Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.
August 27, 2026በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጸጥታ ችግር ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውበዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና የአማራ ክልል የማለፍ ምጣኔ 15.56 በመቶ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፣ ተማሪዎች በክልሉ ያለዉ የጸጥታ ችግር ተፅኖ ባያሳድርባቸዉ ኖሮ ከዚህ የላቀም ዉጤት ማምጣት ይቻል ነበር ብለዋል።...more0minPlay
August 27, 2026የቀድሞው የቦስኒያ ሰርብ ወታደራዊ መሪ ራትኮ ምላዲች በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩየቀድሞዉ የቦስኒያ ሰርብ ጄኔራል ራትኮ ምላዲች በ 84 ዓመታቸዉ በእስር ላይ በሞት ተለዩ። ምላዲች፤ በቦስኒያ ከ1992 እስከ 1995 በተካሄደዉ ጦርነት፣ እንዲሁም በጎርጎረሳዉያኑ ነሐሴ 1995 በስሬብሬኒጻ ወደ 8,000 የሚጠጉ ሙስሊም ወንዶችና ፤ ታዳጊ ወንድ ልጆች በተገደሉበት ጭፍጨፋ ውስጥ ለነበረው ሚና ተጠያቂም ነበሩ።...more0minPlay
August 27, 2026የ 9/11 ጥቃት ዋና አቀናባሪ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነዉየአሜሪካው 9/11 የሽብር ጥቃት ዋና አቀናባሪ ተጠርጣሪ ካሊድ ሼክ መሐመድ ከ20 ዓመት እስራት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ፍርድ ሊቀርብ መሆኑ ተሰማ። የኦሳማ ቢላደን የፕሮፖጋንዳ ክፍል ኃላፊ ነበር የተባለዉ ተጠርጣሪ ፤ በኪዮባ ጋንታናሞ እስርቤት 20 ዓመት ሞላዉ። ቀደም ሲል በምህንድስና ሞያ ከአሜሪካ ዩንቨርስቲ ዲግሪዉን ተቀብሏል።...more0minPlay
August 26, 2026ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ታጣቂዎች ሰዎች ገደሉ፣ ንብረት አወደሙበማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ታጣቂዎች ማክሰኞ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓም ባደረሱት ጥቃት ሰዎች መሞታቸውን እና ንብረቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ ፡፡ታጣቂዎቹ በዞኑ የሱተን እና የጢያ ከተሞችን ለግማሽ ቀን ተቆጣጥረው መቆየታቸውን የአይን እማኞች ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል ፡፡...more0minPlay
August 26, 2026በአላማጣና ዙሪያዋ ነዋሪዎች ከባድ የእህልና ገንዘብ መዋጮ በግዴታ እየጠየቅን ነው ሲሉ አማረሩበፌደራል መንግስትና በህወሃት ኃይሎች መካከል ዳግም ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ስጋት በርካታ ተፈናቃዮች ራያና አላማጣን እየለቀቁ በሚገኙበት በዚህ ወቅት፣ በአላማጣ ከተማና ዙሪያዋ የሚገኘው ማህበረሰብ ለጦርነት ዝግጅት የሚሆን የገንዘብና የእህል መዋጮ በግዴታ እንዲከፍል እየተገደደ መሆኑን ነዋሪዎችና አርሶ አደሮች ገለፁ።...more4minPlay
August 26, 2026የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ለጨረታ ያቀረበው ከፍተኛ መጠን ያለው ዶላር እና የኢኮኖሚው ፍላጎት አንድምታከፍተኛ መጠን ያለው ዶላር ቀርቦ ብር የዶላር ተመን ይወርዳል ተብሎ ቢገመትም ያ አለመሆኑ የፍላጎቱ ጣሪያ መንካትን የሚሳይ ብለዋል የገንዘብ አስተዳደር ባለሞያው። ባንኮች በተለይም ከወርቅ ግዢ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ገንዘብ ስላከማቹ በቀላል የማይገኘውን ዶላር የመግዛት አጋጣሚ ሲያገኙ ገዝተው በማስቀመጥ ለደንበኞቻቸው ማቅረብ ይፈልጋሉም ብለዋል፡፡...more0minPlay
August 26, 2026የአፍሪካ ህብረት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለማደስ እየጣረ ነውን?የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልክተኛው የመቀሌ ጉብኝትን ተከትሎ ትናንት ማክሰኞ ነሃሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ይፋዊ መግለጫ ያወጡት የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የኦባሳንጆ ጉብኝት “ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት ጋር ለመደራደር የሚያስችል ይዞ የመጠው አዲስ ምክረሃሳብ ወይም ተጨባጭ እምርታ የለውም” ብለዋል፡፡...more4minPlay
August 26, 2026የኦባሳንጆን የመቀሌ ጉብኝት በበጎ እንደሚመለከተው የአሜሪካ ኤምባሲ ገለፀየናይጄሪያ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ሰኞ ዕለት በመቀሌ ያደረጉትን ጉብኝት በበጎ እንደሚመለከተው በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ገልጿል።የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ "የሁሉም መሪዎች ዓላማ መሆን አለበት" ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ "ይህንን ለማሳካት የሁሉም ወገኖች መግባባትና መደራደር ያስፈልጋል" ብሏል።...more5minPlay
August 25, 2026ኦባሳንጆ ትናንት መቀሌን ድንገት መጎብኘታቸዉን የትግራይ ክልል አስታወቀየትናንቱን የኦባሳንጆን ጉብኝት ተከትሎ ክልሉ "ትርጉም ያለው፣ ታማኝ፣ ግልጽና ተጨባጭ፣ የጊዜ ገደብ የተቀመጠለት፣ በዓለም አቀፍ አጋሮች የሚደገፍ የሰላም ውይይት ለማድረግ በማንኛውም ጊዜና ኹኔታ ዝግጁ መሆኑ" ተገልጿል።...more0minPlay
August 25, 2026በአቤዶንጎሮ ወረዳ በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ቅሬታበምዕራብ ኦሮሚያ ባለፉት 3 ዓመታት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤዶንጎሮ እና አሙሩ ወረዳ፣ ከምስራቅ ወለጋ ዞን ደግሞ ኪረሙ እና ጊዳ አያና ወረዳዎች ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት የደረሰባው ወረዳዎች ናቸው፡...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.