Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.
May 31, 2026የድሬደዋ እና የሐረር ነዋሪዎች ስለ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ምርጫከኢትዮጵያ ሁለት የከተማ አስተዳደሮች አንዷ የሆነችው ድሬደዋ ሁለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ነገ ሰኞ ድምጽ ይሰጥባቸዋል። በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የሐረሪ ክልል በተመሳሳይ ሁለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች መቀመጫዎች ድምጽ ይሰጥባቸዋል። በዕለቱ የድሬደዋ ምክር ቤት 189፣ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 36 አባላት ይመረጣሉ።...more3minPlay
May 31, 2026አዲስ አበባ በጠቅላላ ምርጫ ዋዜማኢትዮጵያ 54 ሚሊዮን ሕዝብ በመራጭነት ተመዝግቦበታል የተባለለትን ጠቅላላ ምርጫ ልታደርግ ዋዜማ ላይ ነች። ርእሠ ከተማ አዲስ አበባ ነገ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን በሚከናወነው ምርጫ ዋዜማ ላይ ምን ትመስላለች የሚለውን በጥቂቱ ዳሰናል።...more3minPlay
May 31, 2026የሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋ ነዋሪዎች ስለ ምርጫ ምን ይላሉ?የሶማሌ ክልል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላሉት 23 መቀመጫዎች ገዢው ብልፅግና ፓርቲን ጨምሮ የ12 የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎች እና አራት የግል ተወዳዳሪዎች ለምርጫ ቀርበዋል። ለክልሉ ምክር ቤት 273 መቀመጫዎች የሚወዳደሩት 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎች እና 39 የግል ተወዳዳሪዎች ናቸው።...more0minPlay
May 30, 2026አዲስ አበባ በምርጫ የጥሞና ጊዜ እና የቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ድባብ መካከልአርሰናል በፍጹም ቅጣት ምት በፓሪ ሳንጃርሞ ከመሸነፉ በፊት የምርጫ የጥሞና ጊዜ እና የቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የፈጠረው ስሜት በአዲስ አበባ ሲጋጩ የዶቸ ቬለው ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ ታዝቧል። የእግር ኳስ ወዳጆች ከዚህ ቀደም በአደባባይ ባሳዩት ስሜት ምክንያት የጸጥታ አስከባሪዎች ቁጥጥር ሲያደርጉ ተመልክቷል።...more0minPlay
May 30, 2026የኢትዮጵያ ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ እና የዶቸ ቬለ ጋዜጠኛ የጉዞ ላይ ትዝብትከአዲስ አበባ የተነሳው የዶቸ ቬለ ጋዜጠኛ ታምራት ዲንሳ በኦሮሚያ ክልል በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን እንዲሁም ወሊሶ እና ወልቂጤን በመሳሰሉ ከተሞች ያለውን የምርጫ ድባብ ታዝቧል። በጉዞው የምርጫ ጣቢያዎችን እንቅስቃሴ ከመመልከት ባሻገር አርሶ አደሮችን እና አሽከርካሪዎችን አነጋግሯል።...more0minPlay
May 30, 2026በኢትዮጵያ ምርጫ ውስጥ የሴቶችን ጥቅም እና ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ድምጽ ይሰማል?በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶችና የጸጥታ መደፍረሶች ዋንኛ ተዋናይ ባይሆኑም ቀዳሚ ተጎጂዎች እናቶች እና ሴቶች ናቸው። የዕለት ተዕለት የኢኮኖሚው ውላፈን ይገርፋቸዋል፤ የዋጋ ንረት በቀጥታ የሚያርፈው በእነሱ ትከሻ ላይ ነው። ሰባተኛውን የኢትዮጵያ ምርጫ ሲያስቡ ሴቶች ምን ይላሉ?...more0minPlay
May 30, 2026የአማራ ፋኖ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ ሥራዉን ስለማወኩ የደረሰው መረጃ እንደሌለ ምርጫ ቦርድ ገለፀየአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከአርብ እስከ ማክሰኞ በአማራ ክልል ከአምቡላንስ በስተቀር የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንደማይኖር አሳስቧል። ከመንግሥት ጋር ዉጊያ ላይ ያለው ይህ ኃይል በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቁሳቁስ ስርጭት ሥራ ላይ የፈጠረው እክል ስለመኖሩ የተጠየቁት የቦርዱ ሰብሳቢ "ከምርጫ ቦርድ ሠራተኛ ቆመናል የሚል ሪፖርት የለም" ብለዋል።...more0minPlay
May 30, 2026ግጭት ያልራቀው የአማራ ክልል ወጣቶች ስለ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ምርጫ ምን ይላሉ?የቆቦው ወጣት “ሀገርም እየፈረሰች ቢሆን ምርጫ ግዴታ ነው” የሚል ዕምነት አለው። የደሴው ነዋሪ “በጫካ ውስጥ ያሉት አካላቶች የመጨረሻው ግባቸው ሊሆን የሚችለው ምርጫ ነው” ብሎ ይጠብቃል። ከቅርብ ርቀት ተኩስ የሚሰማው የመካነ ሰላም ወጣት በአካባቢው በሚካሔደው ግጭት ምክንያት “መጀመሪያ ሰላም ሳይኖር ምርጫ አለ እንዴ?” ሲል ይጠይቃል።...more0minPlay
May 30, 20267ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከመራጮች ቁጥር አንጻርከነገ በስቲያ ሰኞ የሚካሄደው የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመራጮች ብዛት በአፍሪካ ቀዳሚ ከሚባሉት ምርጫዎች አንዱ ለመሆን በቅቷል ፡፡ የኢትዮጵያው ጠቅላላ ምርጫ በ2023 በናይጄሪያ እና በ2025 ደግሞ በግብፅ የተካሄዱ ምርጫዎችን ተከትሎ በመራጮች ብዛት ከአፍሪካ ሦስተኛው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።...more0minPlay
May 30, 2026የኢትዮጵያ ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማበኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ሰኞ ለሚካሔደው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአካባቢው የምርጫ ቦርድ ማስተባበሪያ አስታወቀ። በኦሮሚያ መንግስትን በትጥቅ የሚወጋው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ምርጫውን በመንቀፍ መግለጫ አውጥቷል፡፡ የክልሉ ፖሊስ ምርጫው በፀጥታ ችግር እንዳይፈተን በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጿል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.