው በ2021 ከፖለቲካው ራሳቸውን እንደሚያገሉ ካሳወቁ በኋላ ወደ ፓርቲያቸው የተመለሱት ወግ አጥባቂው ሜርስ በሦስተኛው ሙከራቸው በጎርጎሮሳዊው 2022 የክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት ፓርቲ የ(CDU) መሪ ለመሆኑ በቁ። ከዛሬ 25 በፊት የጀርመን የስደት ፖሊሲ ሊያስከትል ስለሚችላቸው ተጽእኖዎች ቅሬታቸውን ያቀርቡም ነበር።...more11minPlay
February 23, 2025የጀርመን ምርጫ ዐበይት ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው?በጀርመን ምክር ቤታዊ ምርጫ በምረጡኝ ዘመቻ ፍልሰት እና ኢኮኖሚ ዋንኛ አጀንዳዎች ነበሩ። በተሰበሰበ የሕዝብ አስተያየት የክርስቲያን ዴሞክራቶች ኅብረት እና የክርስቲያን ሶሻል ኅብረት ይመራሉ። ፓርቲዎቹ እስካሁን ጀርመን በምትከተላቸው ፖሊሲዎች ረገድ ለውጥ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።...more7minPlay
February 21, 2025ተግዳሮት የገጠመው የዩክሬን ሰላም አስከባሪበአንድ ወገን ለዩክሬን የምታደርገውን ድጋፍ ለመቀነስ ወይም ጨርሳ ልታቆም እንደምትችል የምታስፈራራው፤ ዩናይትድ ስቴትስ ኪየቭ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ኔቶ አባል መሆን እንደማይፈቀድላት ይፋ አድርጋለች። በዚህም ምክንያት የአውሮጳ ሃገራት በጦርነት ለደቀቀችው ሀገር የጋራ የጸጥታ ኃይል ለማዋቀር እየተሯሯጡ ነው።...more4minPlay
February 20, 2025ዕድሜው በአንድ ዓመት የተራዘመው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተስፋ እና ሥጋትየኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን «የነፃነት፣ የመለየትና ሀገር የመመሥረት ጥያቄዎች» በአጀንዳነት ቢቀርቡለት እንደማያስተናግድ አስታወቀ። በምክር ቤት የሥራ ጊዜው ለአንድ ዓመት የተራዘመለት ኮሚሽን፤ ሥራውን የሚሠራው በሕገ መንግሥቱ ማዕቀፍ ውስጥ መሆኑን ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።...more4minPlay
February 18, 2025ውዝግብ ያጠላበት የህወሃት ምሥረታ 50ኛ ዓመት በዓልዛሬ ህወሓት የተመሰረተበት 50ኛ ዓመት ተከበረ። ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ «የትግራይ ሕዝብ ትጥቅ ትግል የተጀመረበት 50ኛ ዓመት» በማለት በትግርኛ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ሆኖም ከየካቲት 11 ዓላማዎች ውጭ በሆነ መልኩ ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በትጥቅ ትግል የመፍታት ፍላጎት አሁንም አለ ሲሉም ገልፀዋል።...more0minPlay
February 15, 2025የምርጫ ቦርድ በህወሓት ላይ የወሰደው እርምጃ እና የሰላም ስምምነቱየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህወሓት ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ፥ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ላይ አሉታዊ ጫና እንዳይፈጥር ስጋቶች አሉ። ያነጋገርናቸው ምሁራን የሰላም ስምምነቱ ፈራሚ አካላት ችግሮች በፖለቲካዊ ውይይት መፍታት አለባቸው ይላሉ።...more4minPlay
February 14, 2025አንድ - ለ - አንድ፤ ከዶክተር ራሔል ባፌ ጋርየኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ «ተቃዋሚ ፓርቲዎች አማራጭ ሀሳብ ከማቅረብ ይልቅ ከሳሽ ነበሩ» ሲሉ መውቀሳቸውን ዶር ራሔል ዘለፋና ከእውነት የራቀ ሲሉ በጥብቅ ተቃውመዋል። ፖለቲከኛዋ፣ «ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋ ነው ሀሳብ ያለው ብልጽግና ገዥው ፓርቲ ጋ ግን ባንኩም ታንኩም አለ፤ ስልጣኑም አለ የፈለጉትን ለማድረግ» ብለዋል...more14minPlay
February 11, 2025የምርጫ ዘመቻ በጀርመን፤ የሾልስና የሜርስ የቴሌቪዥን ክርክር ፣የህዝብ አስተያየትየጀርመን መራኄ መንግሥት እና የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ እጩ መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ እና የወግ አጥባቂዎቹ እህትማማች የክርስቲያን ዴሞክራትና የክርስቲያን ሶሻል ኅብረት ፓርቲዎች እጩ መራኄ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ በቴሌቪዥን ያካሄዱት ክርክር ከዳሰሳቸውጉዳዮች ውስጥ ፍልሰት ፣ ኤኮኖሚ የዩክሬን ጦርነት የትራምፕ እርምጃዎችና ዛቻዎች ይገኙበታል።...more11minPlay
February 11, 2025በአማራ ክልል መማር ያልቻሉ ልጃገረዶች እያገቡ ነዉአስትያየት ሰጪዎቹ እንደሚሉት በክልሉ ባለው የሠላም እጦት ምክንያት ብዙዎቹ ተማሪዎች ትምህርት በማቋረጥ የተለያዩ አማራጮችን እየወሰዱ ነው። አንዳንዶቹ ስደትን ሲመርጡ ሌሎች ደግሞ ትዳርን መርጠዋል።በምስራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ነዋሪ ለዶይቼቬሌ እንደገለጡት በርካታ ልጃገረዶች በትምህርት ተስፋ በመቁረጥ አማራጭ ያሉትን እርምጃ እየወሰዱ ነው።...more4minPlay
February 07, 2025በኮንጎ ቀውስ የምስራቅና ደቡባዊ አፍርቃ አገር መሪዎች ጉባኤየምስራቃዊና ደቡባዊ አፍሪቃ አገሮች መሪዎች በኮንጎ ሪፑብሊክ በተክሰተው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ለመምከር ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በታንዛኒያ ዳሬሰላም ከተማ ተሰብስበዋል። በሩዋንዳ ይደገፋል የሚባለው አማጺ ቡድን በምስራቃዊው ኮንጎ በክፈተው ወታደራዊ ጥቃት በሺ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎችን ገድሏል አፈናቅሏልም።...more5minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.