Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀር... more
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 339 episodes available.
May 25, 2026ማሕደረ ዜና፣ ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን ይደራደራሉ፣ ይግባባሉ፣ ይዛዛታሉምባለፈዉ ቅዳሜም የሆርሙዝ ወሽመጥ እንደሚከፈት ለዓለም ነጋዴ «እንቁልልጭ» በማለታቸዉ የነዳጅ ዘይት ዋጋ እንዲያሽቆለቁል አድርገዋል።እዉነቱ ግን «ባጭር ጊዜ» በይፋ ይደረጋል ያሉት ሥምምነት ቅዳሜም አልነበረም ዛሬም የለም።ወይም የአጭር ጊዜ ብያኔ አይታወቅም።ትራምፕ በመሐሉ ትናንት በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴያቸዉ ባሰራጩት መልዕክት ኢራን ካልተስማማች ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን ወደቦች በሚነሱ መርከቦች ላይ የጣለችዉን እገዳ እንደማታነሳ ዝተዋል።...more13minPlay
May 18, 2026የኢትዮጵያ እና ሱዳን ፍጥጫ ወዴት እያመራ ነው?የሱዳን ብሔራዊ ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የሚያደርጉት ውጊያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ወደሚገኝበት ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የበለጠ በመጠጋት ላይ ይገኛል። የሱዳን ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር “የሁለትዮሽ መዋቅራዊ የውይይት ማዕቀፍ” ሥምምነት የተፈራረመችው አሜሪካ በዐይነ-ቁራኛ የምትከታተለው ነው። አሜሪካ ግንቦት 24 ቀን 2018 ይካሔዳል ተብሎ ከሚጠበቀው ምርጫ በኋላ ኢትዮጵያ እና ግብጽን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ማደራደር ትጀምራለች ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ጦርነት እንዲቀሰቀስ እንደማትሻም አስታውቃለች።...more14minPlay
May 11, 2026ማሕደረ ዜና፣ ዩናይትድ ስቴትስ-እስራኤልና ኢራን በጦርነትና ዲፕሎማሲ መሐልለኔታንያሁ ሰበብ ሆኑ ትክክለኛ ምክንያቶች ሐመስ፣ ሒዝቦላሕ፣ሁቲ ጭፍራ፣ ኢራን ዋና የሽብር ማዕከል ናቸዉ።የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል መሪዎች ዋና ጠላት የሚሏትን ኢራንን ለማንበርከክ አምና ሰኔ ሞክረዋታል።አልተሳካም።ዘንድሮ ከየካቲት ማብቂያ እስከሚያዚያ ቀጥቅጠዋታል። የትራምፕ-ኔታንያሁ ዕቅድ፣ፉከራ፣ ዛቻ ምናልባት አንዳዶች እንደሚሉት ለሽንፈት እንጂ ለድል አልበቃም።7000 ዘመናት ያስቆጠረዉን የኢራንን ሥልጣኔ ለማዉደም ትራምፕ ፎክረዉም ነበር።አልቻሉም።...more14minPlay
May 04, 2026የትግራይ ክልል አዲስ ፕሬዝደንት አዲስ ሥራ አስፈጻሚ እየጠበቀ ነው-ግጭት የማቆም ሥምምነቱስ?በህወሓት ውሳኔ መሠረት በጳጉሜ 2012 በተካሔደው እና ፌድራል መንግሥት “ሕገ-ወጥ” ባለው ምርጫ የተመሠረተው የትግራይ ክልል ምክር ቤት በመጪዎቹ ቀናት ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል። የምክር ቤቱ ወደ ሥራ መመለስም ይሁን የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች የትግራይ ክልል እና የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ቀጣይ ግንኙነት ምን እንደሚመስል የሚበይኑ ይሆናል።...more17minPlay
April 20, 2026ሱዳን “የጭካኔ ቤተ-ሙከራ” የሆነችበት ጦርነት አራተኛ ዓመቱን ጀመረበሱዳን ጦርነት በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በድሮኖች ጥቃት ጭምር ተገድለዋል። ጦርነቱ አራተኛ ዓመቱን ሲጀምር 34 ሚሊዮን ሰዎች ሰብአዊ ርዳታ ይጠብቃሉ። ሀገሪቱን ለሁለት የከፈላትን ጦርነት ለማቆም የሚደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። ጦርነቱ ከሱዳን ድንበር በመሻገር ወደ ጎረቤት ሀገሮች ተዛምቶ “ከቁጥጥር ውጪ” ሊሆን እንደሚችል ሥጋት አለ። የሱዳን ብሔራዊ ጦር አዛዥ ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል-ቡርኻን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች አዛዥ መሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ጦርነቱን ለማቆም እስካሁን ተጨባጭ ፈቃደኝነት አላሳዩም።...more12minPlay
April 06, 2026ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ ስድብና ዛቻ፣ ያበደዉ ማን ይሆን?የኢራን ትምሕርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የመድሐኒት ፋብሪካዎች፣ ድልድዮች፣ ዩኒቨርስቲዎች ሳይቀሩ ወድመዋል።የእስራኤልና የመካከለኛዉ ምሥራቅ የአረብ ሐገራት በርካታ የኃይልና የሰላማዊ ተቋማት ተመትተዋል።ከሁሉም በላይ ምትክ የሌለዉ ከአራት ሺሕ በላይ ህይወት ጠፍቷል።በአንዳዶች ግምት በትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ አንድም ጠፍቷል ሁለትም ከስሯል።ትራምፕም ግን ነገ ማክሰኞ የኢራን የመሰረተ ልማት ተቋማት የሚፈራርሱበት ቀን እንደሆነ አዉጀዋል።ባለፈዉ ሳምንት ለኢራኖች የሚገባዉ «የድጋይ ዘመን ነዉ» ያሉት ትራምፕ ትናንት ኢራኖችን «እብድ፣ ዲቃሎች» በማለትም ባደባባይ ተሳድበዋል።ያበደዉ ማን ይሆን?...more15minPlay
March 23, 2026እስራኤል እና አሜሪካ ከኢራን የገጠሙት ጦርነት እንዴት እና መቼ ይቆማል?ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሣምንት አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን የገጠሙት ጦርነት መቼ እንደሚቆም ሲጠየቁ “እስከ አጥንቴ ዘልቆ ሲሰማኝ” የሚል መልስ ሰጥተዋል። መልሳቸው የጦርነቱን መቋጫ ለሚናፍቁ ማስተማመኛ የሚሰጥ አይደለም። ተንታኞች 24ኛ ቀኑን ያስቆጠረው ጦርነት የሚቆምበት ጊዜ እና ሁኔታ እጅግ ውስብስብ እንደሆነ ሥጋት አላቸው።...more13minPlay
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 339 episodes available.