Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.
July 24, 2026በትግራይ ክልል እየተደረጉ ያሉ ሰሞነኛ ስብሰባዎችና የነዋሪዎች ኹኔታበትግራይ ክልል በተለይ መቀሌ ውስጥ ተከታታይ ስብሰባዎች እየተደረጉ ነው። በስብሰባዎቹ የሚደመጡት መልዕክቶች ህወሓት ከኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት እየተካረረ ለመሄዱን ጉልህ ማሳያ ተደርጓል። የፌዴራል መንግሥት የሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙኃን፣ ህወሓትን እና መሪዎቹን የሚነቅፉ ተከታታይ ዝግጅቶችን እያስተጋቡ ይገኛሉ።...more5minPlay
July 23, 2026የጀርመኑ ጎተ የባህል ተቋም 75 ዓመት ሆነዉጎተ-የባህል ተቋም አዲስ አበባ በጎርጎረሳዉያኑ 1962 ዓ.ም ተመሰረተ። ተቋሙን መርቀዉ የከፈቱት ንጉሠ ነገሥት አጼ ኃይለ ሥላሴ እና የወቅቱ የጀርመን አምባሳደር ፓውለስ ቮን ስቶልዝማን ናቸዉ። ኢትዮጵያ የሚገኘዉ የጀርመኑ የባህል ተቋም የጎተ 64 ኛ ዓመቱን ይዟል። ተቋሙ በሚቀጥለዉ ዓመት 65 ኛ ዓመቱን ለማክበር በዝግጅት ላይ ነዉ።...more0minPlay
July 23, 2026ኢትዮጵያውያን በገዛ ፈቃድ ከደቡብ አፍሪቃ እየተመለሱ ነዉበደቡብ አፍሪቃ በዉጭ አፍሪቃዉያን ዜጎች ላይ የሚፈፀመዉ ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ወደ ሃገራቸዉ የሚመለሱ አፍሪቃዉያን ቁጥር እየጨመረ ነዉ። በደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን አብዛኞቹ ሱቆቻቸዉ ተዘርፈዉባቸዋል ፤ ወድመዉባቸዋል፤ አልያም ከሱቃቸዉ ተባረዋል። በርካታ ኢትዮጵያዉያን በየእለቱ ወደ ሃገራቸዉ እየተመለሱ ነዉ።...more0minPlay
July 23, 2026የድሮን ጥቃት በአባይ ገዳመ አስቄጤስ አቡነ አረጋዊ እና ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳምበአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ በሚገኘው አባይ ገዳመ አስቄጤስ አቡነ አረጋዊና ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ላይ ሐምሌ 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ተፈፀመ በተባለ የድሮን ጥቃት የ2 መነኮሳይት ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ፣ በ11 መነኮሳይት ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ አካል ጉዳት መድረሱን የገዳሙ አበምኔትና የወረዳዉ ቤተክህነት ኃላፊ ገለፁ።...more0minPlay
July 23, 2026የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) ከሌሎች ታጣቂዎች ጋር ስለመተባበር ምን አለ?ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስትን እንደሥጋት ተመልክተው ከሚወጉ አካላት ጋር ትብብር መፍጠሩን ዐሳውቋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት ስምንት ዓመታት ግድም አገሪቱን የሚመራውን መንግስት ያለማቋረጥ በመውጋት ላይ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ-ኦነሰ) ይህን የህወሓት መግለጫን አላስተባበለም፡...more0minPlay
July 23, 2026የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች በሚያቀርቡት ሐሳብ እንዳይጠየቁ ኃላፊነት እወስዳለሁ - አገራዊ ምክክርየአገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች በምክክሩ ላይ በሚያቀርቡት ሐሳብ እንዳይጠየቁ ኃላፊነት እንደሚወስድ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ ተናገሩ። ዋና ኮሚሽነሩ ይህንን ያሉት፦ ከተጀመረ ስምንተኛ ቀኑን በያዘው ጉባኤ ያለፉት ሦስት ቀናት ሂደት ምን እንደሚመስል ዛሬ ቀትር ላይ በሰጡት አጭር ገለፃ ነው።...more0minPlay
July 23, 2026የአሜሪካ ሕግ አውጪ ምክር ቤት ስለ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትየአሜሪካ ሕግ አውጪ ምክር ቤት (ኮንግረስ) አባላት፣ የውጭ ፖሊሲ ጉዳይ ፖሊሲ ባለሙያዎች፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እና ተሟጋቾች የኢትዩጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ሰሞኑን የምስክርነት ቃል መከታተላቸውን ፣የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪል ድርጅቶች ሰብሳቢ አቶ መስፍን መኮንን ለዶቼ ቬለ ዐሳውዋል።...more5minPlay
July 22, 2026ናሳ፤ ወደ መሬት ሊወድቅ ተቃርቧል የተባለን ቴሌስኮፕ ለማዳን ሮቦት ወደ ጠፈር ላከየአሜሪካው የጠፈር ምርምር ጣቢያ ናሳ፤ ወደ መሬት ሊወድቅ ተቃርቧል የተባለን ቴሌስኮፕ ቀልቦ የሚይዝ ሊንክ የተባለ በሮቦት የታገዘ መንኮራኩር ሰሞኑን ወደ ህዋ አምጥቋል። ይወድቃል የተባለው ስዊፍት የምልከታ ቴሌስኮፕ ከጎርጎሪያኑ 2004 ዓ/ም ጀምሮ በአፅናፈዓለም (Universe ) ከፍተኛ ፍንዳታዎች ከመከሰታቸው በፊት የሚመረምር ነው።...more0minPlay
July 22, 2026የግብፅ የህዳሴ ግድብ ውንጀላና የኢትዮጵያዊው ባለሙያና ተደራዳሪ ምላሽየግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ግብፅና ሱዳን ስለህዳሴ ግድብ የደህንነት ደረጃ ወይም አካባቢያዊ ተጽዕኖ የደረሰን የጥናት ውጤት የለም ብለዋል። የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን አባልና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሃይድሮ ፖለቲክስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ግን የግብፅ አስተያየት የተለመደና በመረጃ ላይ ያልተመሰረተ መኾኑን ይናገራሉ።...more0minPlay
July 22, 2026ደብረ ብርሀን የሚገኙ ተፈናቃዮች ሮሮየወይንሸት መጠለያ ካምፕ ነዋሪ አቶ መካሻ ይመር ለሁለት ወር ከ10 ቀናት ምንም ዓይነት ምግብ እንዳልቀረበላቸው ይገልጻሉ። «ቀኑም ሌሊቱም፣ ጨለማ ነው ለእኛ። ምንግዜም ሌሊቱም ቀኑም ጨልሞብናል፤ መቼ እንደሚነጋ ብቻ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው። ዝናቡ 24 ሰዓት ነው የሚዘንብብን እንደማንም ብርዱ ይቻል ነበር፤ ግን ረሃብ አይቻልም። »ብለዋል,...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.