Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀር... more
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 340 episodes available.
August 25, 2025ማሕደረ ዜና፣የኢትዮጵያ ጉዞ አቅጣጫዉ ይታወቅ ይሆን?ኢትዮጵያ ከሉሲ ግኝት እስከ አክሱም ሐዉልቶች፣ ዋልያን ከመሰሉ-እንስሳት እስከ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ከሶፍ ዑመር ዋሻ-እስከ ሐረር ግንብ፣ ከአድዋ እስከ ካራማራ ድል የሚደርሱ የጥንታዊ ሥልጣኔ፣ የተፈጥሮ ፀጋ፣ የጀግንነት ታሪኮች ባለቤት መሆንዋ አያከራክርም።የዚያኑ ያክል የርስበርስ ጦርነት፣ የጎሳ ጥቃትና የፖለቲካ ዉዝግብ ኢትዮጵያን ቁል ዉል እየደፈቋት ነዉ።የድሕነት፣የበሽታና የረሐብ አስከፊነት ከተጠቀሰ የኢትዮጵያዉያን ቁጥር የአሐዞች ማድመቂያ ነዉ።የኑሮ ዉድነት፣ሥራ አጥነት፣የስደተኞች ብዛትና ሞት ከተዘረዘረ ኢትዮጵያና ዜጎችዋን ማለፍ አይቻልም።ሥርዓተ አልበኝነት፣ እገታና ዘረፋም ከኢትዮጵያ «መለያዎች» እየተካተቱ ነዉ...more14minPlay
August 18, 2025ማሕደረ ዜና፣ የዩክሬን ጦርነት፣የጉባኤ ጋጋታና የዲፕሎማሲዉ ዉጣ ዉረድ3 ዓመት ከመንፈቅ።ጦርነቱ አንዳዶች እንደገመቱት ከሁለቱም ወገን በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ወታደር አልቆበታል።በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሠላማዊ ሰዉ ተገድሏል።ቆስሏል።ተፈናቅሏልም።በብዙ መቶ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሐብት ንብረት ወድሟል።ዩናይትድ ስቴትስ፣ የአዉሮጳ ሕብረትና ብሪታንያ ከመቶ ቢሊዮን ዶላር በላይ ከስክሰዋል።ያሸነፈም፣ የተሸነፈም የለም።የጦርነቱ መሠረታዊ ምክንያት ምንም ሆነ ምን ከግዛት ይገባኛል ያለፈ ሰበብ አልቀረበበትም።ተጨማሪ ሕይወት፣ ሐብትና ንብረት እንዳይጠፋ የዩናይትድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ባለፈዉ ቅዳሜ አንዳሉት ተፋላሚዎች ሰጥቶ ለመቀበል ፈቃደኛ ሊሆኑ ይገባል።...more15minPlay
August 11, 2025ማሕደረ ዜና፤ የጋዛ እልቂት፣ የእስራኤል አዲስ ዕቅድና የገጠመዉ ተቃዉሞበእስራኤልና በጠላቶችዋ አፀፋ ጥቃት ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ፣ ቤይሩት፣ ሐይፋ፣ ቴሕራን፣ ብዙ ሺሕ ሕዝብ አልቋል።የጋዛ ለብቻዉ ነዉ።የግዛቲቱ የጤና መስሪያ ቤት እንዳስታወቀዉ ከ60ሺሕ በላይ ሕዝብ ተገድሏል።ረሐብ የፈጀዉ ሰዉ ቁጥርም ወደ ሁለት መቶ ተቃርቧል።ሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል።እስራኤልም ወደ 800 የሚሆኑ ወታደሮች ተገድለዋባታል።22 ወራት።ከዚሕ ሁሉ እልቂት፣ስደት፣ረሐብ፣ ስቃይ-ሰቆቃ፣ በኋላ የጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ ዕቅድ ከግብ አልደረሰም።...more14minPlay
August 04, 2025ማሕደረ ዜና፣ ሒሮሺማ-የመጀመሪያዋ የአዉቶሚክ ቦምብ ሰለባ 80ኛ ዓመት«ያየነዉን ማመን በጣም ከባድ ነበር።» አሉ ኮሎኔል ቲቤትስ ኋላ።«አንዱ ባልደረባችን «የፈጣሪ ያለሕ» ሲል ሰማሁት» አከሉ ኮሎኔሉ።እነሱ የሚጥበረብር አስደንጋጭ ብልጭታ፣ ሰቅጣጭ-ድምፅ፣ ሐምራዊ፣ሰማያዊ ነጭ ቀለም ያለዉ ወፍራም፣ እምቅ፣ ጢሱን ሰንጥቀዉ ወደ መጡበት ተፈተለኩ።መሬት ላይ ለነበሩት ግን የዕልቂት እቶን በር ተበረገደ።አፍንጫ የሚሰነፍጥ ቅርናት፣ጆሮን የሚሰቀጥጥ የሰቆቃ ጩኸት፣ ከተቀመጡት አስፈንጥሮ የሚያንሳፍፍ ንዝረት፣ ትንፋሽ የሚያሳጣ ወበቅ---ዕልቂት።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ሐሪስ ኤስ ትሩማን እንዳሉት ግን ለዩናይትድ ስቴትስና ለተባባሪዎቿ ታላቅ የታላቅ ድል የመጀመሪያ ምዕራፍ ነዉ...more14minPlay
