Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.
June 16, 2026የጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይነሳኝ እስርጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይነሳኝ ከሳምንት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሏን ቤተሰቦቿ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።የጋዜጠኛዋ ታናሽ እህት ለዶይቸ ቬለ እንደገለፀችው፤ እህቷ ያለፈው ሰኞ ሰኔ አንድ ቀን፣ 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ በፖሊስ ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ ተብላ ነው የተያዘችው። ያም ሆኖ እስካሁን ፍርድ ቤት አልቀረበችም።...more5minPlay
June 16, 2026የአፍሪካ ኀብረት ጋና ባቀረበችው ጥያቄ ላይ እንደሚነጋገር ይጠበቃልበጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሙኤል ኦኩድዜቶ ኦብላክዋ የተጻፈውና ለአፍሪካ ኀብረት የተላከው ደብዳቤ፣ በደቡብ አፍሪካ ያለውን ኹኔታ በተመለከተ አፋጣኝ አህጉራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ይጠይቃል። በኅብረቱ የሚመራ የእውነት አፈላላጊ ቡድን እንዲቋቋምና ጉዳዩን እንዲመረምርም ያሳስባል።...more4minPlay
June 16, 2026በትግራይ ክልል የወጣው አዲስ ሕግ እና የጦርነት ስጋትየትግራይ ክልል አስተዳደር አርቅቋል ተብሎ እየተገለጸ የሚገኘው አዲስ ሕግ፤ “የትግራይ ሕዝብ ኅልውና እና ደኅንነትን ለማረጋገጥ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ያወጣው አዋጅ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ነው፡፡...more4minPlay
June 16, 2026በሥራ ላይ መዋል የጀመረው አዲሱ የአውሮጳ የፈላስያንና ስደተኞች ሕግየመንግሥታቱ ድርጅት የስድተኞች መርጃ ድርጅት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ዛሬ በዓለማችን ክ136 ሚሊዮን በላይ ሕዝቦች ተስድደው መንግሥት አልባ መኾናቸውን ይጠቁማሉ። ጦርንት፤ ድህነት፤ የተፈጥሮ አደጋዎችና የአገዛዝ ሥራቶች ዋናዎቹ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንዲፈናቀሉና እንዲስደዱ የሚያደርጉ ምክንያቶች መሆናቸው ይታመናል።...more10minPlay
June 16, 2026ተደጋጋሚ ማዛጋት(ማፋሸክ) ለምን ይከሰታል?ማዛጋት እንደማስነጠስ ሁሉ ልንቆጣጠራቸው ከማንችላቸው የተፈጥሮ ክስተቶች አንዱ ነው። የህክምና ባለሙያዎች ማዛጋት ሰውነት ሲደክምና አዕምሮ ሲከብደው በተፈጥሮ ስርዓት እራሱን የሚያነቃቃበት ስልት ነው ይሉታል።...more11minPlay
June 15, 2026ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ሥምምነት-የሠላም ጭላንጭል ብርቀትየዓለም ምርጥ፣ ጠንካራ፣ ዘመናይ ጦር መሳሪያ የታጠቁት የሁለቱ ሐገራት ጦር ኃይላት በማዕቀብ፣ መገለልና ተደጋጋሚ ጦርነት የተዳከመች በመሰለችዉ ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ግን ከመካከለኛዉ ምሥራቅ አልፎ ከሰርቢያ እስከ ኢንዶኔዢያ፣ ከፊሊፒንስ እስከ ፈረንሳይ የሚገኙ ሐገራት ዜጎችን ገድሏል።...more0minPlay
June 15, 2026የሰኔ 8 ቀን፣ 2016 ዓም የስፖርት ዘገባተጠባቂው የዓለም ዋንጫ በድምቀት ተጀምሯል ። የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን እስካሁን ከተደረጉ ግጥሚያዎች በአጠቃላይ በአንድ ጨዋታ በርካታ ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ ቀዳሚ ብሔራዊ ቡድን ኾኗል ። አትሌቲክስ እና ሌሎች ዘገባዎችንም አካትተናል ።...more0minPlay
June 15, 2026የኢራን አሜሪካ ስምምነትዩናይትድ ስቴትስና ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ተባብሶ የከረመውን ጦርነት ለማስቆም ያስችላል ከተባለው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ይፋ አድርገዋል። አደራዳሪዋ ፓኪስታንም ይህንኑ አረጋግጣለች።...more0minPlay
June 15, 2026የጡት ወተት ባንክ ምንድን ነው?የጤና አገልግሎት ጥራትን ለማስጠበቅ በ2.8 ቢሊየን ብር ወጪ ትናንት በሀዋሳ ለምረቃ ከበቁት ፕሮጀክቶች መካከል የጡት ወተት ባንክ ይገኙበታል። በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለው የጡት ወተት ባንክ የጨቅላ ሕጻናትን ሞት ምጣኔ ለመቀነስ እንደሚያግዝ ነው በምረቃ ስነሥርዓቱ ላይ የተጠቀሰው።...more0minPlay
June 15, 2026የቱለማ አባገዳ ሥልጣን ሽግግር እና የቀጣዩ አባገዳ ፈተናበየስምንት ዓመቱ የሚፈጸመው የቱለማ አባገዳ የሥልጣን ሽግግር ሰኔ 07 ቀን 2018 ዓ.ም. «ዳካ ኮራ» በተባለ ከአዲስ አበባ ቅርብ ርቀት ላይ ተካሄደ። በሥልጣን ሽግግሩ ላለፉት ስምንት ዓመታት የቱለማ ኦሮሞ አባገዳ በመሆን ያገለገሉት አባገዳ ጎበና ሆላ ለአዲሱ ተሿሚ ጌቱ ተሊላ አላንጌ በመስጠት የቀድሞ አባገዳ ለመባል በቅተዋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.