Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.
April 16, 2026የሟች ቤተሰቦች በገዳዮች የተረዱበት አሳዛኝ እውነትሁለት የፖሊስ መኮንኖች እና አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል ሚያዝያ 6 ቀን 2018 በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቀሬ በተባለ አካባቢ በታጣቂዎች ተገድለዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ሌሎች መንገደኞች ላፕቶፖችና ስልኮችን መዘረፋቸውን ገልጸዋል። ኮማንደር ታጁ ጥቃት ፈጻሚዎቹን “ሰርጎ ገብ” ብለዋቸዋል...more0minPlay
April 16, 2026የኢራን ማስጠንቀቂያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ስጋት ደቅኗልኢራን ቀይ ባሕርን ልትዘጋ እንደምንችል ማስጠንቀቂያ መስጠቷ፣ በአፍሪካ ቀንድና በተቀረውም የአህጉሪቱ አካባቢ የበለጠ ስጋት ደቅኗል። ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ተንታኝ እንዳሉት፣የቀጠለው ውጥረት እንዲረግብና ኢኮኖሚያዊ ጫናው እንዲቀንስ፣ አፍሪካ ከሚመለከታቸው ጋር በቅንጅት መስራትና ለተያዘው የሰላም ጥረት ድጋፍ መስጠት አለባት።...more0minPlay
April 16, 2026የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ና ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕካሜሩንን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ “ዓለም በጥቂት አምባገነኖች እየተናጠች ነው” ሲሉ ተናግረዋል። በቅርቡ በአሜሪካው ፕሬዝደንት የቃላት ጥቃት የተፈጸመባቸው ሊዮ “ለራሳቸው ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም በሐይማኖትና የእግዚአብሔርን ስም የሚያጭበረብሩ ወዮላቸው” ብለዋል...more5minPlay
April 16, 2026ትናንት ከሥራ ቦታው የተወሰደው የአዲስ ስታንዳርድ ማኔጂንግ ኤዲተር ያለበት አልታወቀምየኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የአዲስ ስታንዳርድ ማኔጂንግ ኤዲተር ሚሊዮን በየነ ያለበትን ለመለየት እና ነጻ ለማውጣት የአቅማቸውን ጥረት እንዲያደርጉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ወይም ሲጂጄ ጥሪ አቀረበ። ሚሊዮን ከመሥሪያ ቤቱ የተወሰደው ትላንት ረፋድ እንደሆነ ጃኬን አሳታሚ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር አስታውቋል።...more0minPlay
April 15, 2026ደቡብ ወሎ ዞን ፓስፖርት ለማውጣት 161 ሐሰተኛ ሰነዶችበአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ስም የተዘጋጁ ሐሰተኛ የልደት ምስክር ወረቀቶችን በመጠቀም ፓስፖርት ለማውጣት የሞከሩ 161 ግለሰቦች በዚህ ሳምንት ብቻ እጅ ከፈንጅ መያዛቸው ተዘገበ ። ግለሰቦቹ በደላሎች አማካኝነት እስከ 6 ሺህ ብር በመክፈል ሕገ-ወጥ ሰነዶችን እንደሚያዘጋጁ ታውቋል።...more0minPlay
April 15, 2026የኢራኑ ጦርነት፣ ለሱዳኑ ግጭት ትኩረት እንዲቀንስ ማድረጉ ተገለፀበአሜሪካ፣ በእሥራኤልና በኢራን መካከል የተፈጠረው ጦርነትና አሁንም የቀጠለው ውጥረት፣ ለሱዳን የእርስበርስ ጦርነት የሚሰጠውን ትኩረት ቀንሶታል ሲሉ ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የፀጥታ ተንታኝ አስረድተዋል ።...more0minPlay
April 15, 2026ኢሕአፓ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በሚመለከት ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ መጻፉን ገለፀየኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ. በዐሥር ከተሞች ለማድረግ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በሚመለከት ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደብዳቤ መጻፉን ገለፀ። ፓርቲው ዛሬ ረቡእ ለዶቼ ቬለ እንዳለው፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፈረሙት የቃል-ኪዳን ሠነድ መሠረት ሠላማዊ ሰልፍ ሲኖር "ማስፈቀድ" የሚል አስገዳጅ ሕግ አለ።...more0minPlay
April 15, 2026የዩናይትድ ስቴትስ የመርከቦች እገዳ በፍኖተ ሆርሙዝ ለኢራን ምን አመጣ?ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከ እና ወደ ኢራን ወደቦች በፍኖተ ሆርሙዝ በኩል የሚያልፉ መርከቦችን የባሕር ኃይላቸው እንዲያስቆም ወስነዋል ። እገዳው ከተሳካ በቀን 2 ቢሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ወደ ውጭ የምትልከው ኢራን ወደ ድርድ ጠረጴዛው እንድትመለስ ጫናው እጅግ ብርቱ ይሆናል ። ኢራን በመርከብ እስከ 2 ሚሊዮን ዶላር እንደምትቀርጥ ይነገራል።...more0minPlay
April 15, 2026በአየር ንብረት ለውጥ የኢትዮጵያ ቡና አብቃይ አካባቢዎች ሲስፋፉ በኮሎምቢያ እና ሖንዱራስ እንደሚቀንስ ጥናት አሳየየአየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያ ለአረቢካ ቡና በጣም ምቹ የሆነውን አካባቢ አሁን ከሚገኝበት 38% በመቶ በምዕተ-ዓመቱ አጋማሽ ወደ 49% ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል አንድ ጥናት አሳይቷል። በሮቦ ባንክ ጥናት መሠረት የዓለም ሙቀት ሲጨምር በኢትዮጵያ ደጋማ አካቢዎችን ቡና አምራች ሊያደርጋቸው ቢችልም ኮሎምቢያ እና ሖንዱራስ ተጎጂ ናቸው።...more0minPlay
April 15, 2026የመረጃ መንታፊዎች የተጠቃሚዎችን መረጃ እንዴት ያገኛሉ?የዕለት ተዕለት ህይወታችን ከበይነመረብ እና ከዲጅታል መሳሪያዎች ጋር በእጅጉ በተሳሰረበት በአሁኑ ወቅት የመረጃ ጠለፋ እና ምንተፋም በዚያው ልክ እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል።ጥቃቱ ፤መገበያያችን ፣የባንክ ደብተራችን ፣መረጃ የምናገኝበት እና የእያንዳንዱ መስተጋብራችን ዋነኛ አካል በሆኑት የተንቀሳቃሽ ስልኮቻችን ላይ መሆኑ ደግሞ አሳሳቢ ያደርገዋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.