Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.
April 30, 2026አዲስ አበባ ድረስ 388 ኪሎ ሜትሮች በእግሩ የተጓዘው እያሱ ማሳረፍ የፈለገው አሻራ ምን ይኾን?የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንግዳችን ከደቡብ ኢትዮጵያ ተነስቶ አዲስ አበባ ድረስ በእግሩ እየተጓዘ ያለ የ20 ዓመት ወጣት ነው። ዛሬ ጉዞውን አጠናቆ አዲስ አበባ ለመግባት እቅድ ይዟል። በመኪና የአንድ ቀን ጉዞ የሆነውን መንገድ ለምን በእግሩ መጓዝን እንደመረጠ እና በጉዞው የገጠሙትን ነገሮች አጫውቶናል።...more10minPlay
April 30, 2026የታጣቂዎች ጥቃት በምሥራቅ ጉራጌ ዞንበማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ምሥራቅ መስቃን ወረዳ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ አምስት ሰዎች በታጣቂች ተገደሉ። ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ትናንት ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ የተኙበት ገብተው መሣሪያ በመተኮስ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የሟች ዘመዶች ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።...more0minPlay
April 30, 2026ግድያና እገታን ያስከተለው የአበርገሌ ወረዳ ግጭትበአማራ ክልል ዋግምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ ከዘጠኝ ቀናት በፊት በተከሰተ ግጭት የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መሞታቸውንና ከ40 በላይ ሰዎች መታገታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና የወረዳው አስተዳደር ገለጹ።...more0minPlay
April 30, 2026የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂዎችን አወገዘየጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ጉ.ህ.ዴ.ን) በፓርቲው ስም ወደ ትጥቅ ትግል የገቡ ቡድኖችን አወገዘ። ፓርቲው የሰላም ጥሪን ያልተቀበሉ ታጣቂዎች በሰዎች ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ ጠቅሶ ቡድኑም ከፓርቲው ጋር ግንኙነት እንደሌለው የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉዴታ ተናግረዋል።...more0minPlay
April 30, 2026ህወሓት ሰሞኑን በትግራይ ክልል እያደረገ ያለው ስብሰባ ምንድን ነው?ህወሓት በትግራይ ክልል «ምን ዓይነት ሥርዓት ይኑር» በሚለው ላይ ሰሞኑን ውይይት እየተደረገ መሆኑን ለዶቼ ቬለ ገለፀ። ድርጅቱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሥልጣን በፌዴራል መንግሥት «የተናጠል» ያለው ውሳኔ መራዘሙ የፕሪቶሪያን ስምምነት አፍርሶታል በሚል ነው ይህን እያደረገ ያለው።...more0minPlay
April 30, 2026ዓለም አቀፉ የስብአዊ መብት ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች ያቀረበው ጥሪዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች ትናንት ባወጣው መግለጫ በሳውድ አረቢያ የሞት ቅጣት ከተፈረደባቸው ስደተኖች መካከል በክሃሚስ ሙሼት እስር ቤት የሚገኙ ቢያንስ 65 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሞት አፋፍ ላይ መሆናቸውን አሳስቧል።...more0minPlay
April 30, 2026አዲሱ የመንግሥት አቅጣጫ በኢትዮጵያ የነዳጅ አቅርቦት ችግርን ይፈታ ይሆን?የኢትዮጵያ ፋይናንስት ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እንዳሉት የአገሪቱ ዕለታዊ የናፍጣ አቅርቦት የመካከለኛውን ምሥራቅ ቀውስ ተከትሎ በግማሽ የቀነሰ ቢሆንም አሁን ግን አቅርቦቱ ቀደም ሲል ወደ ነበረበት እንዲመለስ መንግሥት ወስኗል።...more0minPlay
April 30, 2026የባሕልመድረክ፤ “ አፊኒ “ በራስ ቀለም የተሠራ የፊልም ጥበብፊልሙ በቀጣይ በአገራችን ነባር ባህላዊ እሴቶችን መሠረት ያደረጉ ፊልሞች እንዲሠሩ ሊያነቃቃ ይችላል የሚል እምነት እንዳለው የተናገረው የአፊኒ ፊልም ደራሲው እለፋቸው ብርሃኑ “ ምክንያቱም ፊልሞች የአንድን ማህበረሰቡ ሁለንታናዊ ገጽታ መመልከቻ መስታወት ናቸው ፡፡...more0minPlay
April 29, 2026የናሳ አዳዲስ ፕላኔቶች ፍለጋናሳ ያለፈው ማክሰኞ፣ በጎርጎሪያኑ ሚያዚያ 22 ቀን ፣ ከስርዓተ ፀሐይ/ Solar System/ ውጭ ያሉ ፕላኔቶችን ለመፈለግ እና ያልታወቀ ቁስ ሀይልን ሚስጥሮችን ለመመርመር አዲስ ቴሌስኮፕ ይፋ አድርጓል። በመጭው መስከረም ተልዕኮውን ለመጀመር ወደ አፅናፈ ዓለም ወይም ዩንቨርስ የምትጓዘው ይህቺ ቴሌስኮፕ ሮማን የሚል ስም ተሰጥቷታል።...more0minPlay
April 29, 2026የነዳጅ እጥረቱ በአማራ ክልል በርካቶችን ለኑሮ መመሰቃቀል ዳርጓል ተባለበአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የነዳጅ እጥረት አሽከርካሪዎችን ለከፋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መዳረጉ ተገለጸ። አሽከርካሪዎች፣ ከሁለት ሳምንት እስከ አንድ ወር ለሚደርስ ጊዜ ስራ በማቆማቸው ለቤት ኪራይና ለዕለት ጉርስ መቸገራቸውን ተናግረዋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.