Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.
April 03, 2026ኢትዮጵያ አሳካሁ ያለችው የ13 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት“ኢንቨስትመንት በሰበብ አይመራም” ያሉት ባለሙያው “በተጨባጭነት መሬት ላይ ያለው ነገር በተለይም ከሰላምና ጸጥታው ጋር ተያይዞ አገሪቱ ውስጥ የሚስተዋለው ጉዳይ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ አዎንታዊ ምልክት ነው ወይ” ሲሉም ጠይቀዋል፡፡...more0minPlay
April 03, 2026ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ነዳጅ የሚያጓጉዙ የጭነት አሽከርካሪዎች እንግልት"ጅቡቲ በጣም ሁሉም ነገር ውድ ነው። የሆቴል፣ የምግብ፣ እንደዚሁ መሰረታዊ ነገሮች፣ የምትወስዳቸው መድኃኒቶች ይኖራሉ። አንድ ሰው በቀን 1,500 እና 2,000 ብር ቢያወጣ፣ በወር ከ15 ቀን ቢቆይ ይሄን ብር ብታባዛው ቀላል ገንዘብ አይደለም።...more0minPlay
April 03, 2026የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የጉዞ ማሳሰቢያ እና ተጽዕኖው"እነዚህ ማስረጃዎች እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት በአብዛኛው ለምንፈልጋቸው፣ ለውጭ ኢንቨስትመንት፣ ለብድሮች ማስረጃዎች ሆነው ይቀርባሉ። የተበዳሪነት ተክለ ቁመና ከሚገመገምባቸው ኹኔታዎች ውስጥ አንዱ ሰዎች ምን ያህል ተንቀሳቅሰው ሥራን መሥራት ይችላሉ?" የሚለው መሆኑን በመጥቀስ ጉዳት ያለው ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።...more0minPlay
April 03, 2026መራጮች ምዝገባ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልየምዝገባው ሂደት ያለምንም ችግር እየተከናወነ እንደሚገኝ የጠቀሱት በኮቸሬ ወረዳ የፍሰሃ ገነት ምርጫ ጣቢያ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ አየለ በጣቢያው ከአንድ ሺህ በላይ መራጮችን ለመመዝገብ የታቀደ ቢሆንም እስከአሁን ግማሽ ያህሉን መመዝገባቸውን ገልጸዋል ፡፡...more0minPlay
April 03, 2026አዲሱ የኢትዮጵያ የወንጅል ስነስርዓት ሕግ ምን ጉዳዮችን አሻሽሎ መጣ?ሕጉ ትናንት በአብላጫ ድምጽ ከመጽደቁ አስቀድሞ በተለይም የኦሮምያ ክልል ፍርድ ቤቶች በአዲስ አበባ የዳኝነት ስልጣን እንዲኖራቸው የሚፈቅደው አንቀጽ 25 (3) ስር የተደነገገው ይዘት ጥያቄ አስነስቶ ነበር።...more0minPlay
April 02, 2026የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት የአፍሪካ አገራትን ገንዘብ ማዳከም ጀምሯል ።ሰነዱ፣ የበርካታ የአህጉሪቱ አገራት የገንዘብ የምንዛሪ መጠን ቅናሽ ማሳየቱን አመልክቷል። የበለጠ ተጋላጭ የሆኑት ነዳጅ አምራች ያልሆኑ አገራት መሆናቸውን፣የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሃፊና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቢሮ ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ ለዶይቼ ቨለ አስረድተዋል።...more0minPlay
April 02, 2026የስደተኞች ሰቆቃ የመን እና ሳውዲ አረቢያ ድንበር ላይከአማራ ክልል ፣በተለይም ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ እንዲሁም ከኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን በርካታ ወጣቶች በየዕለቱ በባህር ይጓዛሉ። የራያ ቆቦ ወረዳ ነዋሪ አቶ ዋሲሁን ምትኩ፣ በየዕለቱ በምንሰማው የልጆቻችን ሞት በሀዘን ላይ ሀዘን እየደረሰብን ነው ይላሉ። የአማራ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ወጣቶች ሕጋዊውን መንገድ እንዲጠቀሙ ያሳስባል...more0minPlay
April 02, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያን መምራት የጀመሩበት ስምንተኛ ዓመትየሰሜን ሸዋ ዞን ደብረጽጌ ከተማ ነዋሪ “ያለፉት ስምንት ዓመታት ምርታማነት ከፍ ያለበትና ነጻነታቸው የተከበረበት” መሆኑን ሲገልጹ ሌላ አስተያየት ሰጭ ደግሞ ቴክኖሎጂ ላይ የታዩ ለውጡች በመልካም የሚታዩ ናቸው” በማለት ይሁንና የሚያመዝነው ከስኬት ይልቅ ከሁሉም ቅድሚያ የሚሰጠው የሰላሙ ጉዳይ ፈተና ሆኖ መቆየቱን በአስተያየታቸው ገልጸዋል፡፡ “...more0minPlay
April 02, 2026ዶናልድ ትራምፕ ስለ ኢራን ጦርነት ለህዝባቸው ያስተላለፉት መልዕክትትራምፕ የኢራን ወታደራዊ አቅም መዳከሙንና አመራሮቿ መመታታቸውን እንደ ትልቅ ስኬት ጠቅሰዋል። «ጦራችንን ወደ አገራችን እንመልሳለን።» የሚለው ቃል ለደጋፊዎቻቸው ትልቅ ተስፋ የሰጠ ቢሆንም፣ የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋቱ ከቀጠለ ግን ኢራንን "ወደ ድንጋይ ዘመን" እንደሚመልሷት መዛታቸው ደግሞ ንግግራቸው አንድ የተጨበጠ አቅጣጫን ያልያዘ አስመስሎታል።...more0minPlay
April 02, 2026በትግራይ ክልል እና ውዝግብ ባለባቸው ቦታዎች የመራጮች ምዝገባ ምን ይመስላል?ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድባቸውን አካባቢዎችን "የፀጥታ ኹኔታ" በተመለከተ ከወራት በፊት "ከባለድርሻ አካላት ጋር" ባደረገው ውይይት የትግራይ ክልል ኹኔታ አለመቅረቡን የነገሩን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር አቶ ፅጋቡ ቆባዕ ትግራይ ክልል የመራጮች ምዝገባን ጨምሮ የምርጫ ሥራ እንቅስቃሴ እየተስተዋለ አይደለም።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.