Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.
April 21, 2026«መታመሜ ይበልጥ የካንሰር ህሙማንን እንዳስብ አደረገኝ»ኢትዮጵያ ውስጥ ለካንሰር ህመም የተጋለጡ የገንዘብ አቅማቸው ደካማ የሆነ ወገኖች ህክምና እንዲያገኙ እያገዘ የሚገኝ አንድ ተቋም ሰሞኑን የተቋቋመበትን 22ኛ ዓመት ዘክሯል።እስካሁን በዚህ ተቋም አማካኝነት በሺህዎት የሚቆጠሩ ወገኖች ተገቢውን ህክምና እና ድጋፍ ማግኘት ችለዋል።...more0minPlay
April 21, 2026"ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እየተጣለብን ነው’" የአላማጣ ነዋሪዎች ቅሬታ እና የአስተዳደሩ ምላሽበአላማጣ ከተማ ከፌደራል ኃይሎች መውጣት በኋላ በህወሃት አስተዳደር ስር የሚገኙ ነዋሪዎች "በልማት ዘመቻ" እና "በሰልፍ አልተሳተፋችሁም" በሚል ምክንያት ለከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እና ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ገለጹ። የአስተዳደሩ ከንቲባ የቀረበውን ቅሬታ መሰረተ ቢስ ነው ብሏል።...more4minPlay
April 20, 2026የሚያዝያ 12 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባበዛሬው የስፖርት መሰናዶ፦ አዲስ አበባ ውስጥ ስለተደረገው የመጀመሪያው ግራንድ ፕሪ ፉክክር ዘገባ ይኖረናል ። ባዬር ሙይንሽን ከወዲሁ ዋንጫውን ማንሳቱን ስላረጋገጠበት የጀርመን ቡንደስሊጋም ዳሰሳ ይኖረናል ። ማንቸስተር ሲቲ አርሰናልን ድል አድርጎ በነጥብ ተጠግቶታል ።...more0minPlay
April 20, 2026ሱዳን “የጭካኔ ቤተ-ሙከራ” የሆነችበት ጦርነት አራተኛ ዓመቱን ጀመረበሱዳን ጦርነት በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በድሮኖች ጥቃት ጭምር ተገድለዋል። ጦርነቱ አራተኛ ዓመቱን ሲጀምር 34 ሚሊዮን ሰዎች ሰብአዊ ርዳታ ይጠብቃሉ። ሀገሪቱን ለሁለት የከፈላትን ጦርነት ለማቆም የሚደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። ጦርነቱ ከሱዳን ድንበር በመሻገር ወደ ጎረቤት ሀገሮች ተዛምቶ “ከቁጥጥር ውጪ” ሊሆን እንደሚችል ሥጋት አለ።...more0minPlay
April 20, 2026ጋዜጠኛ ሚሊዮን በየነ «አሁንም ያለበት ቦታ አይታወቅም» - አዲስ ስታንዳርድሚያዝያ 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም. ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከሥራ ቦታው የተወሰደው ጋዜጠኛ ሚሊዮን በየነ «አሁንም ያለበት ቦታ አይታወቅም» ሲል አሠሪው አዲስ ስታንዳርድ ዛሬ አሳወቀ።...more0minPlay
April 20, 2026ሕገወጥነትን ሕግ እንዴት ይቆጣጠረው?ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ እና ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ ውስጥ በተናጥል የተፈጸሙ ድርጊቶች በማኅበራዊ መገናኛው የበርካቶችን ትኩረት ስበዋል። በሮቤ ዕድሜያቸው ጠና ያለው አባት በጎረምሶች ሲደበደቡና በአምቦ ደግሞ የተደራጁ ናቸው የተባሉ ወጣቶች በተለያዩ አጋጣሚዎች ሰላማዊ ዜጎች ላይ አሰቃቂ ድብደባዎችን ሲፈጽሙ ነው የታዩት።...more0minPlay
April 20, 2026ህወሓት ከ2013 ዓ.ም በፊት የነበረው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ ወሰነህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጥቅምት 24 ከ2013 ዓ.ም በፊት የተመረጠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ መወሰኑን አስታወቀ። የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አንድ የሲቪክ ድርጅት፣ የህወሓት ውሳኔ በክልሉ ዳግም የጦርነት ሥጋት እንደሚፈጥር ገልፀዋል።...more0minPlay
April 19, 2026የጄነራል ታደሰ ወረደ ሹመት መራዘም ለክልሉ መፍትሔ ወይስ ሌላ ቀውስ ?ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ሣምንት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደን የሥልጣን ዘመን ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዳራዘሙ ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል። የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በገታው ግጭት የማቆም ሥምምነት ለተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ሉቴናንት ጄኔራል ታደሰ ሁለተኛ ፕሬዝደንት ናቸው።...more48minPlay
April 18, 2026የ "ሰላም ለኢትዮጵያ" ጥምረት ራሱን ከምርጫ ለማግለል የሚገደድበት ኹኔታ መኖሩን ገለጸስምንት ክልላዊ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያሰባሰበው "ሰላም ለኢትዮጵያ" የተባለው ጥምረት፣ በጥምረቱ ላይ ደረሱ ያላቸው ጥሰቶችና ችግሮች በአስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጣቸው ራሱን ከምርጫ ለማግለል እንደሚገደድ ገለፀ። ጥምረቱ ዓርብ ባወጣው መግለጫ በአባሎቹ፣ በደጋፊዎቹ እና በዕጩዎቹ ላይ "ጥቃት፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት" እየተፈፀመ መሆኑን አስታውቋል።...more0minPlay
April 18, 2026ሶማሊያ ቱርክ የነዳጅ ክምችቷን እንድትጠቀም ለምን ፈቀደች?ቱርክ በሶማሊያ የባህር ዳርቻ ነዳጅ ለማውጣት ዝግጅት ላይ ነች፡። ለነዳጅ ፍለጋው ባለፈው ሳምንት የአገሪቱ ትልቅ መርከብ ካግሪ ቤይ፤ ከሞቃዲሾ የባህር ዳርቻ ደርሳለች። በጎርጎሪያኑ በ2024 ሁለቱ ሀገራት የመከላከያ እና የኢኮኖሚ ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራርመዋል። ትብሩ አሁን ወደ ነዳጅ ፍለጋ አድጓል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.