Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.
May 06, 2026የኢትዮጵያ መንግሥት የስድስት ወራት የሀገር ውስጥ ብድር ወለድ ክፍያ ካለፈው ዓመት ሲነጻጸር 250% ጨመረየኢትዮጵያ መንግሥት የ2018 የመጀመሪያ መንፈቅ የሀገር ውስጥ ብድር ወለድ ክፍያ 126.5 ቢሊዮን ብር ደርሷል። ወለዱ በስድስት ወራት ለዕዳ ከተመደበው በጀት 64.6% ድርሻ አለው። ከ2017 ተመሣሣይ ወቅት ሲነጻጸር ከ250 በመቶ በላይ ጨምሯል። ባለፈው ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ለሀገር ውስጥ ወለድ መንግሥት 36 ቢሊዮን ብር ከፍሎ ነበር።...more11minPlay
May 06, 2026የሳይበር ጉልበተኞች ጥቃት በወጣት ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ላይየማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሰዎች ተሰጦዎቻቸውን እንዲያወጡ፣ ሀሳቦችን እንዲያካፍሉ እና መስተጋብር እንዲፈጥሩ ያግዛሉ። በዚያው ልክ፤መድረኮችቹ የሳይበር ጉልበተኞች ጥቃት የሚስፋፋባቸው ቦታዎች እየሆኑ ነው። በተለይ ወጣት ሴቶች ለዚህ ጥቃት የበለጠ ተጋላጭ ሲሆኑ፤ራስን እስከማጥፋት የሚያደርስ ሥነልቡናዊ ጫና እንደሚፈጥርም ጥናቶች ያሳያሉ።...more0minPlay
May 06, 2026አሜሪካ የኤርትራን ማዕቀብ ለማንሳት ማጤኗ ለኢትዮጵያ በረከት ወይስ መዘዝ?ሮይተርስ የዜና ወኪል አሜሪካ በቀይ ባሕር ዳርቻ ቁልፍ ቦታ ላይ በምትገኘው በኤርትራ ላይ የጣለቻቸውን ማዕቀቦች ልታነሳ መሆኗን የሚያመለክት የአሜሪካ መንግሥት ውስጣዊ ሰነድ ስለማሳየቱ ዘግቧል። አሜሪካ የቆየ የኤርትራ ማዕቀቦችን ለማንሳት ማጤን ለአገሪቱ ይዞላት የሚመጣው በረከት እና በዚህ ውስጥ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ላይ ምን ያስከትል ይሆን?...more0minPlay
May 06, 2026ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ኢትዮጵያውያን በተለየ መንገድ የጥቃት ኢላማ መሆናቸውበደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለየ መንገድ የጥቃት ኢላማ የኾኑት ከተሰማሩበት የንግድ ሥራ ዘርፍ ጋር በተያያዘ መሆኑን አንድ አንጋፋ የፍልሰት ጉዳይ ተንታኝ ተናገሩ ።በደቡብ አፍሪቃ የሚንቀሳቀሱ የአንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ንግግርም፣ እየቀጠለ ለመጣው የመጤ ጠል እንቅስቃሴና ጥቃት አንዱ ምክንያት መኾኑን ተንታኙ አሰረድተዋል ።...more0minPlay
May 06, 2026የአላማጣና አካባቢው ወጣቶች የጦርነት ሥጋትና ስደትበአላማጣ ከተማና አካባቢው የሚገኙ ወጣቶች ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞችና አረብ ሃገራት በስደት እያመሩ መሆኑን ገለጹ። ወጣቶቹ ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ሥጋት ገብቷቸዋል ፤ በፖለቲካ አመለካከታችንም ለእስር እየተዳረግን ነው ብለዋል ።...more0minPlay
May 06, 2026የሱዳን ክስና እና የኢትዮጵያ ምላሽሱዳን ከኢትየጵያ ግዛት ባሕርዳር ከተማ ተነሱ ባለቻቸው ሰው አልባ ጢያራዎች (ድሮኖች) ዋና ከተማዋ ካርቱም አየር ማረፍ ላይ ጥቃት መፈጹሙን ትናንት ዐሳውቃለች ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ የሱዳንን ውንጀላ «መሠረት የለሽ» ሲል አጣጥሎታል።...more0minPlay
May 06, 2026ህወሓት ትናንት የወሰደው 'ርምጃ እና የሚኖረው ውጤትከስድስት ዓመት በፊት የተቋቋመው የትግራይ ክልል ምክር ቤት የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሊቀመንበርን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ ማክሰኞ፤ ሚያዝያ 27 ቀን፣ 2018 ዓ.ም መርጧል። የክልሉ ምክር ቤት ወደ ሥራ የተመለሰው በህወሓት ውሳኔ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ ርምጃውን የሚነቅፉ አስተያየቶች ከልዩ ልዩ አካላት እየተሰማ ነው።...more0minPlay
May 05, 2026አሜሪካን ጀርመን የሚገኙ ወታደሮቿን የማስወጣት እቅዷ መልዕክትና አንድምታውዩናይትድ ስቴትስ ጀርመን የሚገኙ ወደ 5 ሺህ የሚጠጉ ወታደሮቿን እንደምታሳውጣ ባለፈው ሳምንት ማሳወቋ በጀርመን ብሎም በአውሮጳ የሰሞኑ ዐቢይ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል። ይህ የአሜሪካን ውሳኔ የጀርመን መራኄ መንግሥት ዋሽንግተን በኢራን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ስልት ከተቹ በኋላ ይፋ መደረጉ ጉዳዩ ይበልጥ ትኩረት እንዲስብ አድርጓል።...more0minPlay
May 05, 2026የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋምየጥንት ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ በዛሬዉ ዕለት ታስቦ ዉሏል። ሚያዚያ 27 ኢትዮጵያውያን የፋሽስት ወረራን በሕብረትና በአርበኝነት ተጋድሎ የቀለበሱበት ቀን ነው። ይህ ድል ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ ውድመት፣ እልቂት ከደረሰ እና መስዋዕትነት ከተከፈለ በኋላ የተገኘ ነዉ።...more4minPlay
May 05, 2026በምርጫ ቅስቀሳ ተግዳሮት ገጠመን ያሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በደቡብ ወሎ ዞንበ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በደቡብ ወሎ ዞን የሚሳተፉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ ገዢው ፓርቲ የመንግሥት መዋቅርን በመጠቀም እያደረሰብን ያለው ተጽዕኖ እና በአካባቢው ያለው የጸጥታ ስጋት ለምርጫ ቅስቀሳ ሥራችን እንቅፋት ሆኖብናል አሉ። ፓርቲዎቹ ይህ የምርጫውን ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚከተዉ ነዉ ብለዋል።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.