Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.
March 26, 2026ድንገተኛ በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብበደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ 01 አዲስ መንደር ቀበሌ ከትናንት በስቲያ የጣለ ድንገተኛ በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ፣ በ60 ሄክታር መሬት ላይ የነበረን የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ሙሉ በሙሉ ማውደሙ ተገለጠ። ማሳው ላይ የነበረ ፓፓዬ፣ ድንች፣ የበርበሬና የማንጎ ተክሎች ቅጠላቸውንና አበባው ረግፎ እንጨታቸው ብቻ መቅረቱ ተገልጧል ።...more0minPlay
March 26, 2026የአፍሪቃ ኅብረት ቀይ ባሕርን ያካተተ የልዩ መልዕክተኛ ሹመት ሰጠየአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሹመት የቀይ ባሕርንም እንዲያካትት መደረጉ "በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ቀንድ ያለው ሁቴታ ውስብስብነት ነፀብራቅ ነው" ሲሉ ዶይቼ ቨለ ያነጋገራቸው የጸጥታ ጉዳዮች ተንታኝ አስረድተዋል።...more0minPlay
March 26, 2026በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስላሉበት ኹኔታ ምን ይላሉ?ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል ከኢራን ጋር ጦርነት ከጀመሩ 26 ቀናት ተቆጥረዋል። ጤርነቱ ብርቱ ውድመትም አስከትሏል። ኢራን ከእስራኤል ባለፈ የአሜሪካ እና የእስራኤል አጋር ወደሄኑ የገልፍ ሀገራት ጭምር ሚሳኤሎችን በመተኮስ በልዩ ልዩ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት አድግሳለች።...more0minPlay
March 26, 2026ከታተመ 60 ዓመት የሞላዉ ፍቅር እስከ መቃብርፍቅር እስከ መቃብር ረዥም ልብ ወለድ የታተመበትን 60ኛ ዓመት የሚዘክር መርሐ-ግብር ባለፈው ሣምንት በአዲስ አበባ ተካሒዷል። በሀዲስ አለማየሁ የተጻፈው ፍቅር እስከ መቃብር በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ዘመን አይሽሬ ከሚባሉ ሥራዎች መካከል አንዱ ነው።...more0minPlay
March 26, 2026በርዳታ አቅርቦቱ እጥረት ተፈትነናል ያሉት የትግራይ ክልል ተፈናቃዮችበትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች የምግብ ርዳታ በማጣት ለረሐብ መዳረጋቸውን ወደ ሦስት መቶ የሚጠጉ ተፈናቃዮች ደግሞ በቅርቡ በበሽታ ምክንያት ለሞት መዳረጋቸውንውን ገለጡ ። መንግስት ዘለቄታዊ እልባት በማፈላለግ ወደ ቀዬያቸው እንዲመልሳቸውም ተፈናቃዮቹ እየተማጸኑ ነው፡፡ ሙሉ ዘገባውን በድምፅ እና በጽሑፍ በማገናኛው ማግኘት ይቻላል ።...more0minPlay
March 25, 2026ስለምርጫው የታጣቂዎች ማስጠንቀቂያ እና የፓርቲዎች አቋምበአማራ ክልል ክልል የታጠቁ አካላት በዘንድሮ የኢትዮጵያ ምርጫ ተሳትፎ ላይ ማስጠንቀቂያ ከሰጡ ከሳምንት በኋ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ-ኦነሰ) ምርጫውን ተዓማኒነት የሚጎድለው ነው ብሏል፡፡ በሁለቱ የአገሪቱ ትላልቅ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎቹ ያወጧቸው መግለጫዎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አሳስቧል።...more4minPlay
March 25, 2026"ከምርጫ ራሳችንን እስከማግለል ርምጃ ልንወስድ እንችላለን" - የ4 ፓርቲዎች ቅንጅትትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ሙሉ በሙሉ፣ በኦሮሚያ ክልል በከፊል እንዲሁም በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል-መተከል ዞን ያለው የምርጫ አስቻይ ኹኔታ ካልተስተካከለ ከምርጭ ራሳችንን ልናገል እንችላለን"ሲል ገለፀ። ቅንጅቱ በእነዚህ አካባቢዎች ዋስትና እስካላገኘ ድረስ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከማድረግ እቆጠባለሁ"ብሏል።...more4minPlay
March 25, 2026የቀድሞው የታንዛኒያ ፕሬዝደንት ጃክያ ኪክዌቴ የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባሕር ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ተሾሙየአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የቀድሞው የታንዛኒያ ፕሬዝደንት ጃክያ ኪክዌቴን የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባሕር ልዩ መልዕክተኛ አድርገው ሾመዋል። የ77 ዓመቱ ኪክዌቴ “ተለዋዋጭ” ለሆነው የቀጠናው “ውስብስብ የፖለቲካ፣ የሰላም እና የጸጥታ” ሁኔታ መፍትሔ ለማፈላለግ የአፍሪካ ኅብረት የሚያደርገውን ጥረት ይደግፋሉ።...more6minPlay
March 25, 2026የዋሽንግተን እና የቴህራን ዲፕሎማሲ እንቅስቃሴአሜሪካ እና ኢራን ድርድር ሊካሄዱ ነው የሚሉ እየወጡ ይገኛሉ።ይህንን መረጃ ግን አንድ የኢራን ወታደራዊ ቃል አቀባይ በተለቀቀ ቪዲዮ ዩናይትድ ስቴትስ ከራሷ ጋር እየተደራደረች ነው ሲሉ አጣጥለዋል።ያም ሆኖ ሁለት የፓኪስታን ባለስልጣናት ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ከአሜሪካ የ15 ነጥብ ሀሳብ ቀርቦላታል ሲሉ ገልፀዋል።...more4minPlay
March 25, 2026በአማራ ክልል ያለው የነዳጅ ዘይት እጥረትና ድብቅ ገበያነዳጅ ከማደያዎች ውጪ በሊትር ደሴ 350 ብር፣ በዳባት 900 ብር መሸጡን አሽከርካሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በጎንደር እና ባሕር ዳር በነዳጅ ማደያዎች ለወረፋ ከ2,000 እስከ 10,000 ብር የተከፈለባቸው ቀናት አሉ። በአማራ ክልል የነዳጅ እጥረት እና የዋጋ ለውጥ በግብርና እና በኢንዱስትሪ ምርቶች መሸጫ ላይ ጭማሪ አስከትሏል።...more11minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.