Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,856 episodes available.
September 06, 2026አማራጭ ለጀርመን በዛክሰን አንሃልት ግዛት የምክር ቤት ምርጫ ትልቅ ውጤት እንደሚያገኝ ተተነበየበዛክሰን አንሃልት ግዛት በተካሔደው ምክር ቤታዊ ምርጫ ቀኝ አክራሪው አማራጭ ለጀርመን ከ44% በላይ ድምጽ በማግኘት እንደሚያሸንፍ መራጮች ድምጽ ሰጥተው ሲወጡ የተሰበሰበ አስተያየት አሳይቷል። የመራኄ መንግሥት ፍሬድሪሽ ሜርስ ክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት (CDU) በምርጫው ከተሰጡ ድምጾች 18.5% እንደሚያገኝ ይፋዊ ያልሆነው ውጤት አሳይቷል።...more0minPlay
September 06, 2026በኢትዮጵያ ሰላም ለምን እውን መሆን አልቻለም?የትግራዩ ክልሉ ጦርነት በውጪ ኃይሎች ፖለቲካዊ ተፅዕኖና በአፍሪቃ ሕብረት ሽምገላ በፕሪቶሪያ ውል ቢቋጭም ግጭት ጦርነቱ ግን በአማራ ክልል በሌላ መልኩ ቀጠለ:: ኦሮሚያም ሰላም ከራቃቸው ክልሎች ቀዳሚው ነው። በርከት ባሉ መደበኛና ኢመደበኛ ታጣቂና አማጻያን ፍልሚያ የሲቪሉ ማኀበረሰብ ኑሮ ለሰቀቀን ከተዳረገ ከርሟል።...more45minPlay
September 06, 2026በጀርመን ዛክሰን አንሃልት ግዛት ከፍተኛ ትኩረት የሳበ ምክር ቤታዊ ምርጫ እየተካሔደ ነውበዛክሰን አንሃልት ግዛት እየተካሔደ በሚገኘው ምክር ቤታዊ ምርጫ 1.7 ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ድምጽ የሚሰጡ ሲሆን መላው ጀርመንና የተቀረው ዓለም በዐይነ ቁራኛ የሚከታተሉት ነው። ምርጫውን ቀኝ አክራሪው አማራጭ ለጀርመን (AFD) ፓርቲ ሊያሸንፍ እንደሚችል ይጠበቃል።...more0minPlay
September 05, 2026ትኩረት በአፍሪካ፤ የኒጀር ወቅታዊ ሁኔታ፤ የዛምቢያ የዴሞክራሲ እሴቶች መሸርሸር« ፕሬዝደንቱ ወደፊት መራመድ አለባቸው። ወደፊት በሚጓዙበት ጊዜ በምርጫው ወቅት የገቡትን ቃል ኪዳን መተግበር አለባቸው። ይህ ማለት ድምፁን ለሳቸው የሰጣቸውም ያልሰጣቸውም ሁላችንም እኩል ነን። የሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ድምፅችን የሚደመጥበት በተለይ ወጣቶች ደግሞ ልዩ ትኩረት የሚያገኙበት እንዲሆን እፈልጋለሁ።»...more16minPlay
September 05, 2026በኢትዮጵያ የሚቋቋመው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ«ባለፈው 20 ዓመት የተጀመረው የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ እስካሁን ድረስ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክልል ከተሞች የተገነቡ ቤቶች ግማሽ ሚሊየን እንኳ አለመድረሳቸውን ስትመለከት ይህን ያህል ማሳካት ቀላል አይሆንም።»...more4minPlay
September 05, 2026የመብራትና የቴሌኮም አገልግሎትን ያስተጓጎለው ሥርቆት«ተይዘው እንኳን በዋስትና የሚለቀቁበት ነገር አለ። ለእኛም እስካሁን ድረስ ይህ ነገር እንዲባባስ ያደረገበት ምክንያት ይህ ነው ብለን የምናስብበት ነገር አለ። የፍትህ አካላት ጉዳዩን እና ችግሩን አይተውት በቀጣይ ላይ እንደው ማስተካከያ ቢሰራ የሚል ሀሳብ አለኝ።»...more4minPlay
September 05, 2026ተስፋ የተጣለበት የዘይሴ የሰላም ምክክርግጭቱ ንጹሃን ሰዎች ለሞት ፣ ለአካል ጉዳት እና ለመፈናቀል መደረጋቸውን የተናገሩት አቶ አብረሃም «ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ከተፈለገ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላት በህግ የሚጠየቁበት ሁኔታም አብሮ መታየት አለበት» ብለዋል ፡፡...more4minPlay
September 04, 2026በእሥር ላይ ያሉት የኢሕአፓ አመራሮች የዋስትና መብት ተፈቀደጠበቃቸው እንዳሉት ተጠርጣሪዎቹ እያንዳናቸው በ50 ሺህ ብር ማስያዣ የዋስትና መብታቸው ተፈቅዶላቸዋል። ፖሊስ ተከሳሾቹን "ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን እንደሽፋን በመጠቀም" ሥልጣን በኃይል ለመያዝ"በማሰብ ከህወሓት፣"ሌሎች ፀረ-ሰላም" ካያላቸው ኃይሎች ጋርና "ፅምዶ" ከተባለ አካል ጋር በመቀናጀት ተንቀሳቅሰዋል በሚልም ከተያዙ አንድ ወር አልፏቸዋል።...more4minPlay
September 04, 2026የራያ እና የአላማጣ አካባቢ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ርሃብ፣ ድርቅ እና የሰብአዊ መብት ጥሰት መዳረጋቸውን ገለጹበራያ አካባቢ የሚገኙ የስድስት ወረዳዎች እና የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ባለፉት ስምንት ዓመታት በነበረው ጦርነትና አለመረጋጋት ምክንያት ከፍተኛ መከራ ሲያስተናግዱ መቆየታቸውንና አሁንም ለከፋ የሰላም እጦት እንዲሁም ለርሃብ መዳረጋቸውን አስታወቁ።...more4minPlay
September 04, 2026ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የ “ፌሚኒዝም (እንስታዊነት) “ ንቅናቄበዚህ ንቅናቄ ላይ አንዳንዶች እንቅስቃሴው የሴቶችን መብት ከማስጠበቅ አንጻር በበጎ ጎኑ ይመለከቱታል ፡፡ ሌሎች ደግሞ ንቅናቄውን ከሚገባው በላይ በመለጠጥ በተለይ ታዳጊ ሴቶች ከወንዶች ጋር ያላቸው ማህበራዊ መስተጋብር በፍርሃትና በጥርጣሬ የተሞላ እንዲሆን እያደረገ ነው የሚሉም አሉ ፡፡...more12minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,856 episodes available.