Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.
January 23, 2025ትግራይ ክልል የቀጠለው ውዝግብየትግራይ ሐይሎች አዛዦች በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ያለውን ሃምሳ ሲደመር አንድ ድርሻ እንዲረከብ እንደሚሹ አስታወቁ። ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ያሉ ታጣቂዎች በትግራይ ሰላም እና ፀጥታ ሴክሬታሪያት ስር እንዲሆኑ፥ ከዚህ ውጪ በሆነ ላይ ግን እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።...more0minPlay
January 19, 2025የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ ጃን ሜዳበዚህ መንፈሳዊ ክብረ በዓል ከንጋቱ ጀምሮ ቅዳሴ ተቀድሷል፣ የኪዳን ፀሎት እና ዝማሬ ደርሷል፣ ቃለ - እግዚአብሔር ተነግራል፣ በቅዱስ ፓትርያርኩም ባህረ ጥምቀቱ ተባርኳል።በልዩ ልዩ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ሕብር ዝማሬዎች ያሸበረቀው የጥምቀት በዓል ታቦተ ሕግጋቱ ወደየ መንበራቸው በምዕመኑ ታጅበው ተመልሰው የበዓሉ ፍጻሜ ኾኗል።...more3minPlay
January 18, 2025የጥምቀት በዓልና ባህላዊ ክዋኔ በወሎሳዱላዎች የተመረጠ ለብሰዉ አርቲና አሽኩቲ ይዘዉ ሹርባ ተሰርተዉ ለጥምቀት በዓል አደባባይ ሲወጡ ከጢነኛ ሎሚ ያልደረሳት ሳዱላ ካለች ማኩረፍ ልማዷ ነዉ ይላሉ ወይዘሮ አረጋሽ ደምሴ...more4minPlay
January 15, 2025ኢትዮጵያውያን በደቡብ አፍሪቃ በሕገ ወጥ የሰዎች አዛዋሪዎች የሚፈጸምባቸው በደል ከፍቷልአቶ ኮስሞስ ገብረ ሚካኤል ለወጣት ኢትዮጵያውያን የተስፋይቱ ምድር ተደርጋ በምትታየው በደቡብ አፍሪቃ በደላሎች የሚፈጽምባቸው በደል መክፋቱን ገልጸዋል።። በሕገ ወጥ መንገድ ደቡብ አፍሪቃ ከደረሱ በኋላ ለእገታ የሚዳረጉት አስቀድሞ ከደላሎች ጋር የተስማሙበትን ውል በጊዜው አላሟሉም የሚባሉት ኢትዮፕያውያን መሆናቸውንም ተናግረዋል።...more5minPlay
January 15, 2025በ2024 በብዛት የተጫኑ መተግበሪያዎች የትኞቹ ናቸው? በ2025 የሚጠበቁትስ?የመተግበሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ በተለያዩ ድረ ገፆች የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በ2024 ዓ/ም ተጠቃሚዎች አውርደው የተጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ናቸው። በቻይናው ኩባንያ ባትዳንስ የተሰራው እና በአሜሪካ የመዘጋት አደጋ የተጋረጠበት ቲክቶክ /TikTok/ በ2024 በብዛት የተጫነ መተግበሪያ ሆኗል።...more0minPlay
January 10, 2025በአፋር የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለው ስጋት እና የክልሉ መንግስት የሰጠው ምላሽበአፋር ክልል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ እየተከሰ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከክልሉ ባሻገር ስጋት ደቅኗል። የመሬት መንቀጥቀጡ ያስከተለው ንዝረት እስከ መዲናዋ አዲስ አበባ ድረስ በተደጋጋሚ እየተሰማ ነዋሪዎችን ስጋት ውስጥ መጣሉ ታይቷል። የ አፋር አባቶች መሬት መንቀጥቀጡ ከፈጣሪ የመጣ ስለሆነ ፈጣሪ እንዲመልስልን ዱአ እናደርጋለን ብለዋል።...more11minPlay
January 10, 2025የትግራይ የሠራተኛ ማሕበራትና የክልሉ መንግስት ዉዝግብየትግራይ መንግስት ሰራተኞች ማሕበር፣ የትግራይ ዓቃብያነ ሕግ ማሕበር፣ የክልሉ ጤና ባለሙያዎች እና የግል ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ማሕበራት እና ሌሎች በጋራ እንዳሉት የተከማቸ የረዥም ወራት ደሞዝ ካለመክፈል በተጨማሪ ከሕግ፣ ከአሰራር እና የቆዩ ስምምነቶች ውጭ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ክልከላዎች አኑሯል ሲሉ ከሰዋል።...more4minPlay
January 06, 2025በአዲስ አበባ የገና ዋዜማ የበዓል ግብዓቶች ግብይትነገ ማክሰኞ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ( የገና በዓል ) ይከበራል።በአዲስ አበባ ልዩ ልዩ ቦታዎች ባደረግነው የበዓል ግብዓቶች ግብይት ቅኝት ገበያው የአቅርቦች እጥረት እንደሌለበት ከሸማቾችና ሻጮች ሰምተናል።ለእርድ የሚሆኑ ከዶሮ እስከ ፍየል፣ ከበግ እስከ የቀንድ ከብት በስፋት የቀረበ ሲሆን የሸማች ፍላጎት መቀነሱን ግን ተገንዝበናል።...more4minPlay
December 31, 2024በኦሮሚያ ክልል አሙሩ ወረዳ ልጆቻቸው ወደ ታጣቂዎች ተቀላቀሉ የተባሉ 17 ሰዎች ታሰሩበአሮሚያ ክልል አሙሩ ወረዳ “ልጆቻችሁ ታጣቂዎች ተቀላቅለዋል” በሚል 17 ሰዎች መታሰራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ 7 ወራት ታስረው የተፈቱ የ75 ዓመት አረጋዊ በተመሳሳይ ክስ ድጋሚ መታሰራቸውን ልጃቸው ገልጸዋል። የአሙሩ ወረዳ አስተዳዳሪ “ቤተሰብ ልጆቹን እንዲያመጣ በተቀመጠ አቅጣጫ” የታሰሩ መኖራቸውን ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል...more5minPlay
December 25, 2024የአቶ ክርስትያን ታደለና ዮሐንስ ቧያሌው ከቃሊቲ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት መዛወርየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው ከቃሊቲ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት መዛወራቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.