Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,856 episodes available.
August 29, 2026የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ትርፍ ማጋበስ እና የተጠቃሚዎች ምሬትበኢትዮጵያ የኃይል ማመንጨት፣ የከፍተኛ ቮልቴጅ ማስተላለፍ እና የጅምላ ኤሌክትሪክ ስርጭትን የሚያከናው ነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) ዘንድሮ ከመቼውም ግዜ የበለጠ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።...more0minPlay
August 29, 2026በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ ነውበአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ ነው። ጋርሺያ ባለፈው ግንቦት ወር ከተሾሙ ወዲህ ኢትዮጵን ሲጎበኙ የአሁኑ የመጀመሪያቸው ይሆናል።...more0minPlay
August 28, 2026ለሃገራቸውና ለማኅበረሰባቸው በጎ የሰሩ ግለሰቦች ሽልማትየሃገራቸው እና የማኅበረሰባቸው ባለውለታዎች ናቸው የተባሉ ግለሰቦች፣ ዩናይትድስቴትስ ቴክሳስ ዳላስ ውስጥ ዕውቅና እና ሽልማት ተሰጣቸው። ዘንድሮ ለዐሥረኛ ጊዜ በቴክሳስ ዳላስ በተካሄደው በዚሁ የምስጋና እና ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ፤በተለያዩ ዘርፎች ሽልማትና ዕውቅና የተሰጣቸው ዐሥር ግለሰቦች ናቸው።...more0minPlay
August 28, 2026በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ምላሽበኢትዮጵያ ሰሜን ምስራቅ እና ሰሜናዊ ክፍል አንዳንድ አከባቢዎች ላይ በክረምቱ በብርቱ የሚጠበቀው ዝናብ ባለመጣሉ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው አርሶአደሮች እና አርብቶ አደሮች ላይ ስጋት ማንዣበቡ ተነግሯል። በኢትዮጵያው ድርቅ አደጋው 165 ወረዳዎች ተለይተው ለምላሹ እየተሰራበት መሆኑን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ገልጿል።...more0minPlay
August 28, 2026በአፋር ክልል የዝናብ መቅረትና የቀረጥ ጭማሪ አርብቶ አደሩን ፈትኖታልበአፋር ክልል ባለፈው አንድ ዓመት በቂ ዝናብ ባለመገኘቱ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ በአርብቶ አደሮችና እንስሳቶቻቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። በተለይም በዳሊፋጌ እና በያንጉዲ ወረዳዎች የውሃና የመኖ እጥረት በመከሰቱ በርካታ አርብቶ አደሮች አካባቢያቸውን ለቀው ወደ አዋሽ ተፋሰስ በመሰደድ ላይ ናቸው።...more0minPlay
August 28, 2026በኦሮሚያ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ምስራቃዊ ወረዳዎች ጥቃትበኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቀርሳ ማሊማ ወረዳ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ታጣቂዎች አደረሱት በተባለው ጥቃት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡ በወረዳው ማክሰኞ ማለዳውን ተጀምሮ ቀኑን ውሎበታል በተባለው የታጣቂዎቹ ጥቃት ቢያንስ በአንድ ቀበሌ ብቻ ሰባት ሲቪል ሰዎች ስለመገደላቸው የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡...more4minPlay
August 28, 2026በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ያስመዘገበው ጃለል ግርማጃለል ግርማ ጎበዝ ተማሪ እንደሆነ አስቀድሞ ያውቀዋል። ጥሩ ውጤት እንደሚያመጣም ጠብቆ ነበር። ያልገመተው ነገር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ውጤት እንደሚያስመዘግብ ነው።...more0minPlay
August 28, 2026ፍርድ ቤት የቀረቡት የኢሕአፓ አባል ፖለቲከኞች ተቀጠሩ"በአገር ማፍረስ ሴራዎች" ተጠርጥረው በእሥር ላይ የሚገኙትና ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት የኢሕአፓ አባል ፖለቲከኞች እና ጠበቃ ለቀጣዩ ሐሙስ ነሐሴ 28 ቀን ተቀጠሩ። ኢሕአፓ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለኢሰመኮ ጉዳዩን በደብዳቤ ያሳወቀ መሆኑን ገልጾ "ኹኔታው ተጣርቶ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥያቄ አቅርቧል።...more3minPlay
August 28, 2026የመቀሌ የሰላም ናፍቆትትዝታዋ፣ ፍቅሯ ከናፍቆት ጋር በዜማና በጽሑፍ የተነገረላት መቀሌ፣ ከዓመታት የጦርነት ቁስል በኋላ ዳግም በጦርነት ስጋት ውስጥ ገብታለች። የከተማዋ ነዋሪዎች የዕለት ኑሮ፣ የንግድ እንቅስቃሴ፣ የወጣቶች ተስፋ ሌላ መልክ ይዟል።...more0minPlay
August 27, 2026ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገራት ብሔራዊ ምክክር የትኛዉን ተሞክሮ ትዉሰድ?ኢትዮጵያዉያን ያካሄዱት ምክክር የሃገሪቱን የኃይል ፖለቲካ ወደ ዉይይት ባህል፤ ወደመደማመጥ ባህል ያመጣ ከፍተኛ ለዉጥ ነዉ ብለዉ ያስባሉ? የተገኙት የመፍትሄ ሃሳቦች በቀጣይ ተግባራዊ እንዴት ተግባራዊ ይደረጋሉ? በአፍሪቃ የትኞቹ ሃገራት ብሔራዊ ምክክርን አካሄዱ? የትኞቹ ተሳካላቸዉ? የትኞቹ ሃገራትስ አልተሳካላቸዉም? የትኛዉን ተሞክሮ እንዉሰድ?...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,856 episodes available.