Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,856 episodes available.
September 04, 2026የተባባሰው የሩሲያ እና የጀርመን-አውሮፓ ህብረት ውዝግብየአውሮፓ ህብረትና አባል መንግስታቱም ይህን በጀርመን ላይ ተቃጣ የተባለውን የድሮን ጥቃት የተፈጸመ ያህል በመቁጠር ቁጣቸውን በመግለጽ ከጀርመን ጎን እንደሚቆሙ አስታውቀዋል። በሩሲያ ላይ ከፍተኛ ጫና በማድረግም ከድርጊቱ እንድትቆጠብ ማድረግ የሚያስፈልግ መሆኑን በጋራና በየግላቸው ባወጧቸው መገለጫዎችና ባስተላለፏቸው መልዕክቶች አሳስበዋል።...more5minPlay
September 04, 2026ደብዛው የጠፋው የፎቶ ባለሙያ ፊልሞን ገብረ ሕይወት የት እንዳለ እንዲገለጽ አምነስቲ ጠየቀአምነስቲ ኢንተርናሽናል እንዳስታወቀው የሰብአዊ መብት ተሟጋች፣ የፎቶ እና ተንቀሳቃሽ ምስል ባለሙያ ሲል የገለፀው ፊልሞን ገብረ ሕይወት እንደ በጎርጎሮሳዊውት ነሐሴ 2025 ወዲህ የት እንዳለ አይታወቅም። የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት ስለ ግለሰቡ መጥፋት የተጀመረ ምርመራ ስለመኖሩ በይፋ አለማሳወቃቸውንም አስታውቋል።...more4minPlay
September 04, 2026የኢትዮ-ቴሌኮም እቅድና የደንበኞች ምሬትዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የስትራቴጂያቸው ዋና ትኩረት ኩባንያውን ከቴሌኮም ኦፕሬተርነት ወደ ላቀ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ኩባንያ ማሸጋገር እና የደንበኞችን ተሞክሮ ማሻሻል ነው ይላሉ። ይሁንና ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የቴሌኮም ደንበኞች አሁንም ተደጋጋሚ የኔትወርክ መቆራረጥ፣ የዳታ ፍጥነት መቀነስ እና የአገልግሎት ጥራት መጓደል አማሯቸዋል።...more4minPlay
September 04, 202612ተኛ ክፍል የወደቁ ተማሪዎች ዕጣ ፋንታቸው ምን ይሆን?በ2018 ዓ.ም. በተካሄደው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ565 ትምህርት ቤቶች ምንም ዓይነት ተማሪ አላሳለፈም። ከ550,210 ተፈታኞች ያለፉት 70,544 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።...more0minPlay
September 03, 2026ህወሃት በፌደራል መንግስት ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት እየተፈጸመብኝ ነው ሲል ከሰሰየፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ በአንጻራዊ ሰላም ውስጥ የቆየው የህወሃትና የኢትዮጵያ መንግስት አለመግባባት ዳግም ማንሰራራቱን ተከትሎ፣ የፌደራል መንግስት በሲቪልና በህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ የድሮንና የሚግ ጥቃት እያካሄደብኝ ነው ሲል ህወሃት ይከሰሰ።...more4minPlay
September 03, 2026የሀረሪ ሕዝብ ማንነትና ባህል ገላጮቹሆኑ የእደ ጥበብ ሥራዎችየሐረር የጌይ ሞኣት (የአለላ ስፌት) ሥራ ዓለም አቀፍ የንግድ ምልክት ሆኖ የመዘገበው የሀረሪ እናቶች እደ ጥበብ ነው። ለመሆኑ ስለ ሀረሪ ሕዝብ የእደ ጥበብ ሀብቶች ስናነሳ በዋናነት የሚጠቀሱት የትኞቹ ናቸው?...more15minPlay
September 03, 2026አብን የኦሮሚያ የጸጥታ ሁኔታ በእጅጉ አሳስቦኛል አለበኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሚፈጸሙ ጥቃቶች ዜጎችን ህልውና እየተፈታተኑ በመሆኑ መንግሥት የሕግ የበላይነትን የማስከበር እና የዜጎችን ደኅንነት የማረጋገጥ ቀዳሚና የመጀመሪያ ደረጃ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ሲል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አሳሰበ፡፡...more5minPlay
September 03, 2026የኤልኒኖ ያስከተለው የአየር ንብረት ለውጥ እና የኃይል አቅርቦት ተጽዕኖኢትዮጵያ ውስጥ በዘንድሮ የክረምት ወራት ባጋጠመው የኤልኒኖ የአየር ንብረት ለውጥ ወደ ወንዞች እና ግድቦች መግባት የነበረበት የውኃ መጠን በ20 በመቶ መቀነሱ እየተነገረ ነው፡፡...more5minPlay
September 03, 2026ስለ ምክክር ጉባኤ የሲቪል ማሕበራት እና ፓርቲዎች ትዝብቶችሰሞኑን የመጀመርያ ደረጃ የትዝብት ዳሰሳውን ይፋ ያደረገው የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት፣ አሥር ታዛቢዎቹ አንዳንድ ውይይቶችን እንዳይታደሙ እንደተደረጉ፣ ወደ አዳራሾች እንዳይገቡም ክልከላ ተጥሎባቸው እንደነበር ገልጿል።...more5minPlay
September 03, 2026በአሜሪካ የጥገኝነት ጠያቂዎችን ቃለ መጠይቅ ያስቀራል የተባለው አዲሱ ሕግ ምን ይዞ መጣ?የአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደኅንነት መስሪያ ቤት፣የዩናይትድ ስቴትስ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት ባለሥልጣናት፣ ለጥገኝነት ጠያቂዎች ያደርጉት የነበረውን ቃለ መጠይቅ የሚያስቀር ሕግ ማውጣቱ ተገለጸ።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,856 episodes available.