Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.
May 22, 2026ለውጭ ገበያ በሚቀርበው የኢትዮጵያ ቡና ላይ የተጋረጠው ፈተናየኢትዮጵያ ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ የሆነው ወደ ውጭ የሚላክ ቡና ዘርፍ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብቷል። በዚህ የተነሳም የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣንን ጨምሮ የሚመላካታቸው ሁሉ ቡና ላኪዎችና አምራቾች ያከማቹትን ቡና በፍጥነት ወደ ዓለም ገበያ እንዲያወጡ ጥሪ እያቀረቡ ነው ።...more3minPlay
May 21, 2026የደቡብ ወሎ የምርጫ ካርድ ውዝግብበደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የጸጥታ ችግር ባለባቸውና በታጣቂዎች በተያዙ ቀበሌዎች ውስጥ ገዢው ፓርቲ በሕገ-ወጥ መንገድ የምርጫ ካርድ እያደለ ነው ሲሉ የወሎ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ወዴፓ) እና የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ቅሬታቸውን አሰሙ። #ምርጫ2018 #EthiopiaElection2026...more0minPlay
May 21, 2026ጋዜጠኛ ሣልሳዊት እና የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ መልዕክቶችዋበጋዜጠኝት ሞያ ፋና ብሮድካስቲንግ ወደ ስምንት ዓመት ገደማ አገልግላለች። በቅርቡ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በተለይ በህብረተሰብ ዘንድ የሚሰሙ እንከኖችን ማለትም ህፀጽፆችን ነቅሳ አዉጥታ በምትለቃቸዉ ትምህርት አዘል፤ ቪዲዮዎችዋ ታዋቂነትን እያተረፈች ነዉ። ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ይመር።...more0minPlay
May 21, 2026አፍሪካ ሲዲሲ ኢቦላ አስቸኳይ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ነው አለየአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል- አፍሪካ ሲዲሲ በኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክና በዩጋንዳ የተከሰተውን የኢቦላ ተሀዋሲ አስቸኳይ አህጉራዊ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ነው በማለት አውጇል።...more4minPlay
May 21, 2026ምርጫ ቦርድ ያሰማራው የፀጥታ ኹኔታን የቃኘው ቡድን ያቀረበው ውጤትና የፓርቲዎች አስተያየትየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 11 ቀናት ለቀሩት ጠቅላላ ምርጫ፣ ምርጫ በሚደረግባቸው አካባቢዎች ያለውን ተጨባጭ «የፀጥታ ኹኔታ እና የፖለቲካ ምኅዳር» እንዲከታተል እና ውጤቱንም እንዲያቀርብ መጋቢት 28 ያሰማራው ቡድን ውጤቱን ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ለቦርዱ ይፋ አድርጓል።...more5minPlay
May 21, 2026ታግተው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፍንጫ ስኳር ፋብሪካ ጊዜያዊ ሠራተኞች መለቀቅባለፈው እሑድ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሱሉላ ፍንጫ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው የፍንጫ ስኳር ፋብሪካ አገዳ ተከላ ሥራ ላይ እንዳሉ በታጣቁ ኃይሎች የታገቱ ከ100 በላይ ሠራተኞች ተለቀቁ።...more4minPlay
May 21, 2026የብሔራዊ ባንክ የ500 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ እና የኑሮ ውድነት ስጋትየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰሞኑን ይፋ ያደረገው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ ከፍተኛ መነቃቃትና ድንጋጤ ፈጥሯል። ባንኩ ለሽያጭ ካቀረበው 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ባሻገር፣ የንግድ ባንኮች የጠየቁት አጠቃላይ የገንዘብ መጠን እጥፍ ጨምሮ 1.06 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።...more3minPlay
May 21, 2026በምርጫ 2018 የተቀዛቀዘው የኦፌኮ ተሳትፎዘንድሮ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሊካሄድ ቀን በተቆረጠለት የኢትዮጵያ ሰባተኛው ምርጫ ገዢው ብልጽግና ፓርቲ እና በርካታ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የምረጡኝ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው። በምርጫው ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጋር በኦሮሚያ ክልል ቁልፍ የገዢው ፓርቲ ተቀናቃኝ ይሆናል ተብሎ የተጠበቀው የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ተሳትፎ በእጅጉ ተ...more0minPlay
May 20, 2026ምርጫ እና ዲጂታል ቴክኖሎጂዲጅታል ቴክኖሎጂ በአሁኑ ወቅት በእያንዳንዱ የዕለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወተውን ያህል፤ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቶችን ለመገንባት በሚካሄዱ ምርጫዎች ውስጥም አንድ አካል እየሆነ መጥቷል። ከመራጮች ምዝገባ እስከ የድምጽ ቆጠራ እና የውጤት ማሳወቂያ ድረስ ቴክኖሎጂ ምርጫዎች የሚካሄዱበትን መንገድ እየቀረጸ ይገኛል።...more12minPlay
May 20, 2026ኢትዮጵያ 60 ሚሊዮን ገደማ ዜጎቿ ኃይል ሳያገኙ ለጎረቤቶቿ ለምን ትሸጣለች?ታላቁን የህዳሴ ግድብ፣ የአሰላ እና የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን በተከታታይ ያስመረቀችው ኢትዮጵያ ለኬንያ የምትሸጠውን ኤሌክትሪክ ለማሳደግ እያጤነች ትገኛለች። አራት ተማሪ ልጆቻቸው ትምህርታቸውን በኩራዝ የሚያጠኑትን እናት ጨምሮ 60 ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያን ግን የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙበትን ቀን ይናፍቃሉ።...more10minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.