Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.
May 05, 2026የነዳጅ ዋጋ ላይ የተደረገው የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ የሚኖረው ጫናየኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ትናንት ጉልህ ጭማሪ አድጓል። በዚህ መሠረት በሊትር 23 ብር ጭማሪ የተደረገበት ቤንዚን 167 ብር ከ50 ሳንቲም እየተሸጠ ነው። ኬሮሲን እና የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ ከእጥፍ በላይ የዋጋ ጭማሪ ተደርጎባቸዋል። አንድ የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ኹኔታው አደጋ እንዳይፈጥር ሥጋታቸውን ገልፀዋል።...more4minPlay
May 05, 2026የአሜሪካ ወታደሮች ከጀርመን የመውጣት አንደምታየአሜሪካ የጦር ሚኒስቴር (ፔንታጎን) በጀርመን ከሰፈሩት ወታደሮቹ ቢያንስ አምስት ሺውን የሚያስወጣ መሆኑን ባለፈው አርብ አስታውቋል።ፕሬዚዳንት ትራምፕ በማግስቱ በሰጡት መግለጫም ተጨማሪ ወታደራች ከጀርመን ሊወጡ እንደሚችሉ ብቻ ሳይሆን በጣሊያንና ስፔን ካሉት ወታደሮችም ተመላሾች ሊኖሩ እንደሚችሉ ፍንጭ ስተዋል።...more5minPlay
May 05, 2026የደን ልማትን ለማስፋፋት የግለሰብ ጥረት በአሶሳለደን ሀብት መመናመን ዋነኛ ምክንያቱ በአብዛኛው ሰዎች ቢሆኑም የተራቆተ አካባቢን በዛፍና ተክሎች ሸፍነው አረንጓዴ የሚያለብሱትም ያው ሰዎች ናቸው። የዛሬው የጤና እና አካባቢ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ከ30 ዓመታት በላይ የተራቆተ አካባቢን በሀገር በቀል ዛፎች፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች በማልበስ የተሸለሙ ሰው ያስተዋውቀናል ።...more9minPlay
May 04, 2026የትግራይ ክልል አዲስ ፕሬዝደንት አዲስ ሥራ አስፈጻሚ እየጠበቀ ነው-ግጭት የማቆም ሥምምነቱስ?በህወሓት ውሳኔ መሠረት በጳጉሜ 2012 በተካሔደው እና ፌድራል መንግሥት “ሕገ-ወጥ” ባለው ምርጫ የተመሠረተው የትግራይ ክልል ምክር ቤት በመጪዎቹ ቀናት ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል። የምክር ቤቱ ወደ ሥራ መመለስም ይሁን የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች የትግራይ ክልል እና የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ቀጣይ ግንኙነት ምን እንደሚመስል የሚበይኑ ይሆናል።...more0minPlay
May 04, 2026በሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ የቀጠለው የአሜሪካንና የኢራን ውዝግብበሆርሙዝ ሰርጥ የሚተላለፉ መርከቦችን ማጅብ እጀምራለሁ ያላቸው አሜሪካን ዛሬ የተወሰኑ መርኮቦችን በስርጡ ማሰለፏን አስታውቃለች። ትራምፕ ቀደም ሲል ፕሬዚዳንት ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው ማኅበራዊ መገናኛቸዉ ላይ እንደገለፁት «ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ሀገራት» በዚህ ዘመቻ ላይ እንዲሳተፉ ተጠይቀዋል።...more0minPlay
May 04, 2026የምረጡኝ ቅስቀሳ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በመጪው ግንቦት ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ ናቸው ፡፡ በክልል እና በዞኖች ላይ ቅስቀሳዎቻቸውን ያለምንም ችግር ማከናወን መቻላቸውን የተናገሩት የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች «በወረዳ ደረጃ ግን የተለያዩ ጫናዎች አጋጥሞናል» ብለዋል ፡፡...more0minPlay
May 04, 2026የዓለም የፕሬስ ነጻነት መዘርዝርና የኢትዮጵያ ደረጃየጋዜጠኝነት ሙያ በራሱ የተለያዩ ተጋላጭ ሁኔታዎች ውስጥ የሚያስገባ ሙያ ሆኖ ሳለ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ብዙ ጋዜጠኖች ከሙያቸው ውጪ ሆነዋል ሲል አስተያየቱን ለዶይቼ ቬለ የሰጠው በጋዜጠኝነት ሙያው ከ30 ዓመት በላይ ልምድ ያለው ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ፤ “በተለይዩ እስር ቤቶች ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞቻችን አፋጣኝ ፍትህ ይሻቸዋል”ብለዋል፡፡...more0minPlay
May 04, 2026ምርጫ ቦርድ ኢሶዴፓ ያቀረባቸውን 309 ዕጩዎች ከምርጫ ውድድር ውጪ አደረገየኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፖርቲ (ኢሶዴፓ) ቦርዱ ለሕዝብ ይፋ ያደረጋቸውን 309 ዕጩዎች ሕጋዊ መስፈርቱን ተከትሎ መመዝገቡን፣ የተመዘገቡ 309 "ዕጩዎች ልዩ መብት" እንዲከበር ዶክተር ራሔል ባፌ ለቦርድ በጻፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል። "ስህተት ያልሰሩ ዕጩዎችን ከመሬት ተነስቶ ነዉ ከምርጫው ወጥተዋል ያለው።" ሲሉም ለዶቼቬለ ተናግረዋል።...more0minPlay
May 04, 2026የሚያዝያ 26 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባበአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ እግር ኳስ በነገው ምሽት አርሰናል እና አትሌቲኮ ማድሪድ ይፋለማሉ ። የአትሌቲኮ ማድሪዱ አንቷን ግሪዝማን በሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ያላጠናቀቀውን የቤት ሥራ ነገ ማታ አርሰናል ላይ ለመፈጸም ዝቷል ። የዕድሜ ጉዳይ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ እጅግ አነጋጋሪ ኹኗል ። ሙሉውን ዘገባ በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው ማግኘት ይቻላል ።...more0minPlay
May 03, 2026የሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅትና ተግዳሮቶቹከ20 በላይ ሀገራዊ እና ከ40 በላይ ክልላዊ ፓርቲዎች ይሳተፉበታል የተባለው ሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የአንድ ወር ጊዜ ነው የቀረው። ቦርዱ በስድስት ክልሎች «የፀጥታ እና አስቻይ የፖለቲካ ምህዳር»ን እንዲገመግም ያደራጀውን ቡድን ማሰማራቱን ባለፈው ሳምንት አስታውቋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.