Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.
November 21, 2024የቤንዚን እጦት ፈተና የሆነባቸው የሀዋሳ ከተማ አሽከርካሪዎችሀዋሳ በህጋዊ ማደያዎች ነዳጅ ማግኘት ሲበዛ አዳጋች ነው፡፡ በከተማው የነዳጅ አቅርቦት የለም ፡፡ በጥቁር ገበያው ላይ ግን አቅርቦቱ ተትረፍርፎ በየጎዳናው በፕላስቲክ ኮዳዎች ይቸበቸባል፡፡ ዋጋው ግን የሚቀመስ አይደለም ፡፡ መንግሥት በማደያዎች በሊትር 90 ብር እንዲሸጥ ብሎ ካስቀመጠው እዚህ በሁለትና በሦስት እጥፍ ይልቃል ፡፡...more4minPlay
November 14, 2024በአሙሩ ወረዳ የታሰሩ ከመቶ በላይ ሰዎች ባለፉት ሰባት ወራት ፍርድ ቤት አልቀረቡምከሰባት ወራት በላይ በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ የታሰሩ ከ100 በላይ ሰዎች እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው ተሰማ። በአሙሩ ወረዳ ኦቦራ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ እነዚህ ሰዎች ልጆቻቹ በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ ታጠቂዎች ጋር ተቀላቅለዋል ተብለው መታሰራቸውን ያነጋገርናቸው የታሳሪ በተሰቦች ለDW ተናግረዋል፡፡...more4minPlay
November 14, 2024የኦሮሚያ ጸጥታ ይዞታ፤ የንጹሃን ጥቃትበኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ድሮንን ጨምሮ በሚጣሉ ከባባድ መሳሪያዎች ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡ የአከባቢው ነዋሪዎች በተለይም ሰኞ እለት በተጣለው ጥቃት ንጹሃን መጎዳታቸውን ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል ዛሬ ኦሮሚያ ውስጥ በተለያዩ ዞኖች እና ከተሞች ስለሰላም የሚጣሩ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡...more4minPlay
November 07, 2024ኢሰመኮ 5,568 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ዐሳወቀበኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት «በርካታ» ሕፃናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዐሳውቋል ። «ትምህርት ዓለምን ለመለወጥ ልትጠቀምበት የምትችለው እጅግ ኃያሉ መሣሪያ ነው ።»...more4minPlay
November 01, 2024«የምክክር ኮሚሽኑ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ ነው» ፕሮፌሰር መስፍን አርአያባለፉት ሁለት ዓመታት ገደማ በስራ ላይ የነበረው ኮሚሽኑ በአንድ በኩል ሀገሪቱ ካለችበት ግጭት እና ጦርነቶች የተነሳ ሃገራዊ ምክክሩን አላፈጠጠነም የሚል ቅሬታ ሲቀርብበት በሌላ በኩል ደግሞ ለገዢው ፓርቲ የወገነ እና ሌሎች ባለድርሻ ሊሆኑ የሚገባቸውን ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ታጣቆዎችን አላካተተም በሚል የአካታችነት ጥያቄ ሲነሳበት ይሰማል።...more35minPlay
October 30, 2024እስር፤ ግድያና እገታ በጉራጌ ዞንበማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ከፋኖ እና ሸኔ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ነዋሪዎች እየታሰሩ መሆናቸውን ተናገሩ ። በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እገታ እና ግድያ ይፈጽማሉ የሚሉ እንዳሉ ሁሉ መንግሥት ግንኙነት የሌላቸውን እያሰረ ይገኛል ሲሉም ይከሳሉ ።...more4minPlay
October 20, 2024ኢትዮጵያውያንን የሚፈታተነው የዋጋ ግሽበትየመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በጥቅምት ወር ተግባራዊ እንደሚሆን የገንዘብ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። ጭማሪው ተግባራዊ የሚሆነው የዋጋ ግሽበት ኢትዮጵያውያንን በሚፈትንበት ወቅት ነው። በወር 8 ሺሕ ብር የሚከፈላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ 3 ሺሕ ብር የቤት ኪራይ ከፍለው፤ አስቤዛ ሸምተው ወጪያቸውን ለመሸፈን እንደሚጨነቁ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።...more3minPlay
October 19, 2024በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ 19 የመንግስ ታጣቂዎች መገደላቸውንጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም. ሌሊት ለሃሙስ አጥቢያ ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ ውስጥ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለ ጥቃት አንድ ፖሊስን ጨምሮ 19 ሚሊሻዎች ተገድለዋል፡፡...more4minPlay
October 11, 2024የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሰለባዎችን የሚመለከቱ ሕግጋትኢትዮጵያ ውስጥ በተለያየ ጊዜ ለተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለተጎጅዎች ማካካሻ እንዲሰጥ የሚረዳ እና የጅምላ ወንጀሎችን ለመመርመር የሚያግዝ የሕግ ሠነዶችን ማዘጋጀታቸውን የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብት ድርጅት ገለፀ።...more0minPlay
October 09, 2024የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት የገጠመው ፈተናየመንግሥታቱ ድርጅት በአማራ ክልል በረድዔት ሠራተኞች ላይ እየደረሰ ነው ያለውን ጥቃት ተከትሎ መሠረታዊ የምግብ አቅርቦትን ጨምሮ የሚያቀርበውን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቋረጥ ውጥን መያዙን ዘገባዎች አመለከቱ።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.