Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.
April 02, 2026የባሕል መድረክ፣ አቶ ኪዳኔ ዓለማየሁ፣ የመብት ተሟጋችና ዲፕሎማትአቶ ኪዳኔ፣ በ1979 ወደ ታንዛኒያ ተዛውረው በዋና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ በመሆን አገልግለዋል:: በ1981 ከታንዛኒያ ወደ ኬንያ ተዛውረው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰዎች ማሥፈር ማዕከል ዋና መ/ቤት (UN Habitat) ሰርተዋል...more0minPlay
April 01, 2026የትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የጉባኤ ተሳታፊ ልየታ ክልሉ ውስጥ እንዲደረግ ተጠየቀየኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ለሥራው "አስቻይ ኹኔታ" እንደሌለ ገልፆ የክልሉን አጀንዳ ለማሰባሰብ እና የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎችን ለመለየት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ምክክር ከፍቷል።...more0minPlay
April 01, 2026የነዳጅ እጥረት በሐዋሳ ያሳደረው የኑሮ ጫናየሰሞኑ የመካከለኛው ምሥራቅ አለመረጋጋት ወትሮም በአቅርቦት እጥረት ሲፈተን የቆየውን የነዳጅ ሥርጭት አባብሶታል ፡፡ በተለይም በአገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች አሽከርካሪዎች ለቀናት በወረፋ ተሰልፈው ውለው እያደሩ ነው ፡፡ በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች ሁኔታው በኑራቸው ላይ ተፅኖ እያሳደረባቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡...more0minPlay
April 01, 2026ቲክ ቶክ፣ ፌስቡክ እና ዩቱዩብ ሱስ የሚሆኑት ለምንድነው?እንደ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ እና ቲኮክ ያሉ ዲጅታል መድረኮች ለተግባቦት ብቻ የሚያገለግሉ ዲጅታል መድረኮች ብቻ አይደሉም። ባለሙያዎች እንደሚሉት እነዚህ ዲጅታል መድረኮች ትኩረታችንን ለመሳብ እና ይዞ ለማቆየት ጭምር በጥንቃቄ የተነደፉ ናቸው።ለተጠቃሚዎቹ መረጃ የሚጠቁሙበት እና ለፍላጎት የሚስማሙ ይዘቶችን የሚያቀርቡበት መንገድም በዚህ የተቃኘ ነው።...more0minPlay
April 01, 2026የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዲሱ “የህገወጥ ቤቶች ግንባታ” ደንብ ምን ይዞ መጣ?የኦሮሚያ ክልል በተለምዶ “ጨረቃ ቤት” ወይም “ህገወጥ የቤቶች ግንባታ” ተብለው የሚታወቁትን የቤቶች ግንባታ ህጋዊ ለማድረግ የሚያስችለውን ህግ ይፋ አድርጓል፡፡ ለአንድ ዓመት ብቻ የሚቆይ የተባለው ይህ ህግ ከከተሞች አብይ ፕላን ጋር የማይጋጩትን ይዞታዎች ህጋዊ በማድረግ ካርታ እንዲያገኙ የሚፈቅድ ስለመሆኑም ታውቋል፡፡...more0minPlay
April 01, 2026የኢራን ጦርነት በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ላይ “አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ይጠበቃል”በኢትዮጵያ የነጭ ናፍጣ አቅርቦት በአማካይ በቀን ከ9.2 ሚሊዮን ሊትር ወደ 4.5 ሚሊየን ሊትር ቀንሷል። ሀገሪቱ የኢራን ጦርነት ሲቀሰቀስ የገዛችውን 180,000 ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ማስገባት አልቻለችም። በወር ከ15 እስከ 20 ቢሊዮን ብር ለነዳጅ ለመደጎም መገደዱን የገለጸው መንግሥት ዜጎች “ቅድሚያ የማይሰጣቸው ጉዞዎች እንዲሰርዙ” መክሯል።...more0minPlay
April 01, 2026ገቢና ወጪ ሸቀጦችን የሚያጓጉዙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ሥራ በምን ኹኔታ ላይ ይገኛል?አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን የከፈቱትን ጦርነት ተከትሎ ቀውሱ በነዳጅ ምርት ግብይት ዋጋም ሆነ አቅርቦት ላይ ጉልህ መስተጓጎል ፈጥሯል። ጅቡቲ የኢትዮጵያ ዋናዋ የገቢ እና ወጪ ንግድ መስመር ስትሆን ሀገር አቋራጭ የረጅም ርቀት ከባድ ተሽከርካሪዎች ደግሞ የዚህ ኃላፊነት የጀርባ አጥንት ናቸው።...more0minPlay
March 31, 2026የሶሪያው ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት የጀርመን ጉብኝት እና ጀርመን 80 በመቶ የሶሪያ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የያዘችው እቅድየሶሪያውን ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አል-ሻራን በርሊን ያስተናገዱት ሜርስ እንደሚሉት ወደ ሀገራቸው መመለስ ያለባቸው በጀርመን የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ሶሪያውያን ናቸው። ሆኖም እዚህ መስራት የሚችሉ ነገር ግን ሀገራቸው ቢመለሱ ለሀጋራቸውም አስተዋጽኦማድረግ የሚችሉ ሶሪያውያን አሉ። በሜርስ አስተያየት በነዚህ ሰዎች ጉዳይ ላይም መነጋገር ያስፈልጋል።...more12minPlay
March 31, 2026የኢራን ጦርነት በአውሮፓ ሐገራት ያሳደረው ጫናበርካታ የአውሮፓ ሕብረት አባል ሐገራት በግልም ሆነ በሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ATO) በኩል የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን ለማስከፈት በሚደረግ ጦርነት ተሳትፎ እንደማያደርጉ አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል።...more4minPlay
March 31, 2026«ማደያ ላይ ሁለት-ሶስት ቀናትን አድረን ነዳጅ አለቀ እንባላለን»«በከባድ መኪና እቃ ነው የምናጓጉዘው፤ አሁን ነዳጅ ጥበቃ በተሰለፍንበት የተመለከትኩት ሁለት አይሱዙ የጭነት መኪና ቲማትም እንደጫኑ እላያቸው ላይ ሲበሰብስ ተመልክቻለሁ»...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.