Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.
June 12, 2026„ሰው ስለ እኔ ብዙ ያወራል“፤ በረንዳ ላይ ቡና የሚያፈላው ሳሙኤልኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሰዎች ስለ ባህላዊው የጀበና ቡና አፈላል ሲያስቡ ፤ አዕምሮዋቸው ውስጥ ቶሎ የሚስሉት አንዲት ሴት ስታፈላ ነው።የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንግዳ በዚህ ስራ የተሰማራ ወንድ ወጣት ነው። „ስራው መንገድ ዳር ከመለመን ቢሻልም ብዙ ፈተና አለው“ ይላል። በተለይ ወንድ በመሆኑ ሰዎች እንደሚስቁበት ይናገራል። ፈተናው ይህ ብቻ አይደለም!...more0minPlay
June 11, 2026ዛሬ ሜክሲኮ የሚጀመረው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ግጥሚያ ዝግጅትና ተግዳሮቶችጨዋታዎቹ የሚጠናቀቁት ከስድስት ሣምንታት ግድም በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ ኒው ጄርሲ ከተማ ውስጥ በሚደረገው የፍጻሜ ግጥሚያ ነው ። የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በተለይ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በቪዛ ችግር በርካታ የጉዞ መሰናከል መፈጠሩ ቢነገርበትም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ግን 13 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ይገኝበታል ተብሎ ይጠበቃል ።...more0minPlay
June 11, 2026የሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ ስራዎች በፍራንክፈርት ጀርመን«ከህክምናዉ ዉጭ ባለኝ ጊዜ የስዕል እግዚቢሽን ለማድረግ እየሰራሁ ነዉ።» በጽናት ተምሳሌትነቱ በኢትዮጵያዉያን ዘንድ የሚታወቀዉ ብሩክ የሺጥላ፤ በፍራንክፈርት ስዕሎቹን ለእይታ አቅርቧል። በርካታ ኢትዮጵያዉያን ተገኝተዉ ነበር። ብሩክ ወደ ጀርመን የመጣዉ ለህክምና የጉልበት ነቀላ ተከላ ህክምናን ለማካሄድ ነዉ።...more0minPlay
June 11, 2026የኢትዮጵያውያውን ሰቆቃ በደቡብ አፍሪቃምንም እንኳን የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከሕግ በላይ ሆነው በስደተኞች ላይ እርምጃ የሚወስዱትን እነዚህን የተደራጁ ቡድኖች ባለሥልጣኖቻቸው እንደማይታገሱ ባለፈው እሁድ ቢያሳስቡም የተቃውሞ ሰልፎችን ማካሄዳቸው ስደተኞችን ማጥቃት መዝረፋቸው ቀጠለ እንጂ አልቆመም ሲሉ ደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።...more0minPlay
June 11, 2026ሰቆጣ የሚገኙ የዋግህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጻግምጅ እና አበርገሌ ወረዳዎች ተፈናቃዮች ለረሀብ ተጋልጠናል ሲሉ ተናገሩከዋግምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጻግምጅ እና አበርገሌ ወረዳዎች በግጭት ወደ ሰቆጣ ከተማ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች፣ የምግብ እርዳታ ባለማግኘታቸው ለከፍተኛ ረሃብና እንግልት መጋለጣቸውን ተናግረዋል።ከአበርገሌ ወረዳ ተፈናቅለው ወደ ሰቆጣ ከተማ የመጡት አስተያየት ሰጪም ከሰሞኑ የምግብ ማብሰያ ቁሳቁስ እና የብርድ ልብስ ቢሰጣቸውም ምግብ ግን አላገኙም።...more0minPlay
June 11, 2026የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውጤቶችና እያሳወቀ እና ቅሬታዎችንም እያጣራ ነውየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ ከተካሄደባቸው 1 ሺህ 139 የምርጫ ክልሎች በ120 የምርጫ ክልሎች ላይ በፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል እጩ ተወዳዳሪዎች ቅሬታ እንደቀረበለት አስታወቀ፡፡ በስምንት የምርጫ ክልሎች ላይ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ቅሬታ ማቅረቡን ጎጎት ፓርቲ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡...more0minPlay
June 11, 2026የኤቦላ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ የቅኝት ስራዎች እንዲጠናከሩ ተጠየቀአፍሪካ ሲዲሲ ባወጣው መረጃ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ። በኮንጎና በዩጋንዳ ለተከሰተው የኢቦላ ቫይረስ ይበልጥ ተጋላጭ ሊኾኑ ይችላሉ ያላቸውን 10 የአፍሪካ ሃገራት ዘርዝሯል። የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሃገራቸው ኢቦላን ለመከላከል በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እያከናወነች መሆኑን የአፍሪቃ ሲዲሲ ሃላፊ በተገኙበት ጉብኝት ላይ ተናግረዋል።...more0minPlay
June 11, 2026የሁለት የኢትዮጵያ መንግሥት የልማት ድርጅቶች የውጭ ዕዳ ክፍያ በ2019 የበጀት ረቂቅ ውስጥ ተካተተከኢትዮጵያ የ2019 መደበኛ በጀት ውስጥ 43.8% ወይም 542 ቢሊዮን ብር ለዕዳ ክፍያ ተመድቧል። ብድር መክፈል ያቃታቸው ሁለት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የውጭ ዕዳ ክፍያ በበጀቱ ውስጥ ተካቷል። ለበቅርቡ የሥራ ጊዜውን ለሚያጠናቅቀው ሕግ አውጪ ምክር ቤት የቀረበው የ2.34 ትሪሊዮን ብር በጀት ከ300 ቢሊዮን ብር በላይ ጉድለት ይገጥመዋል።...more0minPlay
June 10, 2026ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየው የዘንድሮ የኢትዮጵያ በጀትና አንድምታውየኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የ2019 ዓ.ም. የፌደራል መንግሥት የበጀት ረቂቅ ላይ ከተወያየ በኋላ ከ 2.3 ትሪልዮን ብር በላይ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ አፅድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት መላኩን አስታውቋል።...more4minPlay
June 10, 2026ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ ከፈቀደው ብድር 200 ሚሊዮን ዶላር አስቀድሞ ሊለቅ ነውአሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን የገጠሙት ጦርነት ያሳደረውን ተጽዕኖ ኢትዮጵያ እንድትቋቋም አይኤምኤፍ (IMF) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከፈቀደው ብድር ውስጥ 200 ሚሊዮን ዶላር አስቀድሞ እንዲለቀቅ ታቅዷል። ገንዘቡ የተራዘመ ብድር አቅርቦት መርሐ-ግብር አምስተኛ ግምገማ ሲጸድቅ ከሚለቀቀው 468 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ የሚካተት ነው።...more11minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.