Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀር... more
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 339 episodes available.
October 27, 2025ማሕደረ ዜና፣ የASEAN ጉባኤ፣ የትራምፕ ጉብኝትና የሲኖ-አሜሪካ ድርድርቤጂንጎች ሲያመሩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ «የንግድ ጦርነት ቀላል ነዉ አልኩ እንጂ---ከቻይና ጋር ማለቴ አልነበረም» ማለታቸዉ ተዘገበ።ዘ-ኤኮኖሚስት የተሰኘዉ መፅሔት ደግሞ በቀደም «ቻይና በትራምፕ ዱላ አሜሪካናንን ደበደበች» አለ።የሁለቱ ሐገራት የንግድና የኤኮኖሚ ባለሥልጣናት ሰሞኑን ለ5ኛ ዙር እየተደ,ራደሩ ነዉ።የቻይና ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ጉዮ ጂያኩን ዛሬ እንዳሉት ዉይይቱ የሰከነና መግባባት የታየበት ነዉ።...more14minPlay
October 20, 2025ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ሶማሊላንድ ጥልፍልፍየኢሮ ጉብኝት ባለፈዉ ሐሙስ ሲጠናቀቅ የበርበራ ወደብን የሚገነባዉ፣ DP ወርልድ የተባለዉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኩባንያ፣ መርከቦች ከርበራ ወደብ ጀበል ዓሊ ወደተባለዉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ወደብ እና በተቃራኒዉ መጓዝ መጀመራቸዉን አስታዉቋል። በኢትዮጵያ-ሶማሊያና ሶማሊላንድ መሪዎች ጉብኝት፣ ዉይይት፣ የፖለቲካ ጥልፍልፉ የአቡዳቢና የካይሮ ገዢዎች በቀጥታም በተዘዋዋሪም ጫና ማድረጋቸዉ የተሠወረ አይደለም።ይሁንና የሶማሊላንድ ዲፕሎማቶች በግል እንዳሉት ኢሮ የመሩት የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ በኩል የቀረበለትን የሶማሊያ ፕሬዝደንትን ሥልት አልተቀበለዉም።ጉብኝቱም ባጭሩ ተጠናቅቋል።ምናልባት እስከሚቀጥለዉ ጊዜ።...more14minPlay
October 13, 2025ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት የቃላት ጦርነት ንሯል።ይዋጉ ይሆን?ኢትዮጵያ ዘንድሮ የሕዳሴ ግድብን አስመርቃለች።፣የካሉብ ጋዝ ማምረቻና የማደባሪያ ፋብሪካን የመሠረት ድንጋይ ጥላለች።አማራ ክልል ከፋኖ፣ ኦሮሚያ ክልል ከኦነሠ ወይም OLA ጋር የሚደረገዉ ዉጊያ አሸናፊና ተሸናፊ ሳይለይበት እንደቀጠለ ነዉ።የኢትዮጵያ ምናልባትም የኤርትራ ክረምት ግን አብቅቷል።ዓየሩ ለወታደራዊ ንቅናቄ ይመቻል።እና ይዋጉ ይሆን?...more15minPlay
October 06, 2025ማሕደረ ዜና፣ የእስራኤል መጠቃት፣ የጋዛ ጦርነትና ድርድር 2ኛ ዓመትሕዝባቸዉ በየአደባባዩ የሚያደርገዉ ግፊት የጠናባቸዉ የምዕራብ አዉሮጳ መሪዎች እየተግተለተሉ ለፍልስጤሞች የመንግሥትነት እዉቅና ሰጡ።ኔታንያሁ በሚጭሩት ጦርነት ዘለዉ በመግባት ወይም ለኔታንያሁ መንግስት ፍፁም ድጋፍ በመስጠታቸዉ ምክንያት አረብ-ሙስሊም እየራቃቸዉ፣ ሕዝብ እየተከፋባቸዉ፣ ከተቀረዉ ዓለምም እየተነጠሉ የመጡት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጥብቅ ወዳጃቸዉን ኔታንያሁን በቅርቡ «በቃሕ» አሉሏቸዉ።ወይም ያሉ መሰሉ።...more15minPlay
