Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.
March 18, 2026ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው በዋስትና እንዲፈቱ የተላለፈውን ውሳኔ ሻረየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው በዋስ እንዲለቀቁ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ ዛሬ ውድቅ አደረገው። የካቲት16 ቀን 2018 ዓ.ም. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ100 ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ብይን የሰጠ ቢሆንም በወቅቱ ከማረሚያ ቤት ሲወጡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል።...more0minPlay
March 18, 2026በአማራ ክልል የነዳጅ ዘይት እጥረት የፈጠረው የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎልበመካከለኛው ምስራቅ ካለው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ የመጣው የነዳጅ አቅርቦት እጥረት በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ክፉኛ እየፈተነው ይገኛል። በተለይም የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመጓዝ የወጡ በርካታ መንገደኞች በመናኸሪያዎች ተስተጓጉለዉ እንደሚገኙ ታውቋል።...more0minPlay
March 18, 2026አሳሳቢው የኦሮሚያ ግጭት ማቆሚያው የት ይሆን?አስተያየታቸውን ለዶይቸ ቬለ የሰጡ የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤዶንጎሮ ወረዳ ነዋሪ ወጣት በምዕራብ ኦሮሚያ በ2011 ዓ.ም. የተጀመረው የግጭት ወላፈን መልኩን እየቀያየረ፤ አንዴ ጋል ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀዝቀዝ ቢልም በሂደቱ ማህበረሰቡ በከፍተኛ ሁኔታ ውስጥ እያሳለፈ ነው ይላሉ፡፡...more0minPlay
March 18, 2026የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ፣በትምህርት እና ጤናየሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ፣በዓለም ላይ ከዐይን ጥቅሻ በፈጠነ ሁኔታ እያደገ ይገኛል። ይህንን በፍጥነት እያደገ ያለ ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ ውስጥ በጤና እና ትምህርት ዘርፍ ጥቅም ላይ ለማዋል እና የስልጠና ድጋፍ መሆኑን ፒፕል ቱ ቲፕል የተባለው ተቋም ገልጿል።ተቋሙ በኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አሜሪካ ውስጥ የተቋቋመ ነው።...more0minPlay
March 18, 2026የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም ቢያንስ በአንድ በመቶ ቅናሽ ማሳየቱየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ትናንት ማክሰኞ መጋቢት 08 ቀን 2018 ዓ.ም. ባከናወነው መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ላይ የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ከቀረበው የ70 ሚሊየን ዶላር አኳያ ከሶስት እጥፍ በላይ ብልጫ አሳይቷል።...more0minPlay
March 17, 2026የጀርመን የምርጫ ስርዓትና የኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች የጀርመን ጉብኝትከኢትዮጵያ ፣ የተለያዩ መገናኛና ብዙሀን የተውጣጡት ጋዜጠኞች በመጪው እሁድ የአካባቢ ምርጫ በሚካሄድበት በጀርመንኛ መጠሪያው በራይንላንድ ፋይልስ በእንግሊዘኛው በራይንላንድ ፕላቲኔት ፌዴራዊ ግዛት ዋና ከተማ ማይንዝ ተገኝተው የምርጫ ሂደቱን፣ የምርጫ ዘመቻዎችንና ፣የቴሌቪዥን ክርክርም በአካል ተገኝተው ተከታትለዋል።...more0minPlay
March 17, 2026የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር ምሥረታ በካናዳካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ሰሞኑን ማኅበር መመስረታቸውን ገልፀዋል።የማኅበሩ ሊቀመንበር ገዛኸኝ መኮንን፣ለዶቸ ቬለ እንዳስታወቀዉ፣ማኅበሩ የጋዜጠኞችን መብት ለማስከበር፣የሙያ አቅማቸውን ለማሳደግና አመቺ የሥራ ሁኔታን ለመፍጠር ይጥራል።...more0minPlay
March 17, 2026በኢትዮጵያዉያን ሴቶች ላይ የተፈፀመ በደልና የፍትሕ ጥያቄድርጅቶቹ በሴቶች ላይ የደረሱ ያሏቸው ጥሰቶችን የጊዜ ማዕቀፍ ባይገልፁም፣በኢትዮጵያ ተከስቷል ያሉት ሰብአዊ ቀውስ "ሴቶችን እና ልጃገረዶችን ባልተመጣጠነ ሁኔታ ጎድቷል" ብለዋል።...more0minPlay
March 17, 2026የኢዜማ እና የዎህዴግ የምረጡኝ ቅስቀሳየኢትዮጵያ ለማህበራዊ ዜጎች ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ እንደአጠቃላይ የፓርቲው ማኔፌስቶ አሥር ነጥቦች ላይ ትኩረት መስጠቱን ዶክተር አወቀ ተናግረዋል ፡፡ አገረ መንግሥት ግንባታ ፣ ሰላም እና ፀጥታ ፣ማህበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮች ዋነኞች መሆናቸውን የጠቀሱት ዶክተር አወቀ ” ነገር ግን በምንወዳደርበት ኮሬ ዞን የሚታየው ዋናው የፀጥታ ችግር ነው...more0minPlay
March 17, 2026የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትና የአፍሪቃ አቋምየመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ የአፍሪካ አገራት የጋራ የኾነ መግለጫ አላወጡም። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዮሱፍ ግን ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጥቃት እንደዚሁም ኢራን በባሕረ ሰላጤው አገረት ላይ የፈፀመችውን ጥቃት የሚያወግዝ መግለጫ አውጥተዋል...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,874 episodes available.