Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.
June 08, 2026ወሎ፤ መጠለያ ጣብያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ድምፅ ሊሰጡ ነዉበ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ ያልሰጡ በሰሜንና ደቡብ ወሎ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ነገ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉበት ሆነው በልዩ ሁኔታ ድምፅ ሊሰጡ ነው። ተፈናቃዮቹ መምረጥ በመቻላቸው መብታቸው መከበሩ ቢያስደስታቸውም፣ ስለሚመርጧቸው እጩዎችና ፓርቲዎች በቂ ግንዛቤ እንዳልተሰጣቸው ገልጸዋል።...more4minPlay
June 08, 2026ማሕደረ ዜና፣ የድርድር መሐል ጦርነት፣ የጦርነት መሐል ድርድር---ዜሮ ዉጤትደቡባዊ ሊባኖስን የሚያወድመዉ የእስራኤል ጦር ድብደባ ወይም ጦርነት-ይባል ግጭት የመጫሩ ምክንያት በኢራን ላይ ጦርነት በመከፈቱ ከሆነ የኢራኑ ጦርነት ሲቆም የሊባኖሱ ያልቆመበት ምክንያት ከተጠየቀ-ትክለኛዉ መልስ «በጡንቻዉ የታበየን ማንጠይቆት» የሚል ነዉ-የሚሆነዉ...more12minPlay
June 08, 2026ኢሰመኮ - አርሲ ዞን የተፈፀመዉን ጥቃት ክትትል እና ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገለፀበኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ ከሳምንት በፊት የተፈጸመው የንጹሃን ግድያን በተመለከተ መንግሥት ተገቢውን ምርመራ በማካሄድ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጥ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ፡፡ ኢሰመኮ መንግስት ተጎጂዎችን ለመካስና ለማቋቋም የሚያስችሉ እርምጃዎችን ሊወስድ ይገባልም ብሏል፡፡...more5minPlay
June 08, 2026ዓረና ትግራይ - «የትግራይ ክልል ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል»በትግራይ ክልል ሸራሮ ከተማ አቅራብያ በደረሰ ጥቃት ታጣቂዎች መገደላቸዉን አንድ የትግራይ ክልል ፖለቲከኛ ተናገሩ። የዓረና ትግራይ ለሉዓላዊነት እና ለዴሞክራሲ ሊቀመንበር ለዶቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ አካባቢዉ ላይ የሻብያ የፋኖ እና የህወሓት ታጣቂዎች እንቅስንቃሴ በመበራከቱ ጥቃቱ ተፈፅሟል ሲሉ ተናግረዋል።...more6minPlay
June 08, 2026የሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባያሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ መድረኮች ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ የበራበትና የአትሌቶቻችን የበላይነት የታየበት ሆኖ አልፏል። በሩሲያ እና በኢጣሊያ በተደረጉ ታላላቅ ውድድሮች ላይ አትሌቶቻችን ድንቅ ስኬት አስመዝግበዋል።በሌላ በኩል እንደ አውሮፖውያኑ አቆጣጠር 2026 የሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ሀሙስ ይጀምራል።...more9minPlay
June 08, 2026የሰሜን ኢትዮጵያው የጦርነት ስጋትበትግራይ ክልል ሸራሮ ከተማ አቅራቢያ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት“የፕሪቶሪያ ስምምነትን”የሚጥስ ተግባር ማሳያ ነው ሲል ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት)የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስትን እየከሰሰ ነው። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት በፊናው በሰሜን ኢትዮጵያ “ጽምዶ” በሚል የተቀነጀ ያለው ኃይል የውጪ ኃይሎች አላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ ነው፡፡...more4minPlay
June 07, 2026ዉይይት፤ ቅድመ ምርጫ፣ ምርጫ እና ድኅረ ምርጫ በጋዜጠኞች ዕይታባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ በኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተካሂዷል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው በዚህ ምርጫ ፤ዋዜማው፣ የምርጫው ዕለት እና ድህረ ምርጫ በጋዜጠኞች ዕይታ ምን ይመስላል።?7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ፤ ከዘገቡ የዶቼ ቬለ ጋዜጠኞች መካከል አራቱን አነጋግረናል።...more43minPlay
June 06, 2026ሶማሊያ ወዴት?ሶማሊያ በያዝነው ወር ሊካሄድ የሚገባ ምርጫ በአንድ ዓመት መራዘሙን ተከትሎ ተቃውሞና ተኩስ ዋና መዲናዋን እያናወጠ ነው። ረቡዕ ዕለት በዋና ከተማ መቃዲሾ ተኩስ የተከፈተ ሲሆን የቀድሞው የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን አሊ ካይሬ በመንግሥት ኃይሎች ጥቃት እንደተሰነዘረባቸው ተናግረዋል።...more0minPlay
June 06, 2026የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድህረ ምርጫው አስተያየቶችየዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን አቀራረብን በተመለከተም የሂደቱ ፈተና ነበሩ ያለው ኢዜማ፤ የምርጫ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ቅቡልነት እንዳይኖረውና በምርጫ የሚመሠረት መንግሥት እንዳይኖረን በማድረግ በጎረቤት ሀገራት ጭምር እንደታየው መንግሥት አልባ ሀገር በማድረግ ከብሔራዊ ጥቅማችን ተቃራኒ የቆመ ተግባር አሳይተዋል ሲል ተችቷል።...more5minPlay
June 06, 2026በኬንያ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የልጆች መጥፋት ጉዳይኬንያ ውsseጥ የልጆች መጥፋት ጉዳይ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። ፖሊስ ጉዳዩን የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጋነውታል ባይ ነው። ቤተሰቦች ግን ችግሩ በእነሱ ብቻ እንደማያበቃ በመግለጽ ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ ጥሪ አቅርበዋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.