Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 596 episodes available.
July 30, 2025የኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሪ ሥርዓት ለውጥ በዓመቱ ምን አሳካ?የኢትዮጵያ መንግሥት የውጪ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ ካደረገ ወዲህ የሸቀጦች የወጪ ንግድ እና ሐዋላን ጨምሮ ሀገሪቱ 32 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። በለውጡ ብር ዶላርን ከመሳሰሉ የመገበያያ ገንዘቦች ያለው የምንዛሪ ተመን እየተዳከመ ሲሔድ እንደ ነዳጅ ያሉ ሸቀጦች ዋጋ እየጨመረ የሸማቾችን አቅም እየተፈታተነ ይገኛል።...more12minPlay
July 30, 2025በሰውሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረቱ መተግበሪያዎች እና የውሂብ ግላዊነት ስጋትሰው ሰራሽ አስተውሎት የዕለት ተዕለት ሕይወታችን አንድ አካል እየሆነ መጥቷል።ይህንን ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥርም በፍጥነት እያደገ ነው።ለምሳሌ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተው ቻትጂፒቲ ከ122 ሚሊዮን በላይ ዕለታዊ ተጠቃሚዎች አሉት።ያም ሆኖ ባለሙያዎች በዚህ ቴክኖሎጂ ላይ የግል መረጃ ደህንነት ስጋት መኖሩን ያስጠነቅቃሉ።...more11minPlay
July 30, 2025አብን ለመንግሥትና የፖለቲካ ኃይሎች ያቀረበው የሰላም ጥሪበአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎችና ባለድርሻ አካላት አገራዊ መግባባትንና ዘላቂ መፍትሔዎችን እንዲያመጡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠየቀ። በአማራ ክልል ያለው የፀጥታ ችግር ተባብሶ መቀጠሉንም ንቅናቄው አመልክቷል።...more4minPlay
July 30, 2025ናዳ ያስከተለው ስጋት ሺህዎችን ከመኖሪያ አካባቢያቸው ማስለቀቁበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ደቡብ ኣሪ ወረዳ የተከሰተውን የመሬት መሰንጠቅ ተከትሎ ከአንድ ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከአካባቢው እንዲለቁ መደረጉን የወረዳው መስተዳድር አስታወቀ።...more4minPlay
July 30, 2025በሶማሌ ክልል የአስተዳደር መዋቅር፤ የቀጠለው የፓርቲዎች እና ሕዝብ ተቃውሞከሰሞኑ በሶማሌ ክልል የተደረገውን አዲስ የወረዳዎች መዋቅር የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ነቀፈ። ኦፌኮ «ኢ-ሕገመንግሥታዊ» ያለው የአስተዳደር መዋቅር ለውጥን በመቃወም ጉዳዩ በውይይት እና በመከባበር ብሎም በሕጋዊ መንገድ መልስ በመስጠት ግጭት እንዳይፈጠር አበክሮ መሥራት ይገባልም ብሏል።...more4minPlay
July 30, 2025ሕግ አውጭዎች የሲቪል ድርጅቶች ማሻሻያ ረቂቅ ሕግን ውድቅ እንዲያደርጉ ተጠየቀመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ሥራ ይገድባል ያለው የሲቪል ድርጅቶች ረቂቅ ማሻሻያ በሕግ አውጭዎች ውድቅ እንዲደረግ ሂዩማን ራይትስ ዎች ጠየቀ።...more4minPlay
July 30, 2025የሶማሌ ክልል ምክር ቤት በአዲሱ የወረዳዎች አደረጃጀት ውሳኔየሶማሌ ክልል ምክር ቤት ከትናንት በስተያ ባጠናቀቀው ጉባዔ ላለፉት ዓመታት በሕዝብ ቅሬታ ሲቀርብባቸው ነበር ባላቸው 14 ወረዳዎች አደረጃጀት ላይ ተጠናቆ የቀረበውን ጥናት አጽድቋል።...more5minPlay
July 29, 2025የአማራ ክልል 10ኛ መደበኛ ጉባኤና የክልሉ ሠላምበክልሉ የተፈጠረውን ጦርነት መቀልበስ ተችሏል ያሉት አረጋ ከበደ፣ ሆኖም አሁንም በክልሉ ሙሉ ሠላም ለማምጣት መተባበር እንድሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡“ዘላቂ ሠላም ለማምጣት ታጠቀው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከጠመንጃ ይልቅ በሀሳብ የበላይነት በውይይትና በንግግር እንዲያምኑ ሁላችንም የበኩላችን ጥረት አጠናክረን መቀተል ይኖርብናል፡፡” ብለዋል፡፡...more5minPlay
July 29, 2025የሐገር ሽማግሌዎችና የትግራይ ክልል ፖለቲከኞች ዉይይትከኢትዮጵያ 12 ክልሎች እና 2 የከተማዋ አስተዳደሮች የተወከሉ 50 የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ትላንትና ዛሬ ከክልሉ የአስዳደር አካላት፣ የተለያዩ ፓርቲ ፖለቲከኞች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ሌሎች የተወያዩ ሲሆን ዋና አጀንዳቸውም ሰላም ማፅናት ላይ ማድረጋቸው ተገልጿል።...more3minPlay
July 29, 2025የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ የአስመራን መንግሥት በትጥቅ ለመታገል ዝግጅት ላይ ነኝ አለ"የኤርትራ አፈር ብሔራዊ ጉባኤ" የሥራ አስፈጻሚ አባል እና ቃል ዐቀባይ አሊ መሐመድ ዑመር ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ አፋር ክልል ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መቀመጫውን ካናዳ ካደረገ ካን-ጎ አፋር ከተባለ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ጅቡቲ ውስጥ ያለውን አፋር ታሪኩን---...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 596 episodes available.