ከመጽሐፍት ዓለም፡ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ሥራዎች (በካፍትሌ ቶራይቶ የቀረበ ልዩ ዝግጅት)
ነጋድራስ ገብረ ሕይት ማን ነው?
በ1878 ዓ.ም በአድዋ ተወለደ
በልጅነታቸው ወደ ኤርትራ በመሄድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታተሉ
ከዚያን በመርከብ ውስጥ ተደብቀው ወደ አውስትራሊያ ሄደው የሕክምና ትምህርታቸውን ከመከታተላቸው በተጨማሪ ከሠለጠነው የምዕራቡ ዓለም ጋር ተዋወቁ
ወደ አገራቸው ተመልሰው አጼ ምንሊክን በሕክምና ለመረዳት ሞከሩ፣
ወደ ሱዳን ተሰደዱ
ወደ አገራቸው ተመልሰው ነጋድራሰ ሆኑ፡፡
ሁለት መጽሐፍ ጻፉ፡ 1ኛ) አጤ ምንሊክና ኢትዮጵያ 2ኛ) መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር
ታርክን መማር እጅግ ይበጃል፣ በተለይ ለመሪዎች
ከድንቁርና ወጥቶ ከፍ ባለ ህሊና ተመርቶ ለዜጎች ልማት የሚጥር እርሱ እርኩስ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
ደግሞም እንደ አገራችን ሰው ትምህርት የሌለው ሕዝብ እውነትቱን ሲሰማ አይወድም፣ ሲሰማም አይገባውም፡፡
አእምሮን በአእምሮ ካልሆነ በቀር በሌላ አትታደግም
አርነት ማለት የራስን መንግስት ማቋቋም ብቻ ሳይሆን ራስን መቻልንም ይጠይቃል፡፡