Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.
April 18, 2026ትኩረት በአፍሪቃ፤አስከፊው በሱዳን የኑባ ነዋሪዎች ሕይወትበሱዳን እና በደቡብ ሱዳን መካከል አጣብቂኝ ውስጥ የገቡት እና እራሳቸውን የሚያስተዳድሩት የኑባ ተራሮች ህዝብ ፤በሱዳን ጦርነት ውስብስብ ፈተና እያጋጠማቸው ነው። በአንድ በኩል የድሮን ጥቃት በሌላ በኩል ረሀብ እና ነዋሪዎች መደገፍ የማይችሉት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችንም እያስተናገዱ ነው።...more8minPlay
April 18, 2026አሜሪካ የኢራን ወደቦችን መዝጋቷን የምትቀጥል ከሆነ ኢራን የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን መልሳ እንደምትዘጋ ዛሬ አስጠነቀቀች።ትራምፕ በቃለ ምልልሳቸው ኢራን ለኒኩለር ማብለያነት የምትጠቀምበት ዩራንየም ለአሜሪካ ልትሰጥ ተስማምታለች ብለዋል። ኢራን ግን ያበለጸገችው የዩራንየም ክምችቷ የትም እንደማይሄድ አስታውቃለች።...more0minPlay
April 17, 2026የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እና መልስ የማግኛዉ መንገድየአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ሙሉ ሰላማዊ የሚሆነው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ሲመለስ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ ተንታኞች በፊናቸው የኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚ መሆኑ ከሌሎች ይልቅ እራሷን በኢኮኖሚ እና ደህንነት ጠንካራ ያደርጋታል ብለዋል።...more0minPlay
April 17, 2026በአማራ ክልል መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያችን እንመለስ ጥሪበአማራ ክልል መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙና ከኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ጃርቴ ተፈናቅለው ስድስት ዓመታት ያስቆጠሩ ወገኖች፣ ወደ ቀድሞ ቀያቸው ተመልሰው ራሳቸውን ለመርዳት የዘላቂ መፍትሔ ጥሪ አቀረቡ። የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ስራ አመራር ኮሚሽን ጉዳዩን ለማሳካት እየሰራሁ ነዉ ብሏል። ቅድምያ የሚሰጠዉ ግን ደህንነትና ሰላምን ማረጋገጥ ነዉ።...more0minPlay
April 17, 2026በግጭት አፈታት እና በሰላም ግንባታ ላይ የተካሄደ ጉባኤየኦሮሞ ጥናት ማኅበር፣በግጭት አፈታት እና በሰላም ግንባታ ላይ ያተኮረ ጉባኤ አካሄደ። የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢብራሂም አማኢ ኤሌሞ፣ለዶቼ ቬለ እንዳስታወቁት፣በጉባኤው ላይ፣ ባለፉት በርካታ ምዕተ ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን ረገድ ስላለው ሚና እና ተያያዥ ጉዳዮች ጥናቶች ቀርበውበታል።...more0minPlay
April 17, 2026አፍሪካ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊነት የሚወዳደር የጋራ ዕጩ አላፀደቀችምየቀድሞው የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል፣ ቀጣዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ለመኾን እንዲወዳደሩ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በቡሩንዲ የቀረበውን ሐሳብ ያልተቀበለው የአፍሪካ ሕብረት፣ እስካሁን ሌላ የጋራ ዕጩ አላፀደቀም። አገራቸው ሴኔጋልም የማኪ ሳልን ዕጩነት ከየሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ መቃወሟ ተ።መልክቷል።...more0minPlay
April 17, 2026ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቱ ስልክ ደውሎ ይወያያል ወይስ የጽሑፍና የድምፅ መልዕክት መላክ ያዘወትራል?በአሁን ዘመን አንድን ሰው ስልክ ደውሎ ማናገር ከመቼውም በላይ ቀላል ነው ፣ ይሁንና በእርግጥ ይህን እናደርጋለን? ወይስ የጽሁፍ ወይም የድምፅ መልዕክት መላኩ ይቀናናል? በተለይ ደግሞ በወጣቱ ዘንድ ያለው ተሞክሮ ምን ይመስላል?...more0minPlay
April 16, 2026የኢትዮጵያ እና በጀርመን መካከል ባህላዊዉ የቡና ድልድይ«የኢትዮጵያ ቡና እንደ ባህልም ነዉ። ኢትዮጵያ አረቢካ ቡና የተገኘበት ሃገርም ነዉ። ቡናዉ በራሱ የቱሪስት መስዕብ ነዉ። እኛ ኢትዮጵያዉያን ነን ብለን ስንናገር፤ ብዙዎች አረቢካ ቡና የተገኘበት ሃገር ይሉናል። ጀርመኖች ደግሞ ከሌላዉ ሃገር ይልቅ የኢትዮጵያን ቡና ነዉ መግዛት የሚፈልጉት፤ እንደ ቅመም ነዉ የሚጠቀሙበት ያደባልቁታል» ፈትያ ሹበርት...more17minPlay
April 16, 2026“ብትናገር ትሞታለህ” የተደራጁ ሰዎች ድብደባ የሚፈጽሙባት የአምቦ ከተማ ነዋሪበአምቦ ከተማ የተደራጁ ጉልበተኞች ሰዎች የሚደበድቡበት ድርጊት በርካቶችን አስደንግጧል። የከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት ጉዳዩ ቀድመው የሚያውቁት የተሳቀቁበት ድርጊት ነው። አንድ የከተማው ነዋሪ “ብትናገር ትሞታለህ” ሲሉ አደገኛ እንደሆነ ተናግረዋል። ሌላ ነዋሪ በበኩላቸው “መናገር አንችልም፤ ፈጣሪ እውነቱን ያወጣል ብለን ነበር ዝም ያልንው” ይላሉ።...more4minPlay
April 16, 2026የስምንት ሰዎች ሕይወት ባለፈበት የራያ ቆቦ የጎርፍ አደጋ ከ30 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀምየ8 ሰዎች ሕይወት ካለፈበት የራያ ቆቦ የጎርፍ አደጋ አሁንም ከ30 በላይ ሰዎች አሁንም የደረሱበት አይታወቅም ተባለ። በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ በሚገኝ ቤተ-ክርስቲያን የጸበል ሥፍራ አደጋው የደረሰው ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ነበር። በወቅቱ ከ50 እስከ 60 ሰዎች በቦታው ነበሩ ተብሎ እንደሚታመን የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.