Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀር... more
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 340 episodes available.
October 07, 2024ሃማስ እስራኤልን ያጠቃበት ጥር 7 ፤ 2023 ሲታወስጋዛ እንዳልነበረች ሆናለች ፤ ሊባኖስ የጋዛ መንገድ የተከተለች መስሏል ፤ ሞት እና ውድመት እዚህም እዚያም ይሰማል ፤ ከኢራን እና ከምትደግፋቸው ታጣቂዎች ከኋላ እና ከፊት የሚሳኤል እና የሮኬት ዝናብ የሚዘንብባት እስራኤል በቆሰለች ቁጥር ቁጣዋ እያየለ የምትወስደው እርምጃም ሰላማዊን ከጦረኛ ሳይለይ እንዳነፈረ እነሆ አንድ ዓመት ደፈነ ።...more15minPlay
September 30, 2024ማሕደረ ዜና፣ መካከለኛዉ ምሥራቅ ደም ጠጥቶ ደም የሚጠማዉ ምድርየአረብ መሪዎች ይርመጠመጣሉ፣ ኢራን ትፎክራለች።ሐማስ ይሽሎኮሎካል፣ ሒዝቡላሕና ሑቲዎች ይፍጨረጨራሉ።ፍልስጤም ያልቃል።እስራኤል፣ ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ እንዳሉት በረጅም ምህረት የለሽ እጇ፣ ሲሻት ጋዛን፣ ሲያሰኛት ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻን፣ ሲፈልጋት ሊባኖስን፣ ካሰኛት ሁዴይዳሕን፣ ቴሕራንን፣ ደማስቆን ታጋያለች...more15minPlay
September 16, 2024አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያዉያን ምን ይዞላቸው መጣ? ተስፋ ወይስ የቀጠለ ስጋት ?ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም ሰባት ዓመታት ከመንፈቅ ገደማ ወደ ኋላ የምትቀርበት የዘመን ቀመር 2017 ላይ ደርሶ እነሆ 2016 አሮጌ ሆኖ ለአዲሱ ዓመት ተሸጋገረች ። በእርስ በርስ ግጭት ጦርነት ውስጥ ያለችው ሀገር ከአንዱ የግጭት ጦርነት ምዕራፍ ወደ ሌላው እየተሸጋገረች ዓመታቱም ሂያጁ ለመጪው እየለቀቁ ቀጥለዋል።...more13minPlay
September 04, 2024ቃለ መጠይቅ፣ የሶማሊያና የግብፅ ወታደራዊ ዝግጅት ያስከተለዉ ሥጋትግብፅ ከዚሕ በተጨማሪ በመጪዉ ታሕሳስ ባዲስ መልክ ይዋቀራል ለተባለዉ በሶማሊያ የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት 5000፣ ለሶማሊያ መንግሥት በቀጥታ ድጋፍ የሚሰጥ ሌላ 5000 ጦር ኃይል ሶማሊያ ዉስጥ ለማስፈር ማቀዷም በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።የሶማሊያና የግብፅ ጦር ኃይላት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ እየተዘጋጁ መሆናቸዉም ተነግሯል...more19minPlay
August 19, 2024የህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንትን ከምክትል ሊቀመንበርነት አሰናብቶ ተጠቀቀ-ከዚያስ?ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ አመራሮቹን ለውዝግብ የዳረገውን ጉባኤ ሲያጠናቀቅ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በሊቀ-መንበርነታቸው ቀጥለዋል። አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊቀ-መንበር ሆነው አቶ ጌታቸው ረዳን ተክተዋል። ለህወሓት አዲስ የሥራ አስፈፃሚ፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እና ቁጥጥር ኮሚሽን የተመረጠበት ጉባኤም ይሁን ውጤቱ ግን በምርጫ ቦርድ እውቅና አልተሰጠውም። በህወሓት መሪዎች መካከል የተፈጠረው ልዩነት የፖለቲካ መሪዎች እና ነዋሪዎችን አስግቷቸዋል።...more14minPlay
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 340 episodes available.