Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,856 episodes available.
September 02, 2026በጋምቤላ ክልል የምርት መቀነስን ለማካካስ መስኖ እንደማራጭየዝናብ እጥረት በስፋት የተስተዋለበት የክልሉ አካባቢዎች የኑዌር ዞን አንዱ ሲሆን በዞኑ ስር በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ውስጥ አሁንም የዝንብ እጥረት እንዳለ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የክልሉ ግብርና ቢሮው አመልክተዋል፡፡ የክልሉ ግብርና ቢሮ ችግሩን ለመቅረፍ መስኖ እንደአማራጭ ይሰራል ብሏል።...more4minPlay
September 02, 2026የምስራቅ ወለጋ ዞን አንጌር ጉቴ አከባቢ ግጭትና ግጭቱ ያፈናቀላቸው ብሶትአንድ ተፈናቃይ እንዳሉት«አሁንም ድረስ ባለው የጸጥታው ችግር መንገድ እንደተዘጋ ነው ያለው፡፡ በቀደም ከአንድ ቀን በፊት እሁድ ከአንገር ጉቴ ወደ ነቀምቴ በቆሎ ጭኖ ስጓዝ የነበረን መኮነን ነጋዴ ፣ታጣቂዎች መንደር 11 ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ከከተማው ብዙም ሳይርቅ እሱን ገድለው ሾፈሩን አግተው ይዘውት ሄደው እስካሁን እጣፈንታው አልታወቀም፡፡...more4minPlay
September 02, 2026የሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበት ቁጥሮች በባለሙያዎች ሲፈተሹኢትዮጵያ ውስጥ የዋጋ ግሽበቱ 15.3 በመቶ መድረሱን በቅርቡ ይፋ የሆነው የሀገሪቱ ስታትስቲክስ አገልሎት መረጃ ያመለክታል። መረጃው እንደሚያመለክተው በተለይ የዋጋ ግሽበቱ ጭማሪ ያሳየው በዋናነት በምግብ እና አልክሆል ያልሆኑ መጠጦች ላይ ነው።...more10minPlay
September 02, 2026በጃናሞራ ወረዳ በደረሰው ድርቅ ከ85 ሺህ በላይ ሰዎች ለከፍተኛ ረሀብ መዳረጋቸው ተገለጸበድርቁ ምክንያት ምግብ በማጣታቸው ሰባት ሰዎች ተስፋ ቆርጠው በመርዝ ራሳቸውን ለማጥፋት ሞክረው፣ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ አምስት ሰዎች በህክምና ድጋፍ መዳናቸውን አርሶ አደር ፈጬ አብዱልቃድር ይገልፃሉ። መርዝ አሁን ትጠጣለህ፣ መርዝ አማራጭ ይወስዳል ብለዋል...more4minPlay
September 02, 2026ጀርመን በሀገርዋ የሚገኙ የተለያዩ የሩስያ ተቋማት እንዲዘጉ ወሰነችየጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሐን ቫደፉል ቦን የሚገኘው የሩስያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት እንደሚዘጋ ፣ በርሊን የሚገኘው የሩስያ ማዕከል የሩስያ ቤት ቤት ኪራይ እንደሚቋረጥ ጀርመን በሚገቩ የሩስያ ዜጎች ላይም ቁጥጥሩ እንደሚጠናከር ተናግረዋል። ሞስኮ ግን ክሱን የሚደግፍ ምንም ዓይነት ማስረጃ የለም ስትል አስተባብላለች ።...more5minPlay
September 02, 2026የምሥራቅ ጀርመኑ የዛክሰን አንሃልት ምርጫና የውጭ ዜጎች ስጋት«በርካታ ሰዎች እየፈሩ ነው። ከሁለት ሳምንት በፊት እናቴን አናግሬያት ነበር። እዚህ ስትኖር 34 ዓመታት ተቆጥረዋል። በታህሳስ ወር ከዚህ ለቃ እንደምትሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ነግራኛለች። በሚቀጥሉት 3 ወራት ነገሮች እንዴት እደሚቀጥሉ ትመለከትና ከዛ ከዚህ ለቆ መሄድን እንደ አማራጭ ይዛለች። በእውነት ይህ ያማል። »...more12minPlay
September 01, 2026የማጃንግ ዞን ደን ይዞታና የተጋረጠበት ስጋትኢትየጵያ በተለያዩ ወቅቶች የሚዳሰሱና የማይደሱስ ቅርሶችን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት አስመዝባለች። በጋምቤላ ክልል የሚገኘው የማጃንግ ዞን ደንም በዚሁ ድርጅት በ2009 ዓ.ም የዓለም የከባቢ ሕይወት ጥበቃ ወይም የባዮስፈር ሪዘርቭ ሆኖ ተመዝግቧል።...more11minPlay
September 01, 2026በአዲስ ዓመት ዋዜማ የሚጎሉት የሰላም ጥሪዎችና ነባራዊ እውነቶችጦርነትና አሁንም የቀጠሉ የትጥቅ ግጭቶች ያደረሱት ሞትና ውድመት ለመሰል ውትወታዎች ዋነኛ ምክንያት ቢሆኑም ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚቃጣ የዘፈቀደ ግድያ፣ ማፈናቀል፣ ቤት ንብረትን ማውደም፣ እሥር፣ ጥቃትና አካል መጉደል፣ ፆታዊ ጥቃት ለሰላም ጥሪዎች ተጨማሪ መነሻዎች ናቸው።...more4minPlay
September 01, 2026የኳሱ ንጉሥ ሊዮኔል ሜሲ ከእንግዲህ ለአገሩ አይሰለፍምአርጀንቲናዊው የኳስ ጥበበኛ ሊዮኔል ሜሲ ለዓመታት የሚታወቅበት 10 ቁጥር መለያውን ለብሶ ለአገሩ በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ እንደማይሳተፍ ሰኞ ዕለት ይፋ አድርጓል ። የ39 ዓመቱ ሊዮኔል ሜሲ በኳሱ ዓለም ማን ይተካው ይሆን?...more4minPlay
September 01, 2026በሰሜን ጎንደር ጠለምት ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ አንድ ሰው ሞተ፣ሺዎች ተፈናቀሉየሚሸራተተው መሬት መቆም ስላልቻለ የሰው ሕይወትን እንጂ እንስሳቶቻቸውን ማዳን አልቻልንም ያሉት ወይዘሮ ውዴ ተሾመ የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፉንና አራት ሰዎች ጠፍተዉ መገኘታቸዉን ይናገራሉ...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,856 episodes available.