Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.
December 23, 2024ለኢትዮጵያ ቀውስ መፍትሔ ሳይበጅ፣ ግጭት ሳይቆም የሽግግር ፍትሕ ተጎጂዎችን ይፈውስ ይሆን?በኢትዮጵያ የቀውስ አዙሪት ግድያ፣ አስገድዶ መደፈር እና መፈናቀልን ጨምሮ የተለያዩ ግፎች የተፈጸሙባቸው ዜጎች ፍትሕ ይጠብቃሉ። ሀገሪቱም ለሽግግር ፍትሕ እየተዘጋጀች ነው። የአማራ እና የኦሮሚያ ግጭት ሳይቆሙ፤ ሀገሪቱን ለቀውስ ለዳረጉ ጉዳዮች መፍትሔ ሳይበጅ ተግባራዊ የሚደረግ የሽግግር ፍትሕ ተጎጂዎችን ለመፈወሱ በርካቶች ጥያቄ አላቸው።...more13minPlay
December 20, 2024የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ - ኮከስ ጥሪ«ፖለቲካችን የተለመደውን የአፈናና አግላይነት፣ የአንድ ፓርቲ የበላይነትና ጠቅላይነት አጠናክሮ ቀጥሏል፣የአገሪቱ ኢኮኖሚ ወደ ጦርነት ኢኮኖሚ ተሸጋግሮ፣ የኑሮ ውድነቱ ከሕዝብ አቅም በላይ በመሆኑ "ምሬትና ተስፋ መቁረጥ በአደገኛ ሁኔታ የመሰደድን ምርጫ እያጎላው መጥቷል"፡፡ ሲል ስብስቡ«ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት» ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ገልጿል።...more4minPlay
December 19, 2024ናዋዥ -የወጣት ኢትዮጵያዉያንን ህይወት የሚበላው የስደት መንገድ«በሕገ-ወጥ ስደት በጣም ብዙ ሰዎች ምድረ በዳ ላይ ቀርተዋል። ሊቢያ ዉስጥ ደብዛቸዉ ጠፍቶ ቀርቷል። ብዙ ስደተኞች አካላቸዉ ጎልዋል። የሰዎችን አካል እየቀደዱ ኩላሊት የሚዘርፉ ሁሉ አሉ። በዚህ ጉዳይ የሰለጠኑ ሰዎች የተደራጁ ሐኪሞችም ጭምር ያሉበት ይህን ስራ የሚሰራ ቡድን በረሃ ላይ አለ።...more17minPlay
December 16, 2024«የዘጠኝ ወር ደሞዛችን አልተከፈለንም» የአዋሽ ወልድያ ሀራ ገበያ የባቡር መስመር ግንባታ ፕሮጀክት ሰራተኞች1.7 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ወጭ የተደረገበት የአዋሽ ኮምቦልቻ ወልድያ ሀራ ገበያ የባቡር መስመር ፕሮጀክት 3500 የሚደርሱ ሰራተኞች ደመወዝ እንዳልተከፈላቸዉ ገለፁ። ግንባታዉ በቱርኩ ስራ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን ሲከናወን የነበረው ፕሮጀክቱ በመቋረጡ ሰራተኞች ደመወዛቸዉ በወቅቱ እንዳልተከፈላቸው ተናግረዋል።...more0minPlay
December 14, 2024የሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የአንካራ ስምምነት፥ የሶማሊላንድ በዓለ ሲመትኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አንካራ ውስጥ ምን አይነት ስምምነት አደረጉ? የሁለቱ አገራት መሪዎች እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችስ ምን አሉ? ዳሰሳ ይኖረናል ። የሁለቱ አገራት ውዝግብ ሰበብ ስለሆነችው ሶማሊላንድ የፕሬዚደንት በዓለ ሲመትም አጠር ያለ ዘገባ አለን ።...more10minPlay
December 06, 2024በጃራ ስደተኞች መጠለያ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ፆታዊ ጥቃትበአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ጃራ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለው ወሲባዊ ጥቃት እየጨመረ መምጣቱ ተገለፀ። በባለፉት ሁለት ወራት 12 ጥቃቶች የተመዘገቡ ሲሆን ጥቃቱ ከዚህም በላይ ሊሆን ይችላል ተብሏል።...more0minPlay
December 04, 2024የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎች አጀንዳዎችን ለሔራዊ የምክክር ኮሚሽን አስረከበ7 አባላት ያሉትና አዲስ ሥራ አስፈፃሚ በቅርቡ የመረጠው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ቢታዩ በሚል በጠቅላላ ጉባኤ ያፀደቃቸውን ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ለብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ አስረክቧል።...more4minPlay
November 27, 2024ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ የሚልቀው የ 2017 ተጨማሪ በጀት አንድምታየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ 582 ቢሊየን ብር በጀት ትናንት ማክሰኛ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።ተጨማሪ በጀቱ የዋጋ ንረትን እንዳያስከትል እና በንግድ ማኅበረሰቡ ላይ ጫና እንዳይፈጥር በምክር ቤቱ አባላት በሥጋትነት ቢነሳም የገንዘብ ሚኒስቴር ግን መንግሥት በጀትን በጥናት ተመስርቶ እና በጥናት መሰራቱን አመልክቷል።...more10minPlay
November 27, 2024የሲቪል ማሕበራት እና አመራሮቻቸው እየገጠማቸው ያለው ችግርየሲቪል ማሕበራትና አመራሮቻቸው በፀጥታ አካላት «በአካልና በስልክ ተደጋጋሚ ወከባና ማስፈራሪያ» እየደረሰባቸው መሆኑን እንደገለፁለት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል አመለከተ። ይህን «ዛቻና ማስፈራሪያ በመሸሽ ከአገር ለመሰደድ የተገደዱ» መኖራቸውንም አስታውቋል።...more4minPlay
November 26, 2024ትግራይ ክልል ሴቶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷልበትግራይ ክልል በሴቶች ላይ የሚፈፀም ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለፀ ። የትግራይ ክልል ሴቶች ማሕበር በአንድ ዓመት 783 ሴቶች ላይ የፆታ ጥቃት ተፈጽሞ 44 ሴቶች በግፍ ተገድለዋል ተብሏል ። የመብት ተቋማት እና የተጎጂ ቤተሰቦች በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች በተለየ ፍርድ ቤት እንዲታዩ መንግስትን ጠይቀዋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.