September 29, 2025ማሕደረ ዜና፣ ዓለም መሪዎች እየተግባቡ ይሆን ወይስ ግራ እያጋቡሰዉዬዉ ከመቸኮላቸዉ የተነሰ በእስራኤል ላይ የሚለዉን በኢራን ላይ የተቃጣ አደጋ ብለዉት ነበር።ቸኩለዉ አሉት።ፈጥነዉ አረሙት።ኔታንያሁ እስራኤል ከመጥፋት አደጋ፣ ዓለምም ከመገደል ሥጋት ድኗል ቢሉም የለንድን፣ የፓሪስና የበርሊን መሪዎች አልተቀበሉትም። እንደ አሜሪካ ሁሉ የእስራኤል የቅርብ ወዳጆች፣ የኢራን ጠላቶች ፈረንሳይ፣ ብሪታንያና ጀርመን የኢራን የኑክሌር መርሐ-ግብር ያሰደረዉ ሥጋት አልተወገደም ይላሉ።ወይም የኔታንያሁን ማረጋገጪያ አላመኑትም።በሶስቱ ሐገራት ግፊት የተሰየመዉ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በኢራን ላይ ዳግም ዓለም አቀፍ ማዕቀብ እንዲጣል ወስኗል።...more14minPlay
September 22, 2025ማሕደረ ዜና፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ80 ዓመት አዛዉንት ወይስ ጨቅላ?ዓለም ከአንድ ሐገር የአዉቶሚክ ሥጋት ወደ ዘጠኝ ሐገራት የኑክሌር ሥጋትና ፍጥጫ ያደገችበት 80 ዓመት የሰላም ዘመን ነበር ማለት ይቻል ይሆን? አንዳድ ጥናቶች እንደጠቆሙት የጋራ ማሕበር ከተመሠረተ ከ1945 ወዲሕ ዓለም ከ300 በላይ ከባድ ጦርነቶችን አስተናግዳለች።በአብዛኞቹ ጦርነቶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መስራች፣ የዓለም ልዕለ ኃያላን መንግሥታት በቀጥታም በተዘዋዋሪም ተካፍለወል።----ዛሬም ከሱዳን እስከ ጋዛ፣ ከዩክሬን እስከ ኮንጎ ዴምክራቲክ ሪፐብሊክ ዓለም ሰላም የላትም...more16minPlay
September 15, 2025ማሕደረ ዜና፣ ዝክረ-2017 ዓበይት ፖለቲካዊ ክንዉኖች2017 ኤርትራን፣ ሶማሊላንድን፣ ሶማሊያንና ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር አስማማም-አጣላ፣ ቱርክን ለሽምግልና ጋበዘም-ጣልቃ አስገባ፣ከበኒ ሻንጉል ጉሙዝ እስከ አዲስ አበባ ኢትዮጵያዉያንን አስደሰተም-አስከፋ ሰበብ ምክንያቱ ሁለትም-አንድም ነዉ ወደብና ግድብ።ዉኃ።በ2017 የኮሪደር ልማትን አዲስ አበባ ላይ ክፉኛ የተፈተነዉ ጎርፍ ነዉ።-ዉኃ፣ወለጋና ደቡብ ኢትዮጵያ ላይ በትንሹ 10 ሰዎችን የገደለዉ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ላይ ሺዎችን ያፈናቀለዉ፣ ደቡብ ወሎ ዉስጥ የተፈናቃዮችን መጠለያ ጣቢያ ያጠፈዉ ጎርፍ ነዉ-ዉኃ።ሥደተኞችን የበላዉ-ባሕር ነዉ።ዉኃ።...more15minPlay
September 08, 2025የኦሮሚያ የጸጥታ ኹኔታ እና የአዲሱ ዓመት መባቻዓመታትን ያስቆጠረው የትጥቅ ትግል አሁንም ድረስ መቋጫ አላገኘም ። አንዴ ውጥረት እያነገሰ ሌላ ጊዜ ረገብ እያለ የቀጠለው የታጣቂዎች እና የመንግስት የጸጥታ አካላት ግጭት ለማህበረሰቡ ሌላ ስጋት ካስከተለ ሰነበተ ። ዕገታ ፤ የዘፈቀደ ግድያ እና ዘረፋ ደግሞ ዋነኞቹ ናቸው ።...more15minPlay
August 25, 2025ማሕደረ ዜና፣የኢትዮጵያ ጉዞ አቅጣጫዉ ይታወቅ ይሆን?ኢትዮጵያ ከሉሲ ግኝት እስከ አክሱም ሐዉልቶች፣ ዋልያን ከመሰሉ-እንስሳት እስከ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ከሶፍ ዑመር ዋሻ-እስከ ሐረር ግንብ፣ ከአድዋ እስከ ካራማራ ድል የሚደርሱ የጥንታዊ ሥልጣኔ፣ የተፈጥሮ ፀጋ፣ የጀግንነት ታሪኮች ባለቤት መሆንዋ አያከራክርም።የዚያኑ ያክል የርስበርስ ጦርነት፣ የጎሳ ጥቃትና የፖለቲካ ዉዝግብ ኢትዮጵያን ቁል ዉል እየደፈቋት ነዉ።የድሕነት፣የበሽታና የረሐብ አስከፊነት ከተጠቀሰ የኢትዮጵያዉያን ቁጥር የአሐዞች ማድመቂያ ነዉ።የኑሮ ዉድነት፣ሥራ አጥነት፣የስደተኞች ብዛትና ሞት ከተዘረዘረ ኢትዮጵያና ዜጎችዋን ማለፍ አይቻልም።ሥርዓተ አልበኝነት፣ እገታና ዘረፋም ከኢትዮጵያ «መለያዎች» እየተካተቱ ነዉ...more14minPlay
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 339 episodes available.