Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.
August 28, 2026በአፋር ክልል የዝናብ መቅረትና የቀረጥ ጭማሪ አርብቶ አደሩን ፈትኖታልበአፋር ክልል ባለፈው አንድ ዓመት በቂ ዝናብ ባለመገኘቱ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ በአርብቶ አደሮችና እንስሳቶቻቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። በተለይም በዳሊፋጌ እና በያንጉዲ ወረዳዎች የውሃና የመኖ እጥረት በመከሰቱ በርካታ አርብቶ አደሮች አካባቢያቸውን ለቀው ወደ አዋሽ ተፋሰስ በመሰደድ ላይ ናቸው።...more0minPlay
August 28, 2026በኦሮሚያ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ምስራቃዊ ወረዳዎች ጥቃትበኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቀርሳ ማሊማ ወረዳ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ታጣቂዎች አደረሱት በተባለው ጥቃት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡ በወረዳው ማክሰኞ ማለዳውን ተጀምሮ ቀኑን ውሎበታል በተባለው የታጣቂዎቹ ጥቃት ቢያንስ በአንድ ቀበሌ ብቻ ሰባት ሲቪል ሰዎች ስለመገደላቸው የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡...more4minPlay
August 28, 2026በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ያስመዘገበው ጃለል ግርማጃለል ግርማ ጎበዝ ተማሪ እንደሆነ አስቀድሞ ያውቀዋል። ጥሩ ውጤት እንደሚያመጣም ጠብቆ ነበር። ያልገመተው ነገር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ውጤት እንደሚያስመዘግብ ነው።...more0minPlay
August 28, 2026ፍርድ ቤት የቀረቡት የኢሕአፓ አባል ፖለቲከኞች ተቀጠሩ"በአገር ማፍረስ ሴራዎች" ተጠርጥረው በእሥር ላይ የሚገኙትና ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት የኢሕአፓ አባል ፖለቲከኞች እና ጠበቃ ለቀጣዩ ሐሙስ ነሐሴ 28 ቀን ተቀጠሩ። ኢሕአፓ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለኢሰመኮ ጉዳዩን በደብዳቤ ያሳወቀ መሆኑን ገልጾ "ኹኔታው ተጣርቶ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥያቄ አቅርቧል።...more3minPlay
August 28, 2026የመቀሌ የሰላም ናፍቆትትዝታዋ፣ ፍቅሯ ከናፍቆት ጋር በዜማና በጽሑፍ የተነገረላት መቀሌ፣ ከዓመታት የጦርነት ቁስል በኋላ ዳግም በጦርነት ስጋት ውስጥ ገብታለች። የከተማዋ ነዋሪዎች የዕለት ኑሮ፣ የንግድ እንቅስቃሴ፣ የወጣቶች ተስፋ ሌላ መልክ ይዟል።...more0minPlay
August 27, 2026ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገራት ብሔራዊ ምክክር የትኛዉን ተሞክሮ ትዉሰድ?ኢትዮጵያዉያን ያካሄዱት ምክክር የሃገሪቱን የኃይል ፖለቲካ ወደ ዉይይት ባህል፤ ወደመደማመጥ ባህል ያመጣ ከፍተኛ ለዉጥ ነዉ ብለዉ ያስባሉ? የተገኙት የመፍትሄ ሃሳቦች በቀጣይ ተግባራዊ እንዴት ተግባራዊ ይደረጋሉ? በአፍሪቃ የትኞቹ ሃገራት ብሔራዊ ምክክርን አካሄዱ? የትኞቹ ተሳካላቸዉ? የትኞቹ ሃገራትስ አልተሳካላቸዉም? የትኛዉን ተሞክሮ እንዉሰድ?...more0minPlay
August 27, 2026በአፍሪካ የሰላም አስከባሪዎች ይበልጥ ለጥቃት እየተጋለጡ ነው መባሉሰሞኑን በደቡብ ሱዳን በሚገኙ የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪዎች ላይ የተፈፀመውና ኹለት ኢትዮጵያውያን ወታደሮች የተገደሉበት ጥቃት፣ በሀገሪቱ እየተፈፀሙ ያሉ በርካታ ጥቃቶች አካል መኾኑን አንድ ከፍተኛ የፀጥታ ጉዳዮች ተመራማሪ ገልፀዋል። በተለይ በሰብአዊ ድጋፍ ላይ የሚሰሩ አለምአቀፍ ሰራተኛችም ብዙ ጥቃት ደርሶባቸዋል።...more0minPlay
August 27, 2026የትግራይ ዳያስፖራ ድርጅቶች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ምን አሉ?የትግራይ ማኅበረሰብ ዳያስፖራ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ፣የተባበሩት መንግስታት፣ የአፍሪቃ ህብረት፣ የአውሮፓ ህብረት እና ሌሎች የሚመለከታቸው መንግስታትን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የድሮን ጥቃቱን በአስቸኳይ ለማስቆም፣ያለምንም መዘግየት እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል።...more0minPlay
August 27, 2026የአውሮጳ ሕብረት እና ሀገራት ለሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም ያደረጉት ጥሪበኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ኅብረት የሚገኙት የአውሮፓ ኅብረት ልዑካን እና የሀገራት ኤምባሲዎች በትግራይ ክልል እንደገና የጦርነት ግጭት ከተከሰተ ለአካባቢው ሕዝቦች "አስከፊ ውጤት" እንደሚያስከትል ገለፁ።...more0minPlay
August 27, 2026የሀገራዊ ምክክር መጠናቀቅ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክረሃሳብየኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ትናንት በሰጠው መግለጫ፣ የሀገራዊ ምክክሩ ምክረ ሐሳቦችን አተገባበር የሚከታተል "ገለልተኛ እና ሕጋዊ" ያለው አካል አንዲቋቋም" ጠይቋል። መኢአድ በመግለጫው በጉባኤው "ሊነሱና ሊነካኩ የማይገባቸው" ያላቸው አጀንዳዎች እንደነበሩ ጠቅሶ ይህም አደጋ የሚያመጣ መሆኑን ገልጿል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.