Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,871 episodes available.
May 20, 2026ኢትዮጵያ 60 ሚሊዮን ገደማ ዜጎቿ ኃይል ሳያገኙ ለጎረቤቶቿ ለምን ትሸጣለች?ታላቁን የህዳሴ ግድብ፣ የአሰላ እና የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን በተከታታይ ያስመረቀችው ኢትዮጵያ ለኬንያ የምትሸጠውን ኤሌክትሪክ ለማሳደግ እያጤነች ትገኛለች። አራት ተማሪ ልጆቻቸው ትምህርታቸውን በኩራዝ የሚያጠኑትን እናት ጨምሮ 60 ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያን ግን የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙበትን ቀን ይናፍቃሉ።...more10minPlay
May 20, 2026የሁለት ዓመት አስገዳጁ የቤት ኪራይ ውል አዋጅ ሊያበቃ ነውቤት ተከራዮች በስጋት ቤት አከራዮች በጉጉት የሚጠብቁት የሁለት ዓመት አስገዳጅ የዋጋ ገደብ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሳምንታት ቀርተዋል ። አከራዮችና ተከራዮች ምን ይጠብቃሉ፥ እርስዎስ ምን ይላሉ?...more4minPlay
May 20, 2026የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) በምርጫ ቦርድ ላይ ክስ መሠረተየሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ሲፌፓ “ አለአግባብ ከምርጫው ተሳትፎ አግልሎኛል “ ባለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ላይ ክስ መመሥረቱን ዐሳወቀ ፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፦ የፓርቲውን ጥያቄ ያልተቀበለው የእጩዎች ምዝገባ ሂደትን አጠናቅቆ ወደ ኅትመት ሥራ በመግባቱ መሆኑን ገልጿል ፡፡...more4minPlay
May 20, 2026ጠ/ሚ ዐቢይ ስለ ሥራና ሠራተኛ ባሰሙት ንግግር የሰዎች አስተያየትጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰሞኑን «በየቦታው ሠራተኛ ችግር ነው» ፣ በሌላ በኩል «ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ የለም» ይባላል የሚል ተቃርኖ መኖሩን ጠቅሰው ችግሩ የት ላይ እንደሆነ እንዳልገባቸው ገልፀዋል ። እርስዎ ምን ይላሉ?...more4minPlay
May 20, 2026«እንኳን ሌላ ፓርቲ ብልጽግናም ራሱ አይቀሰቅስም» የሰሜን ወሎ ዞን ነዋሪቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ሊካሄድ 12 ቀናት ብቻ በቀሩበት በዚህ ወቅት፣ በሰሜን ወሎ ዞን በተለያዩ ከተሞች የሚካሄደው የምርጫ እንቅስቃሴ እጅግ መቀዛቀዙን፤ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች በኩልም ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ እየተደረገ እንዳልሆነ ነዋሪዎች ገለጹ።...more4minPlay
May 20, 2026የትግራይ የሰላምና ለውጥ ምክር ቤት መሥራች ጉባኤ ዓላማና ህወሓት የሰጠው ምላሽበትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የቀድሞ የክልሉ የፀጥታ መሪዎችና ሃራ መሬት የተባለው ኃይል ወታደራዊ አመራሮች የትግራይ የሰላም እና ለውጥ ምክር ቤት መስራች ጉባኤን ትናንት ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ አደረጉ።...more5minPlay
May 19, 2026«አማራጭ ለጀርመን» AfD የሚያገኘው የህዝብ ድጋፍ መጨመር ያስከተለው ስጋትAFD በተለይም ምሥራቅ ጀርመን በሚገኙ ፌደራዊ ክፍለ ሀገራት የሚያገኘውድጋፍ እየጨመረ ሄዷል። በመስከረም ምርጫ በሚካሄድበት በምሥራቅ ጀርመኑ የዛክሰን አንሀልት ፌደራዊ ክፍለ ሀገር ፓርቲው ጠንክሮ እየወጣ ነው። በክፍለ ሀገሩ በተካሄደ ህዝብ አስተያየት መመዘኛ ፓርቲው 41 በመቶ ድጋፍ ሲያገኝ CDU ደግሞ 26 በመቶ ድጋፍ ብቻ ነው የተሰጠው።...more11minPlay
May 19, 2026የአውሮጳ ህብረት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እንዲከበር በድጋሜ አሳሰበየአውሮጳ ህብረት ከ2013 እስከ እስከ 2015 ዓም በስሜን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ያስቆመውን የፕሪቶሪያ ስምምነት ሁሉም ወገኖች እንዲያከብሩና ወደ ዳግም ጦርነት ሊያመራ ከሚችል ማናችውም ድርጊት እንዲቆጠቡ ያሳሰበና የሚያሳስብ መሆኑን የህብረቱ ቃል አቀባይ ሚስተር አኑዋር ኤል አኑዋኒ ትናንት በድጋሜ አስታውቀዋል።...more4minPlay
May 19, 2026ገዢው ፓርቲ ላይ የሰላ ትችት ያቀረበው የትብብር መግለጫ«የኢትዮጵያ ሰላምና መጻኢ ዕድል የሚወሰነው በእውነተኛ የሕዝብ ተሳትፎ እንጂ ለይስሙላ በሚደረግ ምርጫ አይደለም» ሲል ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰኘው የአራት የፖለቲካ ድርጅቶች ቅንጅት አስታወቀ፡፡...more0minPlay
May 19, 2026በባንክ ደንበኞች ላይ የተጥለው ገንዘብ ማንቀሳቀስ እገዳ እና አንድምታውየኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ በታሪኩ አይቶት የማያውቀውን ትልቅ እና ጥብቅ እርምጃ መተግበር ጀምሯል። የባንክ ሒሳባቸውን "ፋይዳ" ከተሰኘው ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ያላገናኙ ደንበኞች የባንክ ሒሳባቸው ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ መታገድ እና መዘጋት መጀመሩ ተገልጿል።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,871 episodes available.