Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.
May 28, 2026ኬንያታ የኢትዮጵያን ምርጫ ታዛቢ ቡድን እንዲመሩ ለምን ተመረጡ?«ኡሁሩ የኢትዮጵያን ሁኔታ ይረዳሉ። በኢትዮጵያ ያለውን ሁሄታ ይረዳሉ። ኡሁሩ የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ባላቸው ኢትዮጵያውያንም በቀላሉ ተቀባይነት ያገኛሉ። እኔ እንደ ምርጫ ጉዳይ ባለሙያ፣የኡሁሩን ሹመት ተአማኒነት ያለው አድርጌ ነው የምመለከተው። በኢትዮጵያ ከሚገኙና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው በርካታ አካላትና ተሳታፊዎች ጋር መስራት ይችላሉ። »...more4minPlay
May 28, 2026ምርጫና የሴቶች ተሳትፎ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ እንደሚያመለክተው በ7ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ 50.5 ሚሊዪን የሚደርሱ ዜጎች ለመምረጥ የተመዘገቡ ሲሆን 46 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስለሴቶች ተሳትፎ ያነጋርናቸው ነዋሪዎች ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚካሄደው ምርጫ ለመሳተፍ በመጠበባቅ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡...more4minPlay
May 28, 2026ወጣት መዓዛ ግደይ፤ ታዋቂዋ ተፅዕኖ ፈጣሪና የማኅበረሰብ አንቂትግራይ የነበረዉ ጦርነት ሰዎች ላይ ብቻ ያነጣጠረ አልነበረም፤ ጦርነቱ ሰዎች የተገደሉበት ብቻ አልነበረም፤ የምትለዉ ወጣት መዓዛ ግደይ፤ የትግራይ ህዝብ ከሠላሳ ዓመት በላይ ጥሮ ግሮ ያፈራዉ ሐብትም ወድሞበታል ብላለች። ትግራዋይት ነኝ የምትለዉ ወጣትዋ በትግራይ ወላድ እናቶች በቂ የህክምና ጣብያ እንዲኖራቸዉ ድርጅት አቋቁማ እየሰራች ነዉ።...more15minPlay
May 28, 2026''ምርጫው፣ አገሪቱን ወደ ባሰ ቀውስ ሊያሸጋግር የሚችል ነው።'' የሰላማዊ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ትግል ደጋፊዎች የጋራ-መድረክየዘንድሮው ምርጫ በሂደቱ አሳታፊነትና ነጻነት ካለፋት 6 ምርጫዎች የበለጠ ፋይዳ-ቢስ ብቻ ሳይሆን በውጤቱም አገሪቱን ወደ ባሰ ቀውስ ሊያሸጋግር የሚችል ነው ሲል የሰላማዊ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ትግል ደጋፊዎች የጋራ-መድረክ ገለጸ።ተንታኝ አቶ አያና ፈይሳ ሂደቱ እጅግ አመርቂ ስራ የተሰራበት በተሳትፎም ታይቶ የማይታወቅ ቁጥር የተመዘገበበት ብለውታል።...more4minPlay
May 28, 2026የሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ድባብ በአዲስ አበባሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ ሦስት ቀናት ቀርተዋል። የፊታችን ሰኞ ለሚካሄደው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ እስከ ትናንት የተካሄደው የፖለቲካ ፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ተጠናቆ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ምርጫው ያሉት ቀናት የጥሞና ጊዜ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።...more7minPlay
May 28, 2026የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ማስጠንቀቂያየአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መግለጫ ከነገ አርብ ግንቦት 21 እስከ መጨው ማክሰኞ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአማራ ክልል ከአምቡላንስ በስተቀር ምንም አይነት የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዳይኖር አሳስቧል።...more5minPlay
May 28, 2026የትግራይ ክልል ከኢትዮጵያ ፌዴሬሽን እየራቀ ነው?ከጥቅምት 2013 ጀምሮ የትግራይ ክልል በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት ተወካዮች የሉትም። የፌድራል መንግሥት እና ህወሓት ለጥልቅ ልዩነቶቻቸው መፍትሔ አበጅተው ምርጫ ካልተካሔደ የትግራይ ክልል በምክር ቤቶቹ ሳይወከል የሚቀርባቸው ዓመታት ወደ አስር ከፍ ሊል ይችላል።...more0minPlay
May 27, 20261447ኛው የዒድ አል አድሃ አረፋ በዓል በአዲስ አበባበመላው ኢትዮጵያ 1447ተኛው የኢድ አል አድሃ በዓል በድምቀትና በታላቅ የአንድነት ስሜት መከበሩ ተገለጠ። ታላቁ የሰዋዕትነት እና የደግነት መገለጫ የሆነው በዓል በመላው ዓለም በሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድም እየተከበረ ነው።...more3minPlay
May 27, 2026የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በደሴ ከተማ1447ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በደሴ ከተማ የእምነቱ ተከታዮች እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል። የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ከነብዩ ኢብራሂም የተጀመረ የመታዘዝና የመደጋገፍ በዓል ነው ይላሉ የደሴ አረብ ገንዳ መስጂድ ምክትል ኢማም የሆኑት ሼህ ኡመር አሊ።...more4minPlay
May 27, 2026የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በድሬደዋ እና ሀረር ከተሞች1447ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በድሬደዋ እና ሀረር ከተሞች በኢድ ሰላት እና ሃይማኖታዊ ስነ ሥርዓቶች ተከብሯል። በዓሉን አስመልክቶ በሁለቱ ከተሞች መልእክት ያስተላለፉ የሃይማኖቱ አባቶች ከቀናት በኋላ ሀገሪቱ የምታካሂደው ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን መልእክት አስተላልፈዋል።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.