July 28, 2025ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ ቀዉስ ማብቂያ ያገኝ ይሆን?የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ሥልጣን የያዙ ይሁኑ ተቃዋሚዎች ምንም አሉ-አደ,ረጉ፣ግጭት፣ጥቃት፣ ግድያ፣ እገታ፣ዘረፋና ስርዓተ አልበኝነት ግን ለኢትዮጵያዉያን የአዘቦት ትርዒት እስኪመስል ድረስ እንደቀጠለ ነዉ።የመንግሥት ባለሥልጣናትና ደጋፊዎቻቸዉ የቀዉሱን ንረት፣የሚያደርሰዉን ጥፋትና ምናልባት መፍትሔዉን የሚነግሯቸዉን ሁሉ የዚሕ ወይም የዚያ ጎሳ፣ ቡድንና ፓርቲ አባል እያሉ ከመፈረጅ ባለፍ እስካሁን መፍትሔ መስጠት አልቻሉም።ወይም አልፈለጉም።የኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብታዊ ድቀት፣ ግጭት፣ ጥቃትና ምሥቅልቅሉ ኢትዮጵያዉያን ላይ የሚያደርሰዉ ጥፋት፣ አልበቃ ያለ ይመስል ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሐገራት ጋር የገጠመችዉ አተካራ ሌላ ጭንቀት ሆኗል...more14minPlay
July 14, 2025ማሕደረ ዜና፣ የቀይ ባሕር አካባቢ መንግሥታት ዉስብስብ ግጭትና ዉጥረትነሐሴ ላይ አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት አብዱረሕማን መሐመድ ኢሮ አዲስ አበባን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።ጉብኝቱ «በጠወለገዉ» የመግባቢያ ስምምነት ላይ ነብስ ከዘረባት እስካሁን ገሚስ የህወሓት መሪዎችን የክበቡ አካል ለማድረግ የሚዉተረተረዉ የሞቃዲሾ፣ ካይሮ፣ አሥመራ ገዢዎች አክሲስ ወይም ሥብስብ ምናልባት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦብነግ) ገሚስ መሪዎችን ሊያቅፍ፣ አጓጉል መዘዙ ከትግራይ እስከ ኦጋዴን ሊደርስ ይችላል።...more14minPlay
July 07, 2025ማሕደረ ዜና፣ የጋዛ ተኩስ አቁም ተስፋ፣ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ዕዉነታየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ ዛሬ ዋሽግተን ዉስጥ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በሚያደርጉት ዉይይት ሁለቱ መሪዎች የዓመት ከዘጠኝ ወራቱን ወታደራዊ ዘመቻ ለ60 ቀናት ለማቆም ያላቸዉን ዕቅድ ያስታዉቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።ዩናይትድ ስቴትስና ቀጠር አቀረቡት የተባለዉን ሐሳብ እስራኤልም-ሐማስም ተቀብለዉታል ተብሏል።ሐሳቡ መፅደቅ-መዉደቁ የሚወሰነዉ ግን በትራምፕና በኔትንያሁ ትዕዛዝ ነዉ።...more13minPlay
June 30, 2025ማሕደረ ዜና፤ የእስራኤል፣ የአሜሪካና የኢራን የጦርነት ማግሥት የጦርነት ዝግጅትበርግጥ ጀግናዉ ማነዉ? 12 ቀናት የቆየዉን፣ከ600 በላይ ኢራናዉያንን፣ 28 እስራኤላዉያንን የገደለዉን፣ የሁለቱን ሐገራት ምጣኔ ሐብት ያሽመደ።መደዉን ዉጊያ ቀድማ የከፈተችዉ እስራኤል ናት።ዩናይትድ ድብደባዉን ፈቅዳለች፣ ኋላ ራሷ ቀጠላበታለች።አሁን የሚሞጋገሱት የሁለቱ ጥብቅ ወዳጅ መንግሥታት መሪዎች ኢራንን ለመደብደባቸዉ የሰጡት ምክንያት የቴሕራንን የኑክሌር ተቋማት ለማዉደም ነዉ።ወሕኒ ቤት የኑክሌር ተቋም ይሆን?...more14minPlay
June 23, 2025ማሕደረ ዜና፤ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉጊያ፣ መዘዙና ሕግ አልባዋ ዓለምየቀድሞዉ የዶናልድ ትራምፕ የፀጥታ አማካሪ ጆን ቦልተን ባንድ ወቅት «የዓለም ማሕበረሰብ የሚባል ነገር የለም።ያለችዉ አንድ ልዕለ ኃያል ሐገር ናት-ዩናይትድ ስቴትስ።» ብለዉ ነበር።አላበሉም።ዓለም የጋራ ማሕበር፣ ፍርድ ቤት፣ ሕግ፣ ደንብ፣ ሥምምነት የሚኖራት ለአሜሪካና ለእስራኤል እስከጠቀመ ብቻ ነዉ።ባይሆን ኖሮ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯ ከተወገዘ፣ በማዕቀብ ካስቀጣ፣እስራኤልና አሜሪካ ሊባኖስን፣የመንን፣ ሶሪያን፣ኢራንን መደብደባቸዉ፣ታጣቂዎችን ከሕሙማን ሳይለዩ መግደላቸው የማያስወገዝ፣ የማያስጠይቅ፣ የማያስቀጣበት ምክንያት የለም።...more13minPlay
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 340 episodes available.