Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.
June 22, 2026የሰኔ 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባከአዲስ አበባ ስታዲየም ሜዳ ያቋረ ውኃን በመወልወያ እና ባልዲ ለማስወገድ የተጣረበትን አስደማሚ ክስተትም በተመለከተ ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። በዋናነት የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ዳሰሳ እንአደርጋለን ። ተጨማሪ የስፖርት መሰናዶ አካተናል ። ሙሉ ዘገባውን በድምፅ እና በጽሑፍ በማገኛው በኩል መከታተል ይቻላል ።...more0minPlay
June 22, 2026ዘጋቢዬ ከኢትዮጵያ የተባረረችበት ሂደት ተገቢ አልነበረም፤ ላ ክሮዋ ጋዜጣታዋቂው የፈረንሳዩ ጋዜጣ ላፑዋ በቅርቡ ዘጋቢው ኦገስቲን ፓስሊ ከኢትዮጵያ የተባረረችበት ሁኔታ አግባብ አልነበረም ሲል ወቀሰ። የጋዜጣው የዝግጅት ክፍል ለዶቼ ቬለ እንዳለው የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በጋዜጠኛዋ ላይ የወሰዱት ርምጃ የፕሬስ ነጻነት ጥሰት የፈጸመ ነው ሲል ከሷል።...more0minPlay
June 22, 2026በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና 19 የክልል መቀመጫዎች አሸነፉበ7ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተቃዋሚዎች 19 የክልል ምክር ቤት እና አንድ የፓርላማ መቀመጫ አሸንፈዋል፡፡ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዳለው የጉሙዝ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ 14 የክልል እና አንድ የፓርላማ መቀመጫ ሲያሸንፍ የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጸነት ንቅናቄ ድግሞ አምስት የክልል ምክር ቤት መቀመጫ አሸንፈዋል፡፡...more0minPlay
June 22, 2026መቀመጫ ያገኙ ተቃዋሚዎች እና የቀጣዩ ፓርላማ ሚናቸውበ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 17 የፖለቲካ ፓርቲዎች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን ማግኘታቸው በቀጣይ በሚመሠረተው ምክር ቤት ላይ ምን የተለየ ነገር ይዞ ይመጣል ይሆን ?...more0minPlay
June 21, 2026«ብልጽግና ውጤታቸው ከተረጋገጠው 486 የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ወንበሮች 438ቱን አሸንፏል»የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ የምርጫውን ውጤት በገለጹበት ወቅት በምርጫው ወቅት ጉልህ የምርጫ ሕግ ጥሰቶች በተገኙባቸው 23 የምርጫ ክልሎች ላይ ድጋሜ ቆጠራ ወይም ውጤቱ ተሰርዞ ድጋሚ ምርጫ እንዲደረግ መወሰኑን አመልክተዋል፡፡...more0minPlay
June 21, 2026በምርጫው ውጤት ላይ ነዋሪዎች ምን አሉ ?በውጤቱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የክልል እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን እንደተጋሩ መስማታቸው በጎ መሆኑን የጠቀሱት ሁለት አስተያየት ሰጪዎች “ ይህም መንግሥት ክፍተቶቹን ለማየት የሚስችለውን ዕድል ይፈጥራል ፡፡...more0minPlay
June 21, 2026በአርሲ ዞን ጥቃት ግድያው ለምን ተደጋገመ፥ እንዴትስ ይቆማል?ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ይሰነዘራሉ ። በተለይ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ የመገደል የመፈናቀላቸው፣ የቤት ንብረታቸው መዘረፍና መውደም ሰበቡ ምን ይኾን፥ እንዴትስ ይቁም? ሙሉ ውይይቱን በማገኛው በኩል ማድመጥ ይቻላል ።...more44minPlay
June 20, 2026ትኩረት በአፍሪቃ፣ ሱዳን-አል ዑቤይድ ላይ ያጠላዉ ሥጋት፤ የጊኒ ቢሳዉ ቀዉስ ስከዚሕ ዉስጥ ከ14 ሚሊዮን የሚበልጠዉ አንድም ተፈናቃይ ሁለትም ሥደተኛ ነዉ።የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) እና የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ባለሥልጣናት ባገባደድነዉ ሳምንት አጋማሽ እንዳሉት በዓለም በርካታ ሕዝብ ለረሐብ ከተጋለጠባቸዉ 13 ሐገራት ወይም ግዛቶች ግንባር ቀደሟ ሱዳን ናት።...more0minPlay
June 20, 2026የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ ውጤቶችን ይፋ አደረገምርጫ ቦርድ ትናንት ዓርብ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤቶች እጩ አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ቦርዱ ይፋ ካደረጋቸው ውጤቶች መካከል የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ እንዲሁም የቀድሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በግላቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር አሸንፈዋል።...more0minPlay
June 20, 2026በአሜሪካ የእግድ መግለጫ ላይ የሕወሓት ምላሽዩናይትድ ስቴትስ በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አመራሮች እና በቤተሰቦቻቸዉ ላይ ያነጣጠረ የቪዛ እገዳ መጣሏን ማሳወቋን ተከትሎ ሕወሓት መልስ ሰጥቷል።በምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲነት የተሰረዘው ሕወሓት፤ ለአሜሪካው መግለጫ በሰጠው ምላሽ የአሜሪካ የቪዛ እገዳ አድሏዊና ለአንድ ወገን ያደላ ነው ሲል የአሜሪካን መንግስት ውሳኔ ተቃውሞታል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.