Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,915 episodes available.
September 02, 2020የተመራቂ ሐኪሞች ሥራ ማጣትትምህርታቸውን በ2012 ዓ ም መጀመሪያ ላይ ያጠናቀቁ አንዳንድ የህክምና ሳይንስ ተመራቂ ዶክተሮች የአማራ ክልል ቋሚ ቅጥር ሊፈፅምልን አልቻለም አሉ። በመላ ሀገሪቱ ከተመረቁት አብዛኛው ቁጥር በአማራ ክልል እንደሚገኝም አመለከቱ።...more5minPlay
July 05, 2020በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን በቦምብ ጥቃት 5 ሰዎች መቁሰላቸውን የአማራ ክልል አስታወቀድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ በኋላ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን በታጣቂዎች ጥቃት መፈጸሙን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ እንዳሉት ጥቃቱ የተፈጸመው ደዌ ሐረዋ በተባለ ወረዳ ነው። በባቲ ከተማ በተወረወረ ቦምብ አምስት ሰዎች መቁሰላቸውን የክልሉ ባለሥልጣናት ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል...more3minPlay
June 12, 2020«የሙስሊሙ ማሕበረሰብ የረዥም ጊዜ ጥያቄ ተመልሷል፤ ተደስተናል።»ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስጉዳዩ ሃገራዊና የመብት ጥያቄ ነበር ያሉት የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ መንግስት ከህጋዊነት ጥያቄው ባሻገር የባንክ መመስረት እና የመስጊድ መገንቢያ ስፍራዎች ጭምር የተፈቀዱበትና ለዚህ ጥያቄም ምላሽ ማግኘት ኢትዮጵያዊ ክርስትያኖችም የታገሉበት በመሆኑ ፣ ለሁሉም ምስጋና ይገባል ብለዋል።...more0minPlay
June 10, 2020ልጆችና ሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት በኢትዮጵያከሰሞኑ አዲስ አበባ ውስጥ ኮሮና ተሐዋሲ ካስከተለው እንቅስቃሴ ላይ የተጣለ ገደብ ጋር በተያያዘ 101 ልጆች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ለእነሱ የቅርብ በሆኑ ወገኖች መፈጸሙ በይፋ ከተሰማ ወዲህ ጉዳዩ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል። ከዚህ ቀደምም ጥቂት የማይባሉ በርካታ መሰል ድርጊቶች በሕግ ባለሙያዎችና የመብት ተሟጋቾች ዘንድ ተመዝግበዋል።...more5minPlay
May 14, 2020ኢህአፓ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እንደተጠበቀው እየሄደ አይደለም አለየኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ኢህአፓ በሀገሪቱ ውስጥ የሚታየው የፖለቲካ ሁኔታ እንደተጠበቀው እየሄደ አይደለም አለ። ፓርቲው በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ላይ ባወጣው መግለጫው እንዳመለከተው ሃገሪቱ ከገባችበት ችግር ውስጥ እንድትወጣ የበኩሉን ሚና ለመጫወት መዘጋጀቱን የፓርቲው መሪ ወ/ሮ ቆንጅት ብርሃኔ ተናግረዋል።...more4minPlay
December 13, 2019የኖቤል ሽልማቱ ከሸክም ይልቅ ጌጥ እንዲሆን ምን ይደረግ?ኢትዮጵያ በዘመኑ ቋንቋ ስትደመር ስትቀነስ ይኸው ሁለት ዓመት ሊሞላት ነው። ሰሞኑን ብዙ ሰዎች መልሰው የተደመሩበት ሰሞን ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል ሽልማት ሲቀበሉ ከሞላ ጎደል የነበረው ስሜት ጮቤ የመርገጥ ነበር። ስሜቱ ብሔርተኝነት በጣም የተጫነው ስለሆነ ድጋፉ ዘላቂ ይሁን አይሁን ለመገመት ይቸግራል።...more0minPlay
December 12, 2019ስለ ኖቤል ሽልማቱ ኤርትራዊያን ምን አሉ?የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የዓለም የሰላም የኖቤል ሽልማት ተሸላሚ መሆናቸው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተጀመረውን ሁሉ አቀፍ ግንኙነት ከተቀዛቀዘበት አንድ እርምጃ ወደፊት ያራምደዋል የሚል እምነት እንዳላቸው በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ተናገሩ።...more0minPlay
December 10, 2019ጠ/ሚ ዐቢይ የኖቤል የሰላም ሽልማታቸዉን ተቀበሉጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በኦስሎ የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን ተቀበሉ። ዐቢይ የኢትዮ ኤርትራ ወደ ሰላም መምጣት ዋናዉ መሃንዲስ ተብለዉ ተሞግሰዋል። በሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ጥሩ ንግግር ማሰማታቸዉን የዓለም ብዙኃን መገናኛዎች እየዘገቡ ነዉ።...more0minPlay
November 06, 2019የወጣቶች ስደት በትግራይ መበራከቱየትግራይ ክልል ወጣቶች በሕገወጥ መንገድ የሚያደርጉት ስደት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለፀ። ክልሉ የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ይህ የስደት ጉዳይ ለክልሉ መንግሥት አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን ያመለክታል።...more0minPlay
October 17, 2019ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በአፋርበአፋር ክልል የሰሞኑን ጥቃት እና ግድያ በመቃወም በሰመራ እና በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ዛሬ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል። ሰሞኑን በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን ግድያ በመቃወም በተደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች የፌዴራል መንግሥቱ ቸልተናነትን እና ዝምታን አሳይቷል ሲሉ ሰልፈኞቹ ተቃውመዋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,915 episodes available.