Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.
May 26, 2026የተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ በአማራ ክልልቀጣዩ አገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ አንድ ሳምንት ብቻ በቀረበት ወቅት በአማራ ክልል በተፋዘዘ ሁኔታ ላይ የነበረው የተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ከባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀናት ጀምሮ በአንዳንድ ቦታዎች ተጠናክሮ መቀጠሉ ተነግሯል። ፓርቲዎቹ ምልክቶቻቸውን እና አማራጭ የፖሊሲ ሐሳቦቻቸውን እያስተዋወቁ ነው ተብሏል።...more0minPlay
May 26, 2026የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የምርጫው ዘመቻሰኞ ግንቦት 24 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ አስቻይ የፀጥታ ይዞታ አለባቸው በተባሉ አከባቢዎች በአካል በመድረስ የምረጡኝ ቅስቀሳ ማድረጉን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ገለጸ ። በምርጫ ሂደቱም በመገናኛ ብዙኃንና በሌሎች የምርጫ ቅስቀሳ ስልቶች ያሉትን እድሎች ተጠቅሞ ደጋፊዎቹ ጋር ለመድረስ የተቻለውን ማድረጉንም ዐሳውቋል ።...more0minPlay
May 26, 2026የአፍሪቃ ኅብረት ባልተጠናቀቁ የቤት ሥራዎቹ ላይ ማተኮር እንዳለበት ተገለፀየአኅጉሪቱን የኢኮኖሚ ውሕደት ማሳካትና የቀጠሉ ግጭቶችን ማስቆም፣ የአፍሪቃ ኅብረት ቀጣይ የቤት ሥራዎች መኾናቸውን ዶይቸ ቬለ ያነጋገራቸው ተንታኛች ጠቆሙ። የአፍሪቃ አገራት ከቅኝ አገዛዝ ነጻ እንዲወጡ ድጋፍ ከማድረግና የዘር መድልዎ ጨቋኝ አገዛዝ እንዲያበቃ ከመሥራት አንጻር ግን አኅጉራዊ ተቋሙ የተሳካ ሊባል የሚችል ሥራ መሥራቱን አመልክተዋል።...more0minPlay
May 26, 2026የምርጫ ቅስቀሳቃ እና ፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየትበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 8 የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳቀ እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን፤ የቤኒሻንጉል ሕዝቦዝች ነጻነት ንቅናቄ (ቤ.ሕ.ኔ.ን) እና የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉ.ህ.ዲ.ን) በምርጫ ቅስቀሳቀ ውቅት በተወሰኑ ወረዳዎች ክልከላ እንደገጠማቸው የገለጹ ፓርቲዎች ናቸው።...more0minPlay
May 25, 2026ማሕደረ ዜና፣ ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን ይደራደራሉ፣ ይግባባሉ፣ ይዛዛታሉምይሁንና የዋሽግተን ባለሥልጣናት እንዳሉት ከስምምነት ጫፍ ላይ መድረሳቸዉን አላረጋገጡም።ኢራኖች እንደሚሉት የሆርሙዝ ወሽመጥ የኢራንና የኦማን ጉዳይ እንጂ ዩናይትድ ስቴትስን አይመለከትም።የኑክሌር ጉዳይም ወደፊት ድርድር እንዲደረግበት ተግባቡ እንጂ አሜሪካኖች እንዳሉት በእስካሁኑ ድርድር ስምምነት አልተደረገበትም...more13minPlay
May 25, 2026ጎጎት ፓርቲ ራሱን ከምርጫው ለማግለል የሚገደድ መሆኑን አስታወቀፓርቲው አሁን ላይ እየተፈጸመ ይገኛል ያለውን የፓርቲውን እንቅስቃሴ የማሰናከል ድርጊት በአስቸኳይ ካልታረመ ራሱን ከምርጫው ለማግለል የሚገደድ መሆኑን ነው በመግለጫው ያሳሰበው፡፡...more0minPlay
May 25, 2026«ምርጫ ቦርድ የዜጎችን መሠረታዊ የሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሊነጥቅ አይገባም»ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱን ለዶቼ ቬለ የገለፁት ዶክተር ራሔል ፍርድ ቤት ይህንኑ የቦርዱን ውሳኔ ማጽናቱን ነግረውናል። ውሳኔዉም "የፓርቲውን ሕልውና ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱ የጀመረችውን የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት በእጅጉ የሚፈታተን ነው።"ብለውታል።...more0minPlay
May 25, 2026በሰሜን ኢትዮጵያ ሌላ መልክ ያለው አዲስ ግጭት ሊቀሰቀስ ይሆን?የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጀ ተሾመ ገመቹ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ “ፅምዶ” ስለተባለው ስብስብ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡...more0minPlay
May 25, 2026በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት የተቋቋመው የግዚያዊ መስተዳድር መፍረስ የፈጠረው ስጋት«የሱዳን መንግስት ለህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚሰጠው እርዳታ የሚባለውን ያህልም ባይሆን በሁለቱ መካከል የቆየ ግንኑነት ያለ መሆኑንና በአሁኑ ወቅትም በርካታ የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ሀይሎች በሱዳን እንድሚገኙ፤ የፋኖና፤ የኦሮሞ ነጻንት ግምባር (ኦላ) የፖለቲክ ማሳለጫ በመሆን ግን እንደሚረዳ የታወቀ ነው»...more0minPlay
May 25, 2026የግንቦት 17 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባኢትዮጵያውያን እና የምስራቅ አፍሪካ አትሌቶች ደምቀው የዋሉበት የተለያዪ የአትሌቲክስ ውድድሮች ተካሂደዋል። የአፍሪካ ኬፕ ታውን ማራቶን የኢትዮጵያውያን ድርብ ድል የተሰራበት ነበር። በሌላ በኩል የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ትላንት ምሽት የአርሰናል ዘውድ መጫን፣ የዌስትሃም መውረድ እና የስንብት እንባዎች አስተናግዶ ተጠናቅዋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.