Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.
June 20, 2026የአሜሪካው ዲፕሎማት ስቲቭ ዊትኮፍ ከኢራን ጋር ለመነጋገር ወደ ስዊዘርላንድ እያመሩ ነው ተባለየአሜሪካ እና የኢራን ዲፕሎማቶች ለሰላም ድርድር ወደ ስዊዘርላንድ እያመሩ ነው ተብሏል። በሌላ በኩል የፓኪስታን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ዛሬ ወደ ቴህራን አቅንተዋል። በሊባኖስ ደግሞ በእስራኤል እና በሂዝቦላህ መካከል ውጊያው መቀጠሉ ተሰምቷል።...more0minPlay
June 19, 2026በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ የአፍሪቃውያን ቡድኖች እንዴት ይገመገማሉ?በዘንድሮው የዓለም ዋናጫ 10 የአፍሪቃ አገራት ተሳታፊ ሲሆኑ አንዳንዶቹም እስካሁን ጠንካራ የሚባል ግጥሚያ አሳይተዋል። ይሁንና ከ16 ዓመታት በፊት በአፍሪቃ መሬት ላይ የዓለም ዋንጫ ያስተናገደችው ደቡብ አፍሪቃን በአሁኑ ውድድር ብዙ አፍሪቃውያን ድጋፋቸውን ነፍገዋታል።...more11minPlay
June 19, 2026ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰበብ ከአሜሪካ የሚመጣውን ጫና እንዴት ልትይዝ ይገባል?የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የተቋረጠውን የህዳሴ ግድብ ድርድር በኢትዮጵያ እና በግብጽ መካከል እንደገና የማስጀመር ፍላጎታቸውን በድጋሚ ገልጸዋል። ድርድሮቹን በቅርብ የሚያውቁት ፈቂአሕመድ ነጋሽ ትራምፕ “ይኸን ካልተቀበላችሁ ይኸ ይከተላችኋል” እስከ ማለት የሚሔዱ በመሆኑ ጉዳዩ “ከፍተኛ ጥንቃቄ” እንደሚፈልግ ለዶቸ ቨለ ተናግረዋል።...more5minPlay
June 19, 2026አሜሪካ በህወሓት መሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የጣለችው የቪዛ ዕቅባ እና አንደምታውየአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ “አክራሪ” ባሏቸው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላትና በቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ ገደብ ጥለዋል። የግጭትና የዲፕሎማሲ ተመራማሪ ነጋልኝ መኮንን፣ኢትዮጵያ ያለችበትን አጠቃላይ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ያላካተተ ያሉት ይህ የአሜሪካ እርምጃ ውጤት ያመጣል የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልጸዋል።...more5minPlay
June 19, 2026አሜሪካ በህወሓት መሪዎች ላይ የጣለችው የቪዛ እገዳ አንድምታአሚሪካ በህወሓት ላይ የቪዛ ዕገዳ መጣሏን በተመለከተ የወጣው መግለጫ “እንደ ማስጠንቀቂያ ወይም እንደ ማሳሰቢያ የሚቆጠር ነው እንጂ በራሱ ተጨባጭ ውጤት ያለው አይደለም“ ሲሉ የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ዳንኤል ብርሀነ ለዶቸ ቬለ ተናግረዋል። እርምጃውን እንደ “ተግሳጽ“ የሚቆጥሩት ዳንኤል ቢሆንም ዲፕሎማሲያዊ ትርጉም እንደሚኖረው አስረድተዋል።...more4minPlay
June 19, 2026የውክልና መቀመጫ ያገኙ ፓርቲዎች ቀጣይ መንገድበ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተወዳደሩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የፌደራል የህዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤቶች ለመግባት የሚያስችሏቸውን መቀመጫዎች አግኝተዋል ፡፡ በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በአንጻራዊነት የተሻለ ሊባል የሚችል የወንበር ቁጥር መገኘቱ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው የውጤት መግለጫ ላይ ተመልክቷል ፡፡...more4minPlay
June 19, 2026ሥመ-ጥሩው የሙዚቃ ባለሙያ አዲስ ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየከቴዎድሮስ ካሳሁንና እጅጋየሁ ሽባባው ጋር የሠራው የጃኖ ባንድ መሥራች አዲስ ገሠሠ በ73 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ሥመ ጥሩው የሙዚቃ ባለሙያ አዲስ ዚጊ ማርሌይ ኤንድ ዘ-ሜሎዲ ሜከርስ ባንድን ለ24 ዓመታት በማኔጀርነት መርቷል። ኧርዝ ዊንድ ኤንድ ፋየር ከተባለ ታዋቂ የሙዚቃ ባንድ፣ ከፊል ኮሊንስ እና ሎረን ሒል ጋር ሠርቷል።...more3minPlay
June 18, 2026የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች ቁጥር ሻል ብሎ የታየበት የምርጫ ውጤትየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በርካታ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ የሆኑበትን የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።...more5minPlay
June 18, 2026ባህላዊ ክዋኔዎች በሺናሻ ማኅበረሰብበኢትዮጵያ ባሕላዊ የጋብቻ ስርዓት በተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍል ዘንድ የተለመዱና በስፋት ተግባራዊ እየሆኑ የሚገኙ ናቸው ፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚገኘው የሺናሻ ማኅበረሰብ ስምንት የተለያዩ የጋብቻ ስነ ስርዓቶች ያሉት ሲሆን ስርዓቱ ከጥንት ጀምሮ ሲተገበር እንደነበር የብሔረሰቡ የሀገር ሽማግሌዎች ተናግረዋል፡፡...more17minPlay
June 18, 2026የክረምት ወራት የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንበያ ማስጠንቀቂያበክረምት ወራት በምሥራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠን እንደሚጠበቅ ተገለጠ። ይህን ያስታወቀው በኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት የሶማሌ እና አጎራባች ክልሎች የሚትሮሎጂ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸው አስገንዝቧል።...more5minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.