Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.
June 06, 2026«የምግብ ዕርዳታ ያለህ» የተፈናቃዮች ሮሮ«ወደ አራት ወራችን እኮ እየገባን ነው ረመዳን እንደገባ በአምስት ተረዳን ከዚያ ወዲህ እኮ የለም። እንደው ወደ ሀገራችንም አሁን ቢወስዱን እንደው ይሻለን ነበር እዛው ሞት ጋር መታገል ይሻላል ረሀብ ጋር ከምትታገል? ያ ይሻል ነበር።»...more0minPlay
June 05, 2026የምርጫ ሕግ ጥሰዋል የተባሉ በእሥራት ተቀጡበደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቡርጂ እና ጌዴኦ ዞኖች ምርጫ ሲያጭበረብሩ ተደርሶባቸዋል የተባሉ የምርጫ አስፈጻሚና መራጭ ከስድስት እስከ አሥር ወር በሚደርስ እሥራት ተቀጡ ፡፡ አስፈጻሚው ቅጣቱ በፍርድ ቤት ሊወሰንበት የቻለው ለመራጮች በተዘጋጀው የድምፅ መስጫ ቅጾች ላይ አስቀድሞ በሚደግፈው እጩ ተወዳዳሪ ላይ ምልክት አድርጎ በመገኘቱ ነው፡፡...more4minPlay
June 05, 2026በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምጻቸውን የሰጡ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ከምርጫ ምን ይጠብቃሉ?ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በአሳለፍነው ሰኞ ግንቦት 24 ሲከናወን በልዩ ልዩ ምክንያት ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል በመጠለያና ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ድምፅ ሰጥተዋል። እነርሱ በፈቃዳቸው የሰጡት እያንዳንዱ ድምፅ ወደ ትናንት ሰላማዊ ኑሮ እንደሚመልሳቸውም ያስባሉ።...more0minPlay
June 05, 2026ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች ምን ይላሉ?በአንድ ሀገር ላይ ምርጫ ሲካሄድ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ድምፃቸውን ከማይሰጡባቸው ምክንያቶች ውስጥ ይወክለኛል የሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ሳይኖር ሲቀር ፣ ብዙም የፖለቲካ ግንዛቤ ሳይኖራቸው ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ ሰሞኑን በኢትዮጵያ እንደተስተዋለው፤ ሀገራቸው ውስጥ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ጨርሶ በአካባቢያቸው ምርጫ ሳይካሄድ...more10minPlay
June 05, 2026«አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ይቁም» ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ« እኔ ሞቼ እናቴ እሚያነሳት አጥታ ሐዘን ውስጥ እንደምትኖር እያወቅኩኝ፤ እኔ እግሬን ተቆርጬ እሚያነሳኝ አጥቼ ጎዳና ላይ ወጥቼ እንደምለምን እያወቅኩኝ፤ አገሬ ከታገለላት ያውደለደለን እንደምታኖር እያወቅኩኝ፤ መሞቴ እኮ አይቀርም፤ ግን ! እናቴን አሳዝኜ ጎረቤትን ለማስደሰት አልሞትም!»...more6minPlay
June 05, 2026በሶማሌ ክልል በምርጫው የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየትየምርጫውን ሂደት አስመልክቶ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ ከሰጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) እና የሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ተወካዮች ምርጫው ሰላማዊ እንደነበር ጠቅሰው በየምርጫ ጣቢያዎች በወጡ ጊዜያዊ ውጤቶች መሠረትም ጥሩ ውጤት ማምጣታቸውን ተናግረዋል። #ምርጫ2018 #EthiopiaElection2026...more5minPlay
June 05, 2026መንግስት አፋጣኝ ጸጥታን በማስከበር ዘላቂ መረጋጋት እንዲያመጣ ተጠየቀዘጠኝ ሲቪል ዜጎች እና ሁለት የመንግስት ጸጥታ ሃይሎች በደለታ ጨፋ ቀበሌ በእሁድ እና ሰኞው ጥቃት መገደላቸውን የሚያረጋግጡት አስተያየት ሰጪው የግጭቱ ሰለባ፤ አሁን ላይ በርካታ ዜጎች በሱንቴ ቅድስት ማሪያም እና እሬቻ ቅዱስ ሚካኤል ቤትክርስቲያን እንደተጠለሉ ናቸው ብለዋል፡፡...more5minPlay
June 05, 2026በሆለታው ችሎት ስለተፈጸመው ግድያ በቦታው ከነበሩ የተጎጂ ጠበቃ አንደበትበሃብት ክፍፍል ሙግት ላይ የነበሩት የቀድሞ ባልና ሚስት ጋብቻቸውን በፍርድ ቤት አፍርሰው አሁን ላይ በተለያዩ ቤቶች እየኖሩ የነበሩ መሆኑንም አክለው የገለጹት የከሳሽ ጠበቃው፤ በርካታ ቤተሰብ አብረው ያፈሩ ትልልቅ ሰዎች እንደነበሩም ገልጸዋል፡፡...more5minPlay
June 04, 2026የዓለም የገንዝብ ድርጅት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ገንዘብ ሊለቅ ነውየዓለም የገንዝብ ድርጅት (IMF) ለኢትዮጵያ 468 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለመስጠት በመሪዎች ደረጃ ላይ ከስምምነት ላይ መድረሱን ይፋ አድርጓል።...more0minPlay
June 04, 2026ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አስተያየትበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ በሁሉም አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ መካሄዱን በክልሉ ስምንት ፓርቲዎችን ያቀፈው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.