Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,915 episodes available.
August 24, 2022ገዳዩ የማርበርግ ተሃዋሲ ስጋትና ሳይንሳዊ የምርምር ተስፋውከአፍሪቃዊቷ ዩጋንዳ በተለምዶ «አረንጓዴ ጦጣዎች» ከሚባሉ ወርቃማ አረንጓዴ የሆነ የቆዳ ጸጉር ቀለም ያላቸው፤ የአደገኛው የማርበርግ ተላላፊ ተሃዋሲው ተሸካሚ ከሆኑ የጥንት ዘመን የጦጣ ዝርያዎች ተሰራጨ የተባለው ማርበርግ ተሐዋሲ ስያሜውን ያገኘው ከጀርመኗ ማርበርግ ከተማ ነው። ተሐዋሲው ለመጀመሪያ የተገኘውም በከተማዋ የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ነው።...more11minPlay
July 25, 2022የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ኮከስ የግጭት ማስቆም ጥሪበኢትዮጵያ ውስጥ ተባብሶ የቀጠለው ግጭትና የዜጎች የኑሮ ውድነት ፈተና እልባት ካላገኘ ወደ ከፋ ደረጃ ሊሸጋገር እንደሚችል የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ኮከስ አስታወቀ፡፡ ኮከሱ በሳምንቱ መጨረሻ ከተወያዬ በኋላ የዜጎችን ሰቆቃ ለማብቃት አካታች፣ ገለልተኛ እና ግልጽ ብሔራዊ መግባባት ባፋጣኝ እንዲደረግ ጠይቋል፡፡...more0minPlay
June 24, 2022የረሃብ ስጋት በኢትዮጵያኢትዮጵያ ዉስጥ በተከሰተ ድርቅ እና የተለያዩ ግጭቶች ከ 20 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለረሃብ ተጋልጦአል ሲል የተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ድርጅት ገለፀ። የዓለሙ የምግብ ድርጅት ከሚቀጥለዉ ወር ጀምሮ የሚሰጠዉ የምግብ ድጋፍም ሊቀንስ ይችላል ሲል አስጠንቅቋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በሃገሪቱ ረሃብ ስጋት እንደሌለ ገልፆአል።...more5minPlay
May 25, 2022አሳሳቢው የጋዜጠኞች እስር በኢትዮጵያየዘፈቀደ እስር፣ የጋዜጠኛን የሙያ ፈቃድ ነጥቆ ከአገር ማባረር፣ የፕረስ ነጻነት መጣስ እና ጋዜጠኞችን ማጥቃት ከያዝነው ወር ጀምሮ መጨመሩን የገለጹት የድርጅቱ የምሥራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሳዲቡ ማሮንግ የታሰሩት ጋዜጠኞች በሙሉ ባንዴ እንዲፈቱና የስቱድዮ ዕቃዎቻቸውም እንዲመለሱላቸው ጠይቀዋል።...more4minPlay
May 16, 2022በባቲ ወረዳ ታጣቂዎች 3 ሰዎችን ገደሉበአፋር እና አማራ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች ከሳር ግጦሽ፣ ስርቆት እና ግድያ ጋር በተያያዘ የሚከሰትን ችግር ለመፍታት ለእርቅ በተቀመጡ ሰዎች ላይ ባለፈው ቅዳሜ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 3 ሰዎች መገደላቸውን እና የቆሰሉም እንዳሉ የአፋር እና የአማራ ክልል አዋሳኝ ወረዳ ኃላፊዎች ተናገሩ።...more4minPlay
May 11, 2022የተባባሰዉ የሰብአዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያኢሰመኮ ዛሬ ለተወካዮች ምክር ቤት የፍትሕና የዴሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበዉ የ10 ወር ዘገባዉ እንዳለዉ በየጊዜዉ በሚያገረሹ ግጭቶች ምክንያት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየጨመረ፣ ተጠያቂነትና የሕግ የበላይነት እየላላ ነዉ።...more4minPlay
May 04, 2022መንግሥት የደመወዝ ቦርድ የሚያቋቁመውን ደንብ እንዲያወጣ ኢሠማኮ ጠየቀየኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ዝቅተኛ ደመወዝ የሚወስነውን ቦርድ የሚያቋቁም ደንብ እንዲያወጣ ለመንግሥት ጥሪ አቀረበ። ደንቡ በቀድሞው የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተዘጋጀ ነው። የኢሠማኮ ፕሬዝደንት ካሳሁን ፎሎ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ጉዳይን ጨምሮ በሠራተኞች አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ለዶይቼ ቬለ ማብራሪያ ሰጥተዋል...more17minPlay
May 02, 2022የዩክሬን ቀውስና የሩሲያ የነዳጅ ጦርነትሩሲያ በዩክሬን የጀመረችው ጦርነት ዛሬ ሰኞ 68ኛ ቀኑን አስቆጥሯል። ብርቱ ሰብዓዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ቀውስ ያስከተለው ጦርነት ሰሞኑን ወደ ነዳጅ ግብይት የመሻገር አዝማሚያ እያሳየ ነው። ሩሲያ ለፖላንድ እና ቡልጋሪያ የምታቀርበውን ነዳጅ በሩብል ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆኑም በሚል ምክንያት አቋርጣለች። የአውሮፓ ኅብረት ውሳኔውን ነቅፏል...more14minPlay
March 03, 2022የዩክሬን ጦርነት ያስከተለው የዋጋ መናርየሩሲያ ዩክሬን ጦርነት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማድረሱ እየተነገረ ነው። የአንድ በርሜን ዋጋ 110 ዶላር መግባቱ የአፍሪቃ ሃገራት የኃይል አቅርቦት ላይ የዋጋ ጭማሪ አስከትሏል። ተጽዕኖው የነዳጅ ሀብት በሌላቸው ብቻ ሳይሆን እንደ ናይጀሪያ ባሉ የነዳጅ ባለሀብቶች ላይ ሳይቀር ከወዲሁ መታየት ጀምሯል።...more0minPlay
March 02, 2022የሩሲያን ኤኮኖሚ ከዓለም አቀፉ ገበያ ሚገፉት ማዕቀቦችበዩክሬን ጦርነት ምክንያት ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ባለሥልጣኖቻቸውና የሩሲያ ባንኮች ብርቱ ማዕቀቦች ተጥለውባቸዋል። የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ 630 ቢሊዮን ዶላር ከማንቀሳቀስ ሲታገድ የሩብል ምንዛሪ አሽቆልቁሏል። አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረትና አጋሮቻቸው የሚወስዷቸው እርምጃዎች የሩሲያን ኤኮኖሚ ከዓለም አቀፉ ሥርዓት እንደሚገፋ ተንታኞች ይናገራሉ...more9minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,915 episodes